ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ሥልጣን እንዲለቁ ጫና የበረታባቸው የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር የፖለቲካ መፃኢ ዕድላቸውን እያጤኑ ነው
የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር የሥራ መልቀቂያቸውን እንዲያስገቡ ጫና ውስጥ በገቡበት ወቅት የፖለቲካ እጣ ፈንታቸውን እያሰቡበት ነው።
ባለፈው ሳምንት አንዲ ቡርንሀም በግሬተር ማንችስተር ምርጫ ማሸነፋቸው የሌበሪ ፓርቲ መሪ በመሆን ስታርመርን ለመገዳደር አስችሏቸዋል።
ይህንም ተከትሎ የስታርመር የካቢኔ አጋራቸው ፒተር ካይል ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የፖለቲካ ገሀዱን" እያጤኑ ነው ብለዋል።
የምርጫ ውጤቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሚንስትሮቻቸው ለአንዲ ቡርንሀም መንገዱን እንዲያስተካክሉ አዲስ የጫና ማዕበል ገጥሟቸዋል።
ከዚህ ባሻገር የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጫና የበረታባቸው ኪር ስታርመር "ከጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ይለቃሉ" በማለት በኃላፊነት የነበራቸውን ቆይታ ተችተዋል።
ዶናልድ ትራምፕ በማኅበራዊ የትስስር ገፅ ልጥፋቸው ሰር ኪር በኢሚግሬሽን እና የኃይል ፖሊሲ ዘርፍ "በከባዱ ወድቀዋል" ብለዋል።
"መልካሙን ሁሉ እመኝላቸዋለሁ" ሲሉ አክለዋል።
ሁለቱ መሪዎች ባለፈው ሳምንት በተደረገው የቡድን ሰባት ጉባኤ በፈረንሳይ የተገናኙ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ስታርመር በሳምንቱ መገባደጃ ቀናት ከፕሬዝዳንቱ ጋር እንዳልተነጋገሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የአንዲ ቡርንሀምን ድል ተከትሎ ኪር ስታርመር የመሪነት ወንበራቸውን የሚገዳደሯቸውን ፊት ለፊት እንደሚፋለሙ በድጋሚ ገልፀዋል። ይህም ማለት ለውድድሩ ሌበር ፓርቲ እና ግንኙነት ያላቸው የሥራ ማኅበራት ደጋፊዎች የፓርቲው እጣ ፈንታ ላይ መወሰን አለባቸው።
ይሁን እንጂ የንግድ ሚኒስትር የሆኑት ፒተር ካይል ለቢቢሲ ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የዛሬው የፖለቲካ እውነት ከባለፈው ሳምንት እና ከዚህ ሳምንት በፊት ከነበረው በደንብ ለማሰብ ጊዜ እየወሰዱ ነው" ብለዋል።
ባለፈው አርብ ከስታርመር ጋር መነጋገራቸውን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ስለ ሌበር ፓርቲ እጣ ፈንታ "ዛሬ የሚወስኑት ሁሉም ውሳኔ" ለአገሪቱ የተሻለ ጥቅምን የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል።
ካይል አክለውም ሰር ኪርን የፓርቲ መሪነት የሚገዳደር "ምንም ሂደት የለም" እና "ከኋላ ገፊ ኃይል የለም" ብለው ራሳቸውን እንደማያሞኙ ተናግረዋል።
መሪን ለመቀየር ይፋዊ ሂደትን መጠቀም "ለየትኛውም አማራጭ የተሻለ" ቢሆንም፤ የመንግሥት ሥልጣን እና ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳዮችን ማመዛዘን አለበት ብለዋል።
እ.አ.አ በ2020 ኪር ስታርመርን የሌበር ፓርቲ መሪ ለማድረግ የነበረው ውድድር ስድስት ሳምንት የወሰደ ነው። ይህ ሲሆን አንዳንድ የሌበት የፓርላማ አባላት የሀሳብ ልዩነት ወደ መሪዎች ለውጥ ካመራ የፓርቲውን ተስፋ ሊጎዳ ይችላል የሚል ስጋታቸውን ገልፀዋል።
ጫናው በገበያ እና በቁልፍ የመንግሥት ውሳኔዎች ላይ መዘግየትን በማስከተል አላስፈላጊ አለመረጋጋትን ሊፈጥር ይችላል የሚሉ ስጋቶችም ከፍ ብለዋል።
አንዲ ቡርንሀም ከሪፎርም ዩኬ የገጠማቸውን ብርቱ ፉክክር ተቋቁመው የለበር ፓርቲን አብላጫ ድምፅ ከፍ አድርገዋል። ይህም በቅርብ ፓርቲው ያገጠመውን ሽንፈት ያከመ ነው።
ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሀይዲ አሌክሳንደር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይቬት ኩፐር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣናቸውን አስረክበው እንዲለቁ የጊዜ ሰሌዳ እንዲነድፉ ጠይቀዋል።
ባለፈው ወር በተካሄደው ምርጫ ሌበር ፓርቲ ሽንፈት ከገጠመው በኋላ የአገር ውስጥ ሚኒስትር ሰባና መሐመድ እና የኢነርጂ ሚኒስትር ኤድ ሚሊባንድ በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲለቁ ጠይቀዋል።
በርካታ የሌበር ፓርቲ የምክር ቤት አባላትም ኪር ስታርመር መልቀቂያ እንዲያስገቡ ወይንም የመውጫ የጊዜ ሰሌዳ እንዲያወጡ በይፋ ወትውተዋል።
አንዲ ቡርንሀም ሰኞ ወደ ዌስትሚኒስተር አቅንተው የምክር ቤት ወንበራቸውን በይፋ ይይዛሉ።
የቡርንሀም አጋሮች ስታርመር በሳምንቱ መገባደጃ ቀናት ጊዜ ወስደው እንዲያስቡ እና የካቢኔ ሚኒስትሮቻቸውን፣ የምክር ቤት አባላትን እና ቤተሰቦቻቸውን እንዲያዳምጡ ጠይቀዋል።
ከእነዚህ ደጋፊዎች ውስጥ የሌበር ፓርቲ የምክር ቤት አባል የሆኑት ሔለን ሄይስ አንዷ ናቸው።
"በማርከርፊልድ ባለፈው ሳምንት ያየነው ድል በእውነቱ እጅግ ልዩ ነው" ብለዋል ለቢቢሲ ሬዲዮ።
ውድድር ወይስ ሹመት ተብለው የተጠየቁት የምክር ቤት አባሏ ምንም ምርጫ እንደሌላቸው ተናግረዋል።
"አንዲ ለአገሪቱ በሚያቀርቡት ነገር መተማመን አላቸው፤ እህም በማርከርፊልድ ባየነው ውድድር መሠረት ነው። ምርጫ ቢኖር በጣም እንደሚሳካለት አስባለሁ" ብለዋል።
"ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተወዳጅነታቸው በጣም አሽቆልቁሏል፤ ለውጥ ማድረግ አለብን።"
በጋዜጣዎች የፊት ገፅ ላይ ለውጥ በቅርቡ ይመጣል የሚል አርዕስተ ዜና እየተጠበቀ ነው። ኪር ስታርመር የመልቀቂያ የጊዜ ሰሌላ ለማውጣት ተዘጋጅተዋል የሚሉ ዘገባዎች እየወጡ ነው።
ለአንዲ ቡርንሀም ተፎካካሪ ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው የሚጠበቁት የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዌስ ስተሪቲንግ ከዚህ ቀደም የትኛውም ውድድር ላይ እንደሚሳተፉ ተናግረዋል። ፓርቲው በቀጣይ መስመሩ ላይ "በሀሳብ ውጊያ" ውስጥ ማለፍ አለበት ሲሉ ይከራከራሉ።
ከግንቦቱ ምርጫ በኋላ ከለቀቁ አራት ሚኒስትሮች ውስጥ አንዱ የሆኑት ጀሱ ፊልፒስ "የመንገዱ መጨረሻ ላይ እንደደረሰን ይሰማኛል" ብለዋል።
የስተሪቲንግ የቅርብ አጋር አንደሆኑ የሚታመኑት የቀድሞዋ ሚኒስትር አሁናዊ ቀውሱ በሙሉ ለሙሉ ውድድር ባይጠናቀቅ እንኳ "ቀጣዩ ምንድን ነው" የሚለው ጥያቄ ፓርቲው ይመልሳል ብለው ተስፋ አድርገዋል።
"ዝም ብለህ መጥተህ [ሥልጣን] መያዝ አትችልም" ብለዋል። "ቢያንስ ለሌበር ፓርቲ ፓርላማ መጥተህ ሀሳቦችህን ማቅረብ አለብህ" በመላት አክለው ተናግረዋል።
በሜከርፊልድ የአንድ ወር የምርጫ ዘመቻ አንዲ ቡርንሀም የገቢ ግብር፣ ተጨማሩ እሴት ታክስ ወይም ብሔራዊ መድኅንን ላለመጨመር ቃል ገብተዋል።
በአገልግሎቶች ላይ "ማኅበረሰባዊ ጠንካራ ቁጥጥር" እንዲኖር ፍላጎታቸውን የገለፁት አንዲ ቡርንሀም፤ የውርስ ታክስ በአዲስ ሕግ ለመተካት የገቡትን ቃል ደግመዋል።
ይሁን እንጂ የመከላከያ ወጪን ጨምሮ ሀሳቦቻቸውን በሌሎች የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ማሳየት ይኖርባቸዋል።
ከዚህ ቀደም በኪር ስታርመር ስር ትይዩ ሚኒስትር ሆነው የሰሩት የሌበር የምክር ቤት አባል ቶቢ ፐርኪንስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲወርዱ እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። ለዚህም ምክንያታቸው "አገሪቱ በ10 ዓመታት ውስጥ ሰባት ጠቅላይ ሚኒስትር" ይኖራታል የሚል ነው።
ሰር ኪር "ተጨማሪ ጊዜ ይገባቸዋል" እና መንግሥት "እየወደቀ ነው" ብለው እንደማያምኑ ስኬቶችን በማንሳት ተናግረዋል።