ፖምፔዎ ቫይረሱ ከቻይና ቤተ ሙከራ ስለመምጣቱ 'በርካታ ማስረጃዎች' አሉን አሉ
የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ክትባትም ሆነ ለማከም የሚውል መድኃኒት እስካሁን አልተገኘም። ነገር ግን በየአገራቱ ያሉ ባለሙያዎች ሌት ተቀን ጥረት እያደረጉ መሆናቸው እየተነገረ ነው። መቼ ውጤት ላይ ሊደርሱ እንደሚችሉ ግን በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም። ስለዚህ በእጃችን ላይ ያሉትን የመከላከያ መንገዶች በመጠቀም እራስን ከበሽታው መጠበቅ ብቸኛው መንገድ ነው። ለዚህ ደግሞ አካላዊ ርቀታችንን እንጠብቅ፤ እጃችንን በተደጋጋሚ በሳሙናና በውሃ እንታጠብ። ስለወረርሽኙ የሚቀርቡ የቀጥታ ዘገባዎችንና መረጃዎችን ከዚህ ገጽ ይከታተሉ።
የቀጥታ ሽፋን
ትራምፕ ቻይና በምርጫው እንድሸነፍ ትፈልጋለች አሉ
የመን የመጀመሪያውን የኮቪድ-19 ሞት መዘገበች

የፎቶው ባለመብት, Reuters
በየመን በኮቪድ-19 የተያዙ ሁለት ሰዎች መሞታቸው ተነገረ። ሁለቱ ሟቾች ወንድማማቾች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በደቡባዊ ኤደን ሆስፒታል ውስት መሞታቸው ተሰምቷል።
መንግሥት በስፍራው አምስት ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው መገኘታቸውን ገልጿል።
ከአምስት ዓመት በላይ የተካሄደው የእርስ በእርስ ጦርነት የየመንን የጤና ስርዓት ያደቀቀው ሲሆን የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመዋጋት ምንም ዝግጅት አለመደረጉም ተገልጿል።
በየመን እንደ ኮሌራ፣ ወባ እና ደንጌ ፊቨር የመሳሰሉ በሽታዎች በሰፊው ተሰራጭተው የሚገኙ ሲሆን ካሉት ሆስፒታሎች ግማሽ ያህሉ ብቻ በስራ ላይ ናቸው።
በየመን ሚሊዮኖች ከዓለም አቀፍ መንግሥታት በሚሰጣቸው የምግብ እርዳታ ህይወታቸውን ይገፋሉ።
የተባበሩት መንግሥታት ቫይረሱ ምንም ዓይነት ምርመራ ሳይደረግ ሊስፋፋ ይችላል ሲል ያለውን ስጋት ገልጾ ነበር።
ቶም ሃንክስ ከኮቪድ-19 ካገገመ በኋላ ፕላዝማውን ለገሰ
ቶም ሃንክስ በኮቪድ-19 ከተያዙ የሆሊውድ ስመጥር ሰዎች መካከል ቀዳሚው ነው። እርሱና ባለቤቱ አውስትራሊያ ለስራ በሄዱበት ነው በቫይረሱ መያዛቸውን ያወቁት።
አሁን ደግሞ በኮሮናቫይረስ ላይ ለሚደረገው ምርምር እንዲረዳ በሚል ፕላዝማውን ለግሷል።
ፕላዝማ የደም ፈሳሹ ክፍል ሲሆን በኮቪድ-19 ተይዘው ያገገሙ ሰዎች ያመረቱት የመከላከል አቅም (አንቲቦዲስ) በዚያ ውስጥ ይገኛል።
ተመራማሪዎች እርሱን በመውሰድ በቫይረሱ በጽኑ ለታመሙ ሰዎች በመስጠት እንዲያገግሙ ማድረግ ይቻላል ተብሏል።
የ X ይዘትን ይለፉትይዘቱን X ይፈቅዳሉ?ማሳሰቢያ: በሌሎች ገጾች ላይ ላሉ ይዘቶች ቢቢሲ ኃላፊነት አይወስድም።ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ
ባለፉት 24 ሰዓታት በደቡብ ኮሪያ አንድም ሰው በኮቪድ-19 አልተያዘም

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
በአንድ ወቅት በአለማችን ክፉኛ በኮሮናቫይረስ ከተጠቁ አገራት መካከል አንዷ ነበረች። አሁን ግን ባለፉት 24 ሰዓታት በአገር ውስጥ አንድም ሰው በቫይረሱ አለመያዙ ተመዝግቧል።
በደቡብ ኮሪያ ውስጥ አንድም ሰው በቫይረሱ አይያዝ እንጂ አራት ሰዎች ከሌላ አገር መጥተው በአውሮፕላን ማረፊያ ሲመረመሩ ቫይረሱ እንዳለባቸው መረጋገጡ ተገልጿል።
ይህም በደቡብ ኮሪያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 10ሺህ 765 አድርሶታል።
ለደቡብ ኮሪያ በሽታ መቆጣጠርና መከላከል ይህ በሁለት ወራት ውስጥ ከተመዘገበው ዝቅተኛ ቁጥር ሲሆን ከዚህ ቀደም በአንድ ቀን በመቶዎች ተመዝግቦ ያውቃል ተብሏል።
ደቡብ ኮሪያ በየእለቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው በመመርመር እና የታመሙትንና ንክኪ ያላቸውን በመለየት ውጤታማ ስራ መስራቷ ይነገራል።
ሰዎች እጃቸውን የማይታጠቡበትን ሥነ ልቦናዊ ምክንያት ያውቃሉ?
አሜሪካ በኮሮናቫይረስ ሕክምና ላይ የምታደርገው ምርምር ተስፋ ሰጪ ነው ተባለ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
በኮሮናቫይረስ ላይ ከሚደረጉ የተለያዩ ሙከራዎች መካከል መልካም ዜና የተሰማው ከወደ አሜሪካ ነው።
አሜሪካውያን ተመራማሪዎች ሬምዴስቪር (Remdesivir) በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ላይ የሚታየውን ምልክት ከ15 ወደ 11 ዝቅ ያደርጋል ብለዋል።
ሬምዴስቪር ክትባት አይደለም በኮሮናቫይረስ የተያዙትንም ወዲያው አይፈውስም።
ይህ ተመራማሪዎቹ የደረሱበት እርግጥ ሆኖ የሚሰራ ከሆነ በሆስፒታሎች ላይ ያለውን ጫና የሚቀንስ ሲሆን በርካታ ሕይወትም ይታደጋል ተብሏል።
ምናልባትም የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች ቀደም ብለው የሚነሱበት እድልን ሊፈጥር ይችላል ሲሉ ተስፋቸውን ተናግረዋል።
ይህ መድኃኒት ከዚህ ቀደም ይውል የነበረው በኢቦላ የተያዘን ሰው ለማከም ነበር። መድኃኒቱ ከኢቦላ በተጨማሪ ሌሎች የኮሮናቫይረስ አይነቶችን ለማከም በእንስሳት ላይ ተሞክሮ አመርቂ ውጤት አሳይቷል።
በዚህም ኮቪድ-19ን ሊያክም ይችላል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል። ይህ መድኃኒት የዓለም ጤና ድርጅት በ'ሶሊዳሪቲ ትሪያል' ማዕቀፍ ውስጥ ከያዛቸው አራት መድኃኒቶች መካከል አንዱ ይህ ነው። የዚህ መድኃኒት አምራች የሆነው ጊሊድ የተሰኘው ተቋምም በመድኃኒቱ ላይ ምርምር እያካሄደ ይገኛል።
ነገር ግን ይህ የምርምር ውጤት ከቻይና ተመራማሪዎች በኩል ሌላ ሃሳብ ተሰንዝሮበታል።
ቻይናውያኑ ተመራማሪዎች ላንሴት ሜዲካል ጆርናል ላይ ባሳተሙት የምርምር ስራቸው ሬምዴስቪር የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ውጤታማ አይደለም የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል።
የቢቢሲ ወዳጆች እንደምን አደራችሁ!
ቢቢሲ አማርኛ ከኮሮናቫይረስ ጋር የተያያዙ የቀጥታ ዘገባዎቹን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ማቅረብ ይጀምራል።
በዓለም ዙሪያ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ከተከሰቱ ዜናዎች አበይቶቹን እየመራረጥን ወደ እናንተ እናቀርባለን።
በመላው ዓለም 3,190,743 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የጆንስ ሆፕኪንስ አሁናዊ መረጃ ሲያሳይ ከእነዚህም መካከል 227,368 ያህሉ ሞተዋል ይላል።
የአሜሪካ የጤና ባለሙያዎች የኮሮናቫይረስ ሕሙማንን ለማከም እየሞከሩት ያለው መድሃኒት በጎ ውጤት አስገኝቶልናል ብለዋል።
መድሃኒቱ ሬምዴስቪር ሲሰኝ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ምልክት ባሳዩ የተለያዩ ሰዎች ላይ መሞከሩን ተናግረዋል።
በአሁኑ ሰዓት ግን ቫይረሱን ለመከላከል ያለን ብቸኛ አማራጭ፣ በሕክምና ባለሙያዎች የሚሰጡ ምክሮችን ተግባራዊ ማድረግና የራሳችንንም የሌሎችንም ጤንነት መጠበቅ ነው!
መልካም ውሎ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር!

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
