ለንደን ማራቶን፡ ዛሬ በሚከናወነው በትልቁ የአትሌቲክስ መድረክ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተጠባቂ ናቸው

ቀነኒሳ ሁለተኛው ፈጣን የማራቶን ሰዓት ያስመዘገበ ሲሆን የዓለምዘርፍ ደግሞ የባለፈው ዓመት የለንደን ማራቶን አሸናፊ ነች።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ቀነኒሳ ሁለተኛው ፈጣን የማራቶን ሰዓት ያስመዘገበ ሲሆን የዓለምዘርፍ ደግሞ የባለፈው ዓመት የለንደን ማራቶን አሸናፊ ነች።
ታትሟል

በማራቶን ውድድር ከፍተኛ ግምት ከሚሰጣቸው መድረኮች መካከል አንዱ በሆነው የለንደን ማራቶን ተሳታፊ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተጠባቂ ናቸው።

በወንዶች የማራቶን ውድድር ቀነኒሳ በቀለን ጨምሮ በርቀቱ የዓለማችን ፈጣን የሆኑ 4 አትሎቶች ተሳታፊ ይሆናሉ። ከቀቀኒሳ በተጨማሪ እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ የውድድሩ ተሳታፊ ነው።

ቀነኒሳ የማራቶን ሪኮርድ ባለቤት ከሆነው ኬንያዊው ኢሉዩድ ኪፕቾጌ በቀመጠል ሁለተኛው የዓለማችን ፈጣን የማራቶን ሰዓትን አስመዝግቧል።

ቀኒነሳ 42 ኪሎ ሜትር ርቀትን 2፡01፡41 በመሮጥ ምርጡን የግል ሰዓት አስመዝግቧል።

አራት ጊዜ የኦሎምፒክ ወርቅ አሸናፊ የሆነው ሞ ፋራህ ዛሬ ከእኩለ ቀን ላይ በሚጀመርው ውድድር ተጠባቂ አትሌት ነው። ሞ ፋራህ የለንደን ማራቶን የመጨረሻው ውድድሩ እንደሆን ለቢቢሲ ተናግሯል።

ከሁለቱ አትሌቶች በተጨማሪ የ2022 ቫሌንሺያ ማራቶን በ2፡01፡53 ያሸነፈው ኬንያዊ ኬልቪን ኪፕቱም ተጠባቂ ነው።

የማራቶን ውድድርን ከሁለት ሰዓት ከሁለት ደቂቃ በታች የጨረሱ ሁለት አትሌቶች በአንድ ላይ ሲገናኙ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ከአንድ ዓመት በፊት ተካሂዶ በነበረው የለንደን ማራቶን ቀነኒሳ ውድድሩን ሊያሸንፍ እንደሚችል ትልቅ ግምት ተሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ከአሸናፊው አሌክስ ኪፕሩቶ ከአንድ ደቂቃ በላይ ዘግይቶ አምስተኛ ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል።

የ Instagram ይዘትን ይለፉት
ይዘቱን Instagram ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በInstagram. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የInstagram ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ: በሌሎች ገጾች ላይ ላሉ ይዘቶች ቢቢሲ ኃላፊነት አይወስድም።

የ Instagram ይዘት መጨረሻ

በበርሊን ማራቶን የምንግዜም ምርጥ ሰዓቱን ያስመዘገበው ቀነኒሳ የተለያዩ ጉዳቶች ሲገጥሙት ነበር።

ከቀነኒሳ በመቀጠል ፈጣን ሰዓት ያላው ኬቪን ኪፕቱም ነው። ከአራት ወራት በፊት የቫሌንሺያ ማራቶንን ያሸነፈው ኬልቪን ድንቅ አቋም ላይ ይገኛል።

የባለፈው ዓመት የለንደን ማራቶን አሸናፊ አሞስ ኪፕሩቶ የ2022 ድሉን ዘንድሮም ለማሳካት ይሮጣል።

የኒው ዮርክ ሲቲ ማራቶን አሸናፊ ኬንያዊ ጂዮፌሪ ካምዎሮሮ፣ የ2022 የለንደን ማራቶን ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኢትዮጵያዊው ልዑል ገ/ስላሴ እንዲሁም የ2020 እና 2021 የለንደን ማራቶን ሁለተኛ ደረጃን ይዞ የጨረሰው ቪንሰንት ኪፕቹምባ ዛሬ ከሚጠበቁ አትሌቶች መካከል ይገኙበታል።

በሴቶች እነ ማን ይጠበቃሉ?

በሴቶች የለንደን ማራቶን ተጠባቂ አትሌቶች መካከል ሲፈን ሐሰን ንግግር እያደረገች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በሴቶች የለንደን ማራቶን ተጠባቂ አትሌቶች መካከል ሲፈን ሐሰን ንግግር እያደረገች

በሴቶች የውድድር መድረክም በኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያዎች አሸናፊዎች ስብስብ የደመቀ ነው።

በቶኪዮ ኦሊምፒክ በማራቶን ውድድር ወርቅ አሸናፊ የሆነችው ፒርስ ጄፕቺርቺር ቁጥር አንድ ተጠባቂ አትሌት ናት።

የባለፈው ዓመት የለንድን ማራቶን ውድድር አሸናፊዋ ያለምዘርፍ የኋላው ክብሯን ለማስጠበቅ ትሮጣለች። ያለም ዘርፍ በ2022 በለንደን ማራቶን ታሪክ ሦስተኛ ፈጣን በሆነ ሰዓት 2፡17፡26 ነበር ያሸነፈችው።

ለኔዘርላንድስ የምትሮጠው እና የኦሊምፒክ የ5ሺህ እና 10ሺህ ሜትር ሻምፒዮኗ ሲፈን ሐሰን በለንደን ተገኝታለች። ሲፈን በማራቶን ውድድር ስትሳተፍ ይህ የመጀመሪያዋ ይሆናል።

ድንቅ አቋም ላይ የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም የውድድሩ ተሳታፊ እና ተጠናቂ ናቸው። የሪዮ ኦሊምፒክ የ10ሺህ ሜትር ወርቅ አሸናፊ አልማዝ አያና ተወዳዳሪ አትሌት ናት።

ገንዘቤ ዲባባ እንዲሁም የ2022 የበርሊን ማራቶን ሻምፒዮን ትግስት አሰፋ ዛሬ በለንደን ማራቶን የምንመለከታቸው ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች ናቸው።

ሌላ የብዙዎችን ትኩረትን የገዛችው የብሪታኒያዋ ኤሊሽ ማክኮልጋን ናት። በኮመንዌልዝ ውድድር የ10ሺህ ሜትር አሸናፊዋ በአሁኑ ሰዓት ድንቅ አቋም ላይ ትገኛለች።

የለንደን 2023 የሴቶች ማራቶን ውድድር በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከረፋዱ 5፡23 ሲል የሚጀምር ሲሆን የወንዶቹ ደግሞ 45 ደቂቃዎችን ዘግይቶ እኩለ ቀን 6 ሰዓት ላይ ይጀምራል።