ኮሮናቫይረስ፡ "ኮቪድ-19ን አትፍሩት" ትራምፕ ከሆስፒታል ሲወጡ

ዶናልድ ትራምፕ

የፎቶው ባለመብት, EPA

ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 1 ደቂቃ

በኮሮናቫይረስ ተይዘው ለሶስት ቀናት ሆስፒታል አልጋ ላይ ውለው የነበሩት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህክምናቸውን በቤተ መንግሥታቸው፣ ዋይት ሃውስ ለመቀጠል ከሆስፒታል ወጥተዋል።

ዋይት ሃውስ በረንዳም ላይ ሲደርሱም ጭምብላቸውን አውልቀውታል። ይህም ሁኔታ በርካታ የዋይት ሃውስ ሰራተኞች በቫይረሱ በተያዙበት ሁኔታ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም አስደናቂ አድርጎታል።

"በጣም በጥሩ ስሜት ላይ ነኝ። ኮቪድን አትፍሩት። ህይወታችሁን እንዲቆጣጠረው አትፍቀዱለት" በማለትም በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

አሜሪካውያን ቫይረሱን እንዳይፈሩት ባስተላለፉበት የትዊተር መልዕክታቸውም " በአሁኑ ወቅት ከሃያ አመታት በፊት ከነበረው ጥሩ ስሜት ይሰማኛል፤ በቅርቡም ወደ ምረጡኝ የቅስቀሳ ዘመቻዬ እመለሳለሁ" በማለትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በኮሮናቫይረስ ክፉኛ በተመታችው አሜሪካ 7.4 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፣ 210 ሺህ ዜጎቿም ህይወታቸውን አጥተዋል።

ከፕሬዚዳንቱ ህመም ጋር በተያያዘ እርስ በርስ የሚጋጩ መግለጫዎች መውጣታቸውን ተከትሎ የትራምፕ ህመም ምን ያህል የጠና ነበር የሚለው ላይ ጥያቄ አስነስቷል።

ፕሬዚዳንቱ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ ለሁለተኛ ጊዜ ለመመረጥ የሚያደርጉትና፣ ወር የቀረውን የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳቸውን አቋርጠው ነበር።

ዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘው ዋልተር ሪድ የህክምና ማዕከል ሲወጡም " ሁላችሁንም አመሰግናለሁ" ያሉ ሲሆን ከሚዲያዎች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት አልፈቀዱም።

አጠር ካለ የሄሊኮፕተር በረራ በኋላም በዋይት ሃውስ የደረሱ ሲሆን ጭምብላቸውን አውልቀው ብራቮ በሚልም የአውራ ጣታቸውን ምልክት አሳይተዋል እንዲሁም የጦሩን ሰላምታ አይነትም ሰጥተዋል።

የ X ይዘትን ይለፉት
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ

1px transparent line

ፕሬዚዳንቱ አሜሪካውያን ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመልሱ የሚጠይቅም የቪዲዮ መልዕክት አስተላልፈዋል።

"ታሸንፉታላችሁ፤ ምርጥ የሆኑ የህክምና ቁሳቁሶች አሉን። በቅርቡ የተሰራ ምርጥ መድኃኒት አለን" ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ክትባት በቅርብ እንደሚመጣ ቢናገሩም የአሜሪካ የበሽታዎች ቁጥጥርና ክትትል ማዕከል በበኩሉ በአሁኑ ወቅት የሚጠበቅ ክትባት እንደሌለ አስታውቋል።