የመጀመሪያው ቀን ድርድር ሲጠናቀቅ፤ በቀጣይ ቀናት የቴክኒክ ውይይት እንደሚቀጥል ተገለጸ
የኢራን እና አሜሪካ የመጀመሪያ ቀን ድርድር የተገባደደ ሲሆን፤ ሳምንቱን በሙሉ በስዊትዘርላንድ የቴክኒክ ጉዳዮች ውይይት እንደሚቀጥል ተገልጿል።
አደራዳሪዎቹ ኳታር እና ፓኪስታን “የኢስላማባድ የመግባቢያ ሰነድ ማዕቀፍን በተመለከተ የመጀመሪያው ዙር ንግግር ተገባዷል” ብለዋል።
በተቀረው የሳምንቱ ቀናት የቴክኒክ ውይይት እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።
አሜሪካ እና ኢራን በቀጣይ 60 ቀናት ውስጥ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ላይ መስማማታቸው ተመልክቷል።
በሊባኖስ ጦርነቱን ማስቆም የሚቻልበት መንገድ መዘርጋት ላይም መግባባት ላይ መደረሱን አሸማጋዮቹ አስታውቀዋል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ድርድሩን “ትልቅ ለውጥ” የታየበት እንደሆነ በኤክስ ገጻቸው ተናግረዋል።
“በነዳጅ እና በፔትሮኬሚካል የወጪ ንግድ ላይ የተጣለው እገዳተነስቷል” ሲሉም አክለዋል።