ፖምፔዎ ቫይረሱ ከቻይና ቤተ ሙከራ ስለመምጣቱ 'በርካታ ማስረጃዎች' አሉን አሉ
የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ክትባትም ሆነ ለማከም የሚውል መድኃኒት እስካሁን አልተገኘም። ነገር ግን በየአገራቱ ያሉ ባለሙያዎች ሌት ተቀን ጥረት እያደረጉ መሆናቸው እየተነገረ ነው። መቼ ውጤት ላይ ሊደርሱ እንደሚችሉ ግን በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም። ስለዚህ በእጃችን ላይ ያሉትን የመከላከያ መንገዶች በመጠቀም እራስን ከበሽታው መጠበቅ ብቸኛው መንገድ ነው። ለዚህ ደግሞ አካላዊ ርቀታችንን እንጠብቅ፤ እጃችንን በተደጋጋሚ በሳሙናና በውሃ እንታጠብ። ስለወረርሽኙ የሚቀርቡ የቀጥታ ዘገባዎችንና መረጃዎችን ከዚህ ገጽ ይከታተሉ።
የቀጥታ ሽፋን
የቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ሴቶች ከለላ የሚሰጠው ምክር ቤት
በደቡብ አፍሪካ እስከ ሰባት ሚሊዮን ሰዎች ሥራ አጥ ይሆናሉ ተብሎ ተሰግቷል

የፎቶው ባለመብት, REUTERS
የደቡብ አፍሪካ ግምጃ ቤት ከሦስት እስከ ሰባት ሚሊዮን ሰዎች ሥራ አጥ ሊሆኑ ይችላሉ አለ።
የገንዘብ ሚንስትሩ ቲቶ ምቦውኒ፤ “የእንቅስቃሴ ገደቡ የምጣኔ ሀብት እድገቱን አቁሞታል” ብለዋል።
በአገሪቱ ብሔራዊው የእንቅስቃሴ ገደብ እየላላ ነው። አምራቾችና በግንባታ የተሰማሩትን ጨምሮ ሚሊዮኖች ወደ ሥራ ገበታቸው ይመለሳሉ ተብሎም ይጠበቃል።
ምግብ ቤቶች ለደንበኞቻቸው ምግብ የማድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ ቢፈቀድም፤ የሰዓት ገደብ አለው።
ሚንስትሩ ለምክር ቤት አባላት ባደረጉት ንግግር፤ ውጤታማ ያልሆኑ የመንግሥት ተቋሞች እንደሚሸጡ ቢጠቁሙም የትኞቹን እንደሆነ በግልጽ አልተናገሩም።
ችግር የተጋረጠበት ‘ሳውዝ አፍሪካ ኤርዌይስ’ ባለ ሀብቶችን ስለማይስብ ሙሉ በሙሉ ይዘጋ ማለታቸው ይታወሳል።
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕጻናት ክትባት ላያገኙ እንደሚችሉ ተገለጸ

የፎቶው ባለመብት, Unicef
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕጻናት ሕይወታቸውን የሚታደጉ ክትባቶችን ላያገኙ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግሥታት አስጠነቀቀ።
የኮሮናቫይረስ ስርጭት ክትባቶች እንዳይጓጓዙ እንቅፋት ሆኗል።
በወረርሽኙ ሳቢያ በረራዎች በመታገዳቸው፤ በርካታ አገሮች እጅግ አስፈላጊ ክትባቶች ላያገኙም ይችላሉ።
የተባበሩት መንግሥታት የታዳጊዎች ክንፍ ዩኒሴፍ፤ መንግሥታት እንዲሁም የግሉ ዘርፍም መፍትሔ እንዲፈልጉ አሳስቧል።
የኩፍኝ፣ ፖሊዮ እና ቲታነስ ክትባት በየዓመቱ የሦስት ሚሊዮን ሕጻናትን ሕይወት እንደሚታደግ ድርጅቱ አሳውቋል።
ዩኒሴፍ እንደሚለው፤ ለኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት የሚደረገው ርብርብ ሌሎች ክትባቶች እንዲዘነጉ ምክንያት ሆኗል።
የድርጅቱ ቃል አቀባይ ማክሲን መርካዶ፤ “የክትባት ዝውውር እንዲኖር ዩኒሴፍ ትብብር ይጠይቃል፤ ይህም በአንዳንድ አገሮች የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብም ይመለከታል” ብለዋል።
የኬንያ ፕሬዚደንት ለዩኬ የጤና ሠራተኞች አበባ መላኩን ተከትሎ ለቀረበው ትችት ምላሽ ሰጡ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, ኡሁሩ "ወዳጆች በክፉ ቀን ሊተሳሰቡ ይገባልም" ብለዋል የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ አገሪቷ ለዩናይትድ ኪንግደም የብሔራዊ ጤና አገልግሎት ሰራተኞች አበባ መላኳን ተከትሎ ለቀረበው ትችት ምላሽ ሰጡ፡፡
ፕሬዚደንቱ በሰጡት ምላሽ ዩኬ ለኬንያ አበባ ትልቅ ገበያ በመሆኗ የተደረገ ስልታዊ ውሳኔ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
"ወዳጆች በክፉ ቀን ሊተሳሰቡ ይገባልም" ብለዋል፡፡
ከኮሮናቫይረስም በኋላ ሕይወት አለ ያሉት ፕሬዚደንቱ፤ እንግሊዛዊ የጤና ሰራተኞች አበባ ለመግዛት ሲሄዱ የኬንያ አበቦችን ምርጫቸው ያደርጋሉ፡፡ ሰራተኞቹ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ባደጉት ጥረትም እውቅና ያገኙ ናቸው ሲሉ አክለዋል፡፡
ነገር ግን ፕሬዚደንቱ ለብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ባስታላለፉት ንግግር ጥቂት ኬንያዊያን በዚህ ወረርሽኝ ወቅት ወደ ዩኬ አበባ መላክ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም ሲሉ በኦንላይን መንግስትን ሲወቅሱ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
በርካቶች በትዊትር ገጻቸው ላይ "ፕሬዚደንታችን በለይቶ ማቆያ ውስጥ አልጋ እንኳን ሳይሟላ ወደ ዩኬ አበባ ላኩ"
"የኬንያ ነርሶች የበሽታ መከላከያ የህክምና ቁሳቁስ እጥረት ሳቢያ አድማ ለመምታት እያሰቡ ባሉበት ወቅት ለአውሮፓ ነርሶች አበባ ተላከ" ሲሉ ወቅሰዋቸዋል፡፡
የ X ይዘትን ይለፉትይዘቱን X ይፈቅዳሉ?ማሳሰቢያ: በሌሎች ገጾች ላይ ላሉ ይዘቶች ቢቢሲ ኃላፊነት አይወስድም።ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ
በሕንድ ፖለቲከኛው መጠጥ ቤቶች ይከፈቱ አሉ

የፎቶው ባለመብት, WHO
የዓለም ጤና ድርጅት አልኮል መጠጣት አቁሙ ቢልም፤ የሕንድ ፖለቲከኛ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት መጠጥ ቤቶች ይከፈቱ ብለዋል።
“በአልኮል እጅ መታጠብ ኮሮናቫይረስን የሚከላከል ከሆነ አልኮል መጠጣት ቫይረሱን ከጉሮሮ ያስወግዳል ማለት ነው” ሲሉ ፖለቲከኛው ባሀት ኢንግ ተደምጠዋል።
ሕንድ የእንቅስቃሴ ገደብ ብታውጅም፤ መጠጥ ቤቶች እንዲከፈቱ የሚጠይቅ ደብዳቤ ፖለቲከኛው ለከተማ መስተዳድር ጽፈዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት መጠጥ ከኮሮናቫይረስ እንደማይከላከል፣ እንዲያውም ለበሽታው ተጋላጭ እንደሚያደርግ አስጠንቅቋል።
ቢያንስ 60 በመቶ አልኮል ያላቸው የንጽህና መጠበቂያዎች እጅን ለማፅዳት እንዲውሉ ይመከራል።
ሩዋንዳ የእንቅስቃሴ ገደቡን በከፊል ልታነሳ ነው

የፎቶው ባለመብት, AFP
የምስሉ መግለጫ, ሩዋንዳ ከግዛት ግዛት የሚደረግ ጉዞን ከልክላለች የሩዋንዳ መንግሥት የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት ከስድስት ሳምንት በፊት ጥሎት የነበረውን ጥብቅ ገደቦች በከፊል ሊያነሳ እንደሆነ አስታወቀ፡፡
ክልከላውን ለማንሳት የወጡትን ዝርዝር እቅዶችንም ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም መሠረት ተጥለው የነበሩት ገደቦች ከሦስት ቀናት በኋላ የሚነሱ ሲሆን፤ የተወሰኑ ገደቦች ግን ይቆያሉ ተብሏል፡፡
ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 11 ሰዓት ድረስ የሰዓት እላፊም ተጥሏል፡፡
ሁሉም ትምህርት ቤቶች እስከ መስከረም ድረስ ዝግ ሆነው ይቆያሉ፡፡ በተጨማሪም ከካርጎ (የጭነት ትራንስፖርት) እንዲሁም ወደ አገር ውስጥ የሚመለሱ የሩዋንዳ ዜጎችና ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ካላቸው በስተቀር ድንበር ማቋረጥ የተከለከለ ነው፡፡
የገበያ ቦታዎች በከፊል የሚከፈቱ ሲሆን ሆቴሎችና ምግብ ቤቶች ምሽት 1 ሰዓት ላይ ይዘጋሉ፡፡
የስፖርት መስሪያ ቦታዎች፣ ጂም፣ ባር እንዲሁም የእምነት ቦታዎች ተዘግተው ይቆያሉ፡፡ ነገር ግን ግለሰቦች ክፍት በሆኑ ቦታዎች ለይ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል፡፡
መንገደኞች በህዝብ ትራንስፖርት ውስጥ አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ ያለባቸው ሲሆን ከግዛት ግዛት የሚደረጉ ጉዞዎች ግን የተከለከሉ ናቸው፡፡
በሩዋንዳ እስካሁን 243 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 84ቱ የተመዘገቡት ባለፉት ሰባት ቀናት ውስጥ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር የጨመረው ከኬንያና ታንዛኒያ ወደ ሩዋንዳ እንዲገቡ ተፈቅዶላቸው በነበሩት የእቃ ማጓጓዣ መኪና አሽከርካሪዎች ምክንያት እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በቤጂንግ ሕይወት ወደ ቀድሞ ገጽታው እየተመለሰ ነው

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
በኮሮናቫይረስ ምክንያት ቀንሶ የነበረው የቤጂንግ የትራፊክ መጨናነቅ ወደ ቀድሞ ሁኔታው እየተመለሰ ነው።
ቻይና እንቅስቃሴ ላይ ጥላ የነበረውን ገደብ ማላላቷን ተከትሎ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ወደ 117 ሚሊዮን ጉዞዎች ይካሄዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የትራንስፖርት ሚንስትር አስታውቋል።
ሆኖም ግን ሰዎች ምን ያህል ደህንነታቸውን ጠብቀው የረዥም ርቀት ጉዞ ያደርጋሉ የሚለው አጠያያቂ ሆኗል።
‘ፎርቢድን ሲቲ’ የተባለው የቱሪስት መዳረሻ ኮሮናቫይረስ ከተቀሰቀሰ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ ክፍት ሆኗል። ጎብኚዎች ውጪ ከሆኑ የአፍና አፍንጫ ጭንብል ማድረግም አይጠበቅባቸውም።
ከተለያዩ ግዛቶች ወደ ቤጂንግ የሚገቡ ሰዎች ለይቶ ማቆያ እንደማይገቡም ተገልጿል።
'ጥቁር እንግሊዛውያን በሶስት እጥፍ ሞተዋል'
እንግሊዝና ዌልስ ውስጥ የሚኖሩ አፍሪካዊ ደም ያላቸው ጥቁር ብሪታኒያውያን ከነጮቹ ሶስት እጥፍ በበለጠ እየሞቱ እንደሆነ አንድ ጥናት ጠቆመ።
ፊስካል ስተዲስ የተሰኘው ተቋም እንደጠቆመው ጥቁር ብሪታኒያውያን በኮቪድ-19 ምክንያት እጅግ ተጎድተዋል።
ለዚህም ዋነኛው ምክንያት ጥቁር ብሪታኒያውያን የሚኖሩበት አካባቢ ደረጃው ዝቅ ያለ መሆኑና ተጨናንቀው የሚኖሩ በመሆኑ ነው ብሏል ጥናቱ።
ቢሆንም ይላል ጥናቱ፤ አብዛኛዎቹ ወጣቶች በመሆናቸው የማገገም አቅማቸው ላቅ ያለ ነው።
ቢቢሲ በሠራው ጥናት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸውን 135 የሕክምና ባለሙያዎቸች መካከል 84ቱ ከአናሳ ጎሳ ናቸው።
ትራምፕ የኮሮናቫይረስ ከቻይና ቤተ ሙከራ ስለመውጣቱ መረጃ አለኝ አሉ
'ጌታ ይጠብቃችኋል፤ ሥራችሁን ቀጥሉ' የታንዛንያው ፕሬዝዳንት

የፎቶው ባለመብት, AFP
የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የላብ-አደሮች ቀንን ምክንያት አድርገው ባስተላለፉት መልዕክት 'ሥራችሁን ሥሩ፤ ለሌላው ፈጣሪ አለላችሁ' ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ፤ ኮሮናቫይረስ ታንዛንያውያንን ከማገልገል እንደማያግዳቸውም ተናግረው የሃገራቸው ዜጎች የጤና ባለሙያዎች የሚሏቸውን እንዲሰሙ አሳስበዋል።
የላብ-አደሮች ቀንን ለመዘከር ሰዎች መሰብሰብ አለመቻላቸው ቢያስቆጫቸውም ወዛደሮች እየሠሩት ያለውን ሥራ አንደሚያደንቁ ተናግረዋል።
የኮቪድ-19 መግለጫ በየቀኑ እየሰጠች አይደለም ተብላ ስትወቀስ የነበረችው ታንዛኒያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 480 መድረሱን አሳውቃለች።
ምንም እንኳ የዓለም ጤና ድርጅት ማሕበራዊ መራራቅ ይጠበቅ ቢልም ማጉፉሊ ግን ሰዎች ወደ ቤተ-እምነቶች ሄደው ፀሎት እንዲያደርሱ ሲያሳስቡ ነበር፤ ቫይረሱ በክርስቶስ ሰውነት አይዘልቅም በማለት።
በምዕራብ ሐረርጌ ጉባ ኮሪቻ በኮቪድ-19 የተያዘው ግለሰብ ማን ነው?
በኢትዮጵያ ሁለት ወጣቶች በኮሮናቫይረስ ተያዙ
የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ በዕለታዊ የኮቪድ-19 መግለጫቸው እንዳስታወቁት ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው ምርመራ ሁለት ኢትዮጵያዊያን በቫይረሱ መያዛቸውን አሳውቀዋል።
በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር 912 ነው ተብሏል።
ከእነዚህም መካከል ሁለት የ20 እና 25 ዓመት ወንድ ኢትዮጵያዊያን በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 133 ደርሷል። 66 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን 3 ሰዎች ደግሞ መሞታቸው አይዘነጋም።
ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ለ18 ሺህ 754 ሰዎች ምርመራ ያደረገች ሲሆን 62 ሰዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ ናቸው።
የ X ይዘትን ይለፉትይዘቱን X ይፈቅዳሉ?ማሳሰቢያ: በሌሎች ገጾች ላይ ላሉ ይዘቶች ቢቢሲ ኃላፊነት አይወስድም።ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ
ኮሮናቫይረስ ኮሞሮስ ገባ
ኮሞሮስ የመጀመሪያውን የኮሮናቫይረስ ሕመምተኛ ማግኘቷን አስታወቀች።
ፕሬዝደንት አዛሊ አሶማኒ እንዳሉት የመጀመሪያው ኮሞሮሳዊ ታማሚ የፈረንሳይና ኮሞሮስ ዜግነት ካለው ሰው ጋር ግንኙነት ነበረው ሰው መሆኑን አሳውቀዋል።
ፕሬዝደንቱ ትላንት [ሐሙስ] በድረ-ገፃቸው በለጠፉት መልዕክት ኮሮናቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሃገራችን ገብቷል ብለዋል።
ታማሚው ወደ ኤል-ማዕሩፍ ሆስፒታል የተወሰደ ሲሆን ሳል፣ የጉሮሮ መከርከርና የትንፋሽ እጥረት ተስተውሎበታል ተብሏል። ግለሰቡ እየተሻለው ነው ያለሉት ሚኒስትሩ ከሰውዬው ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች እየታሰሱ እንደሆነ አስታውቀዋል።
ሰዎች በመተንፈሻ ችግር ምክንያት እየሞቱ የሚሉ ዜናዎች ባለፈው ሳምንት ቢሰሙም ፕሬዝደንቱ በሶስቱም ደሴቶች ኮሮና የሚባል ነገር የለም ብለው ነበር።
ኮሞሮስ ኮቪድ-19 ሃገሯ እንደገባ ያሳወቀች የመጨረሻዋ አፍሪካዊት ሃገር ነች። በሌላ በኩል ሌሶቶ ምንም ዓይነት የኮሮና ምልክት የለብኝም እያለች ነው።
መከላከያ ቁሳቁሶችን ከአንድ ጊዜ በላይ የሚጠቀሙት ኬንያውያን የህክምና ባለሙያዎች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
በርካታ የኬንያ የህክምና ባለሙያዎች አንዴ የተጠቀሙባቸውን እንደ ጓንት፣ ገዋን፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ያለ መሣሪያ (ፐርሰናል ፕሮቴክቲቭ ኤኪዩፕመንት) ዳግመኛ እንዲጠቀሙባቸው እየተገደዱ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ።
ጥናቱ የተሰራው በኬንያ ህግና ስነምግባር ጉዳዮች ኔትወርክ ሲሆን በርካታ የሕክምና ባለሙያዎች የመከላከያ ቁሳቁሶች እጥረት መኖሩን ተናግረዋል ብሏል።
በጥናቱ ላይ ከተጠየቁት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ባለሙያዎች የኮሮናቫይረስ ህሙማንን እንዴት መንከባከብ እንዳለባቸው ስልጠና መውሰዳቸውን ገልፀዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ማይክል ያኦ ለቢቢሲ እንዳሉት አገራት ለጤና ባለሙያዎች በየጊዜው ሕሙማንን እንዴት መንከባከብ እና ራሳቸውን መከላከል እንዳለባቸው ስልጠና መስጠት አለባቸው።
"ዋናው ጠቃሚ ነገር ደጋግሞ መለማመድ ነው። ካልተለማመዱ ስህተት መስራትና ራሳቸውንም ሆነ ቤተሰባቸውን ለአደጋ ማጋለጣቸው አይቀርም" ብለዋል ዶ/ር ያኦ።
ሲንጋፖር የውጭ ሃገር ሠራተኞችን መርከብ ላይ ማስፈር ጀመረች

የፎቶው ባለመብት, AFP
ሲንጋፖር ከኮሮናቫይረስ ያገገሙ የውጭ ሃጋር ሠራተኞችን ባህር ዳርቻ ባሉ በሁለት ትላልቅ መርከቦች ላይ ማሥፈር ጀምራለች።
መርከቦቹ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እንደሚደረግና ሠራተኞቹ ማሕበራዊ ርቀታቸውን እንዲጠብቁ እንደሚደረግ ታውቋል። ከዚያም አልፎ ሰዎች በቫይረሱ ቢያዙ በሚል በመርከቦቹ አቅራቢያ ለይቶ ማቆያዎች ይኖራሉ።
ሲንጋፖር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን አግኝታለች። አብዛኛዎቹ ደግሞ ከውጭ ሃገር የመጡ የቤት ሠራተኞች ናቸው። እነዚህ የውጭ አገር ዜጎች የሚኖሩበት አካባቢ የተጨናነቀና ማሕበራዊ ርቀትን መጠበቅ እጅግ አዳጋች ነው።
የሲንጋፖር ባለሥልጣናት ለሠራተኞቹ የሚሆን አዲስ የመኖሪያ ሠፈር ሊያዘጋጁ ነው ተብሏል።
ሲንጋፖር ውስጥ 300 ሺህ ያክል የውጭ ሃገራት ሠራተኞች አሉ። አብዛኛዎቹ ከደቡብ እስያ የመጡ ናቸው።
በአንድ ወቅት የኮሮናቫይረስን በመቆጣጠር ምስሌ የነበረችው ሲንጋፖር አሁን 16 ሺህ ያክል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች እንዳሏት አሳውቃለች።
የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀኃፊ የሃገራት አለመተባበር ኮቪድ-19 እንዲስፋፋ አድርጓል አሉ

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በሰጠው ምላሽ “መደናገጣቸውን” ተናገሩ።
በርካታ ሰዎች ሲሞቱ መመልከት እንዲሁም በምጣኔ ሀብት እና በማህበረሰብ ላይ ቫይረሱ ያለውን ከፍተኛ ጫና፣ በተለይ ደግሞ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ላይ መመልከት ያስደነግጣል ብለዋል።
“ነገር ግን አልተደነቅኩም” ያሉት ዋና ፀኃፊው ምክንያታቸውን ሲያስረዱም ዓለም በአንድ ላይ በመሆን ኮቪድ-19 መዋጋት አልቻለም ሲሉ ተናግረዋል።
እያንዳንዱ አገር በግሉ የራሱን ፖሊሲ ሲያራምድ፣ የተለያዩ አገራት የተለያዩ ስልቶችን እና መንገዶችን ሲከተሉ መስተዋሉን ይገልፃሉ።
ይህ ደግሞ ቫይረሱ እንዲስፋፋ እድል እንደሰጠው ጨምረው አስረድተዋል።
የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምላሽ ለመስጠት ህብረት እንደሚያስፈልገው ለቡድን ሃያ አገራት ምክረ ሃሳብ ማቅረባቸውን ጨምረው ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የዓለም ኃያላን አገራት ወደ አንድ ጠረጴዛ መምጣት ባለመቻላቸው የኮሮናቫይረስን በመዋጋት ረገድ የአመራር እጥረትና ክፍተት ታይቷል ያሉት ዋና ፀኃፊው የዓለም አንድ ክፍል ኮሮናን ለብቻው መመከት አይችልም፤ የተባበረ ጥረት ይጠይቃል ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።
የትራምፕ አስተዳደር ለዓለም ጤና ድርጅት የሚያደርገውን ድጋፍ ስለማቋረጡ ሲናገሩ ድርጅቱ በተቻለ መጠን በቂ ድጋፍ እንዲኖረው ማድረግ እንደሚገባ ገልፀው አሁን ባለው ሁኔታ በተለይ ላደጉ አገራት በሚሰጠው ድጋፍ የተነሳ በሌላ ተቋም መተካት አይቻልም ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም ታዳጊ አገራትን መደገፍ የመልካም ምግባር መገለጫ ሳይሆን የተሰላ ፍላጎትን የማስፈፅም ጉዳይ ነው ብለዋል።
የዓለም ገንዘብ ተቋም ለኢትዮጵያ የ411 ሚሊየን እርዳታ ለገሰ
የዓለም ገንዘብ ተቋም ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ትከላከልበት ዘንድ የ411 ሚሊየን ዶላር ልገሳ ማድረጉን አስታውቋል። አልፎም የዕዳ ቅነሳ ሊደርግላት እንደሆነ ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ድርጅቱ ልገሳው ያስፈለገው ሃገሪቱ በወረርሽኙ ምክንያት ያጋጠማትን የምጣኔ ሃብት ቀውስ እንድትወጣ ነው ብሏል።
ልገሳው በአንድ ጊዜ ክፍያ መቶ በመቶ የሚሰጥ ነው ሲል የድርጅቱ ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ አስታውቋል።
ድርጅቱ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ እንደ አስፈላጊነቱ እንደሚቀጥልና የፖሊሲ ድጋፍም እንደሚያደርግ አሳውቋል።
ከልገሳው በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ምስጋናቸው በትዊተር ሰሌዳቸው አኑረዋል።
የ X ይዘትን ይለፉትይዘቱን X ይፈቅዳሉ?ማሳሰቢያ: በሌሎች ገጾች ላይ ላሉ ይዘቶች ቢቢሲ ኃላፊነት አይወስድም።ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ
በኮሮናቫይረስ ዙሪያ የሚለቀቁ ሐሰተኛ መረጃዎችን እንዴት መለየት ይቻላል?
ተጫዋቾች ወደ ሜዳ መመለስ ፈርተዋል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የማንቸስትር ሲቲው አጥቂ ሰርጂዬ አጉዌሮ እግር ኳስ ተጫዋቾች ወደ ሜዳ መመለስ እንደፈሩ እየተናገረ ነው። ከወርሃ መጋቢት ጀምሮ የተቋረጠው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ በቅርብ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል። ሊጉ 92 ቀሪ ጨዋታዎች ይቀሩታል።
በሌላ የኳስ ዜና ፓሪስ ሴይንት ዠርሜይን የፈረንሳይ ሊግ 1 አሸናፊ መሆኑ ተረጋግጧል። የሊጉ አስተዳዳሪ በያዝነው የውድድር ዘመን ኳስ የሚባል ነገር የለም ብለዋል።
የጀርመን ቡንደስ ሊጋ ደግሞ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። የጣልያን ክለቦች ተጫዎቾች በየግላቸው እንዲሠልጥኑ ተፈቅዶላቸዋል።
