የ95 አመቷ አዛውንት በናዚ ማጎሪያ ካምፕ ጭፍጨፋ ተወነጀሉ

የፎቶው ባለመብት, EPA
በናዚ የማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ፀሃፊ ነበሩ ነበሩ የተባሉ የ95 አመት አዛውንት በሰሜን ጀርመን ውስጥ በጅምላ ግድያ ወንጀል ተወንጅለዋል።
ኢምግራንድ ኤፍ የተባሉት አዛውንት ሃምበርግ በሚገኝ የአረጋውንያን እንክብካቤ ማዕከል የሚኖሩ ሲሆን ከአስር ሺህ በላይ ክሶች ቀርበውባቸዋል።
ስተትሆፍ በተባለው አሰቃቂ የማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ፀሃፊ የነበሩ ሲሆን በካምፑ ውስጥ በነበረው የጅምላ ግድያና ጭፍጨፋ አስተባብረዋል በሚልም ነው እየተወነጀሉ ያሉት።
በሁለተኛው አለም ጦርነት ወቅት በዚሁ ማጎሪያ ካምፑም 65 ሺህ ሰዎች እንደሞቱ ተገልጿል።
የፍርድ ሂደቱ እንዴት እንደሚካሄድ እስካሁን ያልሆነ ግልፅ ሲሆን ግለሰቧ በጭፍጨፋው የነበራቸው ተሳትፏውም እየተጠና ነው ተብሏል።
ስተትሆፍ የማጎሪያ ካምፕ በናዚ ቁጥጥር ስር በነበረችው ፖላንድ በ1939 የተቋቋመ ሲሆን ጠባቂዎቹ በ1944 የመርዝ ጋዝ ከተጠቀሙባቸው ዘግናኝ የእልቂት ስፍራዎች አንዱ ነው።
ካምፑን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ የቀድሞዋ ሶቭየት ወታደሮች በ1945 ነፃ አወጡት።
በካምፑ 100 ሺህ የሚሆኑ ታራሚዎች ዘግናኝ በሚባል ሁኔታ ላይ ነበሩ፤ በርካታዎቹ በበሽታና በረሃብ አልቀዋል። አንዳንዶቹም በመርዛማ ጋዝና በገዳይ መርፌ ተገድለዋል።
ግለሰቧ ጭፍጨፋው ሲፈፀም ከ21 አመት በታች ስለነበሩ ከእድሜ በታች የሚቆጠሩ በመሆኑ ክሱ እንዴት መታየት አለበት የሚለው ላይ የሸልስዊግ ሆልስቴይን ፍርድ ቤት መወሰን አለበት።
አዛውንቷ በማጎሪያ ካምፑ ውስጥ መርዛማ ጋዝ ይጠቀሙ እንደነበር አላወቅኩም ብለዋል።
ከናዚ ማጎሪያ ካምፕ እልቂቶች ጋር ተያይዞ ወደ ፍርድ የቀረቡት ጥቂት ሴቶች ሲሆኑ እነሱም የካምፑ ጠባቂዎች እንደሆኑና የግለሰቧ የፀሃፊነት ሚና ክሱን ለየት እንደሚያደርገው የቢቢሲው ዳሚየን ማክ ጊነስ ከበርሊን ዘግቧል።
አቃቤ ህግ ኢርምግራድ ኤፍን ስለነበራቸው ሚና የጠየቃቸው ሲሆን በ2016ም ምርመራ ተከፍቶባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከማጎሪያ ካምፑ ተርፈው ለነጋሪነት የበቁ ሰዎችን አቃቤ ህግ በእስራኤል እንዳናገራቸው የጀርመኑ ሚዲያ አርድ ሪፖርት አድርጓል።
በ10 ሺህ ክሶች ላይ የጅምላ ግድያን በማስተባበርና በማሳለጥ አንዲሁም በግድያ ሙከራ ተወንጅለዋል።
የቀረበባቸው ውንጀላ እንደሚያስረዳው ይሁዳውያን እስረኞች፣ የፖላንድ ተቃዋሚዎችና የሶቭየት ህብረት የጦር እስረኞች በጭምላ እንዲገደሉ ረድተዋል ይላል።
ግለሰቧ በ1943-1945 ፀሃፊ በነበሩበት ወቅት ነው ይህን እልቂት የረዱትና ያስባበሩት በክሱ መሰረት-












