የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ ሰልፍ ከ160 በላይ ከተሞች ላይ ተካሄደ

የፎቶው ባለመብት, Reuters
በብራዚል በሺዎች የሚቆጠሩ የተቃውሞ ሰልፈኞች በትላልቅና ትንሽ ከተሞች የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት ጄር ቦልሶናሮ በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን እንዲወርዱ የተጠየቀበትና ሀገሪቱ ምርጫ ልታካሂድ አንድ ዓመት እየቀራት የተቀሰቀሰውን ይህ ተቃውሞ የሠራተኛ ማህበራትና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች ያስተባበሩት ነው።
ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ ከምርጫው ቀደም ብሎ እየተሰበሰቡ ባሉ የድምጽ ሰጪዎች አስተያየት ተሸናፊ እየሆኑ ነው ተብሏል።
ፕሬዝዳንቱ ከ 600 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡበትን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን የያዙበት መንግድ ብራዚላውያን አበሳጭቷል።
ቅዳሜ ዕለት በብራዚል በሚገኑ ከ160 በሚበልጡ ከተሞች ፕሬዝዳንቱን የሚቃወሙ ሰልፎች የተካሄዱ ሲሆን ተሳታፊዎች ፕርዝዳንት ቦልሶናሮ ከሥልጣን እንዲነሱ የሚጠይቅ ምስሎችን ይዘው ተይተዋል።
"እዚህ ያለው ፕሬዝዳንት በዓለም ውስጥ ኋላ ቀር የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ይወክላል ። ረሃብ ፣ ድህነት ፣ ሙስና አለ እናም እኛ ዲሞክራሲን ለመጠበቅ ወጥተናል" ሲል ቫልዶ ኦሊቬራ የተባለ የሰልፉ ተሳታፊ ለኤ ኤፍ ፒ የዜና ወኪል ተናግሯል።
ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮን ከስልጣን ለማውረድ ለሀገሪቱ ምክር ቤት ከ 100 በላይ ጥያቄዎች የቀረቡ ቢሆንም የምክር ቤቱ መሪ ጥያቄዎቹን ለመመከት ፍቃደኛ አልሆኑም።
የብራዚል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግን በቅርቡ በፕሬዝዳንቱ ላይ የሚካሄዱ በርካታ ምርመራዎችን አጽድቋል።
ከቅዳሜ የተቃውሞ ሰልፍ በፊት ባለፈው ወር ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮን የሚደግፉ በርካታ ሰልፎች ተደርገው ነበር። ይህም ፕሬዝዳንቱ ብዙ ሰው እንደሚግፋቸው ለማስመል የተደረገ ሙከራ ነው ተብሏል።
ፕሬዝዳንቱ እስከቀጣዩ ዓመት በስልጣን የሚቆዩ ቢሆንም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የሚጸደቋቸው ውሳኔዎች አሽቋልቁሏል።
በአትላስ ኢንስቲትዩት በተሰበሰበ የሕዝብ አስተያየት 61 በመቶ ብራዚላውያን የመንግሥታቸውን አፈጻጸም 'መጥፎ' ወይም 'በጣም መጥፎ' ነው ብለው ገልጸዋል። እንደ አውሮፓውያኑ በ2019 የቦልሶናሮ አመራራር ወደ ስልጣን ሲመጣ በተመሳሳይ መንገስ በተሰበሰበ የህዝ አስተያየት ያገኘው ድምጽ 23 በመቶ ነበር።












