የበር መጥሪያ ደወሎች በፖሊስ ላይ መሰለል ማስቻላቸው ኤፍቢአይ ስጋት ሆኖብኛል አለ

ታትሟል

በቤቶች ውስጥ የሚገጠሙ የተራቀቁ የመጥሪያ ደወሎችን ፖሊሶችን ለመከታተልና ለመሰለል አንዳንዶች እየተጠቀሙበት መሆኑ የአሜሪካው የፌደራል የወንጀል ምርመራ ድርጅት ኤፍቢአይ ስጋት አጭሮብኛል ብሏል።

ተመንትፈው ከተገኙ መረጃዎችም ነው ነዋሪዎች የቤት መጥሪያ ደወሎችን ፖሊሶችን ለመሰለል መጠቀማቸው ኤፍቢአይን እንዳሳሳበው የጠቆመው።

ከሶስት አመታት በፊት አንድ ግለሰብ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ፖሊስ ሲያዘጋጅ በርቀት እየተከታተለው እንደሆነ የሚያሳይ ቪዲዮ ወጥቷል።

መረጃው የተገኘው በኢንተርሰፕት አማካኝነት ሲሆን ተመነተፉ ከተባሉ መረጃዎች መካከል ነው።

ከሶስት አመታት በፊት የተገለፀው ይህ ሁኔታ አንድ ተጠርጣሪ ፖሊስ በግቢው ውስጥ ገብቶ የፍርድ ቤት ትዕዛዙን በሚያስተካክልበት ወቅት ጎረቤቶቹንና አከራዮቹን ማሳወቅ ችሏል።

የመጥሪያው ደወሉን የሰራው የትኛው ኩባንያ እንደሆነ አልተገለፀም።

ከዚህ ቀደም የግለሰቦችን ነፃነትና የግል መረጃዎችን መጠበቅ አለባቸው በሚሉ ተሟጋቾች ዘንድ እነዚህ የዘመናዊ የቤት መጥሪያ ደወሎች መረጃዎች ለፖሊስ ተላልፈው መሰጠታቸው ስጋት ነው በማለትም ሲከራከሩም ነበር።

ብሉ ሊክስ የሚል ስያሜ የተሰጣቸው እነዚህ የተመነተፉ መረጃዎች ከ250 የፖሊስ ድረገፆች የተሰረቁ ናቸው ተብሏል።

መረጃዎቹ በአጠቃላይ በቤት ውስጥ የሚገኙ የደህንነት ስርዓቶችን የፈተሸ ሲሆን በተለይም በቤት ውስጥ የሚተከሉ የመጥሪያ ደወሎች ያላቸውን ጥሩ ነገርና ተግዳሮቶችን የሚፈትሽ ጥልቅ መረጃዎችን በዝርዝር የያዘ ነው።

በአሁኑ ወቅት ታዋቂው የመጥሪያ ደወል አማዞን ቢሆንም በርካታ ኩባንያዎች የተለያዩ ሁኔታዎችን መከታተል የሚያስችሉ ፓኬጆችንም አካተዋል።

ከዚህ ቀደም ስጋት የነበረው መጥሪያ ደወሎች ላይ ያለው ካሜራ ለፖሊስ ተላልፎ መሰጠቱ የግል መረጃን መብት ጥበቃን የሚተላለፍ ነው የሚሉ ስጋቶች ቢኖሩም አሁን በተቃራኒው በፖሊስ ላይ መሰለል አስችሏል ተብሏል።

በባለፈው አመት የአማዞን ኩባንያ ከ200 የአሜሪካ የህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች ጋር በመተባበር የቤት መጥሪያ ደወሎቹን ለክትትልና ቁጥጥር ተጠቅሞበታል በሚልም ተተችቷል።

ከአማዞን ጋር በፈጠሩት ሽርኪያም መሰረት ደንበኞች በአካበባቢያቸው የተፈፀመው ወንጀሎችን ለመመርመር ከመጥሪያ ደወሎች የተገኙ ቪዲየዎችን ለፖሊሶች እንዲሰጡ ይጠየቃሉ።

የመረጃ ነፃነትን ማስከበር ላይ የሚሟገተው ቡድን ዘ ፊውቸር ይህ ሁኔታ ዲሞክራሲያዊ ሂደትንና መብቶችን የሚጥስ ነው በማለትም አውግዟል።

በዩናይትድ ኪንግደምም እንዲሁመ መጥሪያ ደወሎችና የደህንነት ካሜራ በቤታቸው ያላቸው ደንበኞች እንዲያስመዘግቡም ፖሊስ ይጠይቃል።