ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የሩሲያ ጦር ዶንባስን ለመቆጣጠር የሚያስችለውን ቁልፍ ከተማ መክበቡ ተገለጸ
የሩሲያ ጦር በምሥራቅ ዩክሬን ስትራቴጂክ የሆነውን ኮስታያንታያኒቪካ ከተማ በከበባ ውስጥ እያስገባ እንደሚገኝ ተገለጸ።
የዩክሬን ወታደሮች ለቢቢሲ እንደገለጹት ከተማው ሙሉ በሙሉ በየትኛውም ኃይል ሥር ስላልወደቀ "ግራጫ ክልል" ሆኗል።
"ከጀርባችን ያሉ አካባቢዎች ላይ ሰፍረዋል። ገፍቶ ለማስወጣት በጣም ከባድ ነው" ሲል በአካባቢው የተሰማራ የዩክሬን የድሮን አብራሪ አሁን ያለውን ሁኔታ ገልጿል።
ከተማው ለዶንባር ቅርብ መሆኑ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ አለው።
የሩሲያ ጦር ከተማውን ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠረ የዩክሬን ወታደሮች በምሥራቃዊ ክልል የመጨረሻ ጠንካራ ይዞታ የሆኑ ሥፍራዎችን መያዝ ይችላል።
የሩሲያ ወታደሮች ክራማቶስክ እና ስሎቪናስክ የተባሉ ከተማዎችን መያዝ ከቻሉ ዶንባስን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥራቸው ሥር ያደርጋሉ።
ዶንባር ከተማን መያዝ የክሬምሊን ዋነኛው የጦርነቱ ግብ ነው።
ዩክሬን ላለፉት ጥቂት ወራት በጠንካራ ሁኔታ ግዛቶቿን መቆጣጠር ችላ ቆይታለች። በያዝነው ዓመት ሰፊ የዩክሬን ይዞታዎችን ማስመለስ እንደተቻለም ተገልጿል።
በሩሲያ ይዞታ ሥር በምትገኘው ክሬሚያ በክሬምሊን የተመረጡ መሪዎች የነዳጅ እጥረት ስለገጠማቸው ለሕዝብ እንዳይሸጥ ከልክለዋል።
ኪቭ በሞስኮ እና ሴንት ፒተርስበርግ በሚገኙ ነዳጅ ማምረቻዎች ላይ በተከታታይ ጥቃት አድርሳለች።
የሩሲያ ወታደሮች ከደቡባዊ አቅጣጫ ተነስተው ኮስታያንታያኒቪካ ከተማ አቅራቢያ ታይተዋል።
ሞስኮ ጦሯ በደቡብ ምዕራብ በኩል በፍጥነት እየገሰገሰ እንደሆነ እና የዩክሬንን ወታደሮች እንደከበበ አስታውቃለች።
የኪቭ 19ኛ ሠራዊት ክፍል የጦር አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ኦሌክሳንደር ባኩሊን ይህንን አስተባብለዋል።
"ሁኔታው በቁጥጥራችን ሥር ነው። ጠላት አልተሳካለትም" ብለዋል።
ሆኖም ግን በከተማው ወደ 130 የሚጠጉ የሩሲያ ወታደሮች መኖራቸውን አምነዋል።
ቢቢሲ ያነጋገረው የዩክሬን ጦር ኃላፊ እንዳለው አሁን ያለው ሁኔታ ሞስኮ እንደገለጸችው የከፋ ወይም ኪቭ እንዳለችው የለዘበ ላይሆን ይችላል።
"አሁንም በከተማው ውስጥ ጥቃት ማድረስ የሚችሉ በድኖች አሉን። የሩሲያ ወታደሮች ቁጥርም እየጨመረ ነው" ብሏል።
ኮስታያንታያኒቪካ ከተማ በበጋ ወቅት ለዩክሬን ጦር እንደ መጠለያ ያገለግላል።
የዩክሬን ድሮኖች ማንኛውንም እንቅስቃሴ ሲመለከቱ እርምጃ የሚወስዱበት ቀጣና መሆኑ ተገልጿል።
የሩሲያ ድሮኖች የዩክሬን ድሮን ማስወንጨፊያ ማዕከሎችን ዒላማ በማድግ ጥቃት ያደርሳሉ።
የዩክሬን የድሮን አብራሪ ለቢቢሲ እንደገለጸው የሩሲያ እግረኛ ጦር ላይ አነጣጥረው ጥቃት የሚፈጽሙ ሲሆን የሞስኮ ኃይሎች ግን "ብዙ ሮኬቶች" ይተኩሳሉ።
የሩሲያ ጦር እንደ ፖክሮቫስክ ያሉ ቁልፍ ከተሞችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተጠቀመበትን መንገድ በኮስታያንታያኒቪካ ከተማም የሚደግም ይሆናል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ በከተማዋ ምዕራባዊ ክፍል ያሉ መንደሮችን መቆጣጠሩን አስታውቋል።
እንደዚህ ያሉ መግለጫዎችን በማውጣት ዩክሬን በሞስኮ ነዳጅ ማምረቻዎች ላይ እያደረሰች ያለውን ጥቃት ለመሸፈንም ይሞክራል።