በጌዴኦ ዞን የጣለው ከባድ ዝናብ ለሰዎች ሞትና መፈናቀል ምክንያት ሆነ

የፎቶው ባለመብት, Gedeo Zone Government Communication Affairs
ታትሟል
በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን ይርጋ ጨፌ ወረዳ በጭቶ፣ በዶማርሶና ቡዱቅሳ በተባሉ ቀበሌዎች የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የአንድ ሰዉ ህይወት ሲያልፍ 156 ሰዎች ደግሞ ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸው ተዘገበ።
የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዮሐንስ ታደሰን ጠቅሶ በማህበራዊ ተስስር ገጹ ባወጣው መረጃ ትላንት [መስከረም 22 -2014] በጣለዉ ከባድ ዝናብ በ 39 አባወራዎች ውስጥ ታቅፈው የነበሩ 156 ሰዎች ገልጿል።
በወረዳው ከቀኑ 7:00 እስከ 10:00 ድረስ በጣለዉ ከባድ ዝናብ የዶማርሶ ቀበሌ አንድ ነዋሪ ህይወቱም አልፏል።
ከቤት ንብረት የተፈናቀሉት ከ150 የሚልቁ ሰዎች በአከባቢው ባሉ አደጋው ጉዳት ባላደረሰባቸው ቤቶች መጠለላቸውም ተግቧል። በአሁኑ ጊዜ የነፍስ አደን ተግባር እየተከናወነ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን አደጋው በደረሰበት አከባቢ ተመሳሳይ አደጋ እንዳይከሰት ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ጥሪ ቀርቧል።








