ፕሬዝዳንት ፑቲን ከዩክሬን ወረራ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኒውክሌር ልምምድን ተመለከቱ

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን

የፎቶው ባለመብት, KREMLIN

የምስሉ መግለጫ, ፕሬዝዳንት ፑቲን የኒውክሌር ልምምዱን በቪዲዮ ተመልክተዋል
ታትሟል

ስምንት ወራትን ባስቆጠረው የዩክሬን ወረራ ምክንያት ከምዕራባውያን ጋር ውጥረት ውስጥ የሚገኙት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው በየዓመቱ የምታካሄድን የኒውክሌር ሃይል ልምምድ ተመልክተዋል።

ፑቲን ቅኝት ባደረጉበት በዚህ ልምምድ የባለስቲክ እና ከባህር የሚወነጨፉ ሚሳኤሎች እንደተሞከሩ የፕሬዝዳንቱ ቢሮ ይፋ አደርጓል።  

ሩሲያና አሜሪካ ባለቸው ስምምነት መሰረት ይህንን የኒውክሌር ሙከራ በተመለከተ ለአሜሪካ መረጃ ተሰጥቷል።

እነዚህ ሙከራዎቹ የተካሄዱት ሩሲያ የዩክሬን ጦር “ቆሻሻ ቦንብ” ጥቅም ላይ ሊያውል ነው በሚል በማስረጃ ያልተደገፈ ውንጀላ እያቀረበች ባለበት ሰዓት ነው።

“ቆሻሻ ቦንብ” የፈንጂ አይነት ሲሆን 'ሬዲዩአክትቭ' ከተሰኘ ግብአት የሚሰራ ነው። ሆኖም በርካታ ምዕራባውያን ሀገራት ይህንን የሩሲያ ውንጀላ ሀሰት ነው ሲሉ አጣጥለውታል።

ዩክሬን በበኩላ የሞስኮ ውንጀላ ሩሲያ ራሷ በዚህ ቦምብ ጥቃት ልታደርስ እንደሆነ አመላካች ነው ብላለች።

ሩሲያ ዩክሬንን ከመውረሯ አምስት ቀናት ቀደም ብሎ ነበር የመጨረሻውን የኒውክሌር ልምምድ ያደረገችው።

የአሜሪካ ወታደራዊ ባለስልጣናት ሩሲያ የኒውክሌር ልምምድን ቀድማ በማሳወቅ ሀገራቱ የገቡትን ስምምነት እያከበረች ብብለዋል።

ከሁለቱ ሚሳኤሎች አንዱ የተወነጨፈው በባሪንትስ ባህር ውስጥ ከሚገኝ የኑክሌር ኃይል ባህር ሰርጓጅ መርከብ ነው።

የፎቶው ባለመብት, RUSSIAN DEFENCE MINISTRY

የምስሉ መግለጫ, ከሁለቱ ሚሳኤሎች አንዱ የተወነጨፈው በኒክሌር ኃይል በሚሰራ የባህር ሰርጓጅ መርከብ ነው።
Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

ኔቶም በሰሜን ምዕራብ የአውሮፓ ክፍል የኒውክሌር ልምምዱን ማደረግ ጀምሯል።

የጦር ቃል ኪዳን ድርጀቱ ይህ ልምምድ እስከ መጪው ዕሁድ ድረስ በቤልጂየም፣ በዩኬ እና ሰሜን ባህር እንደሚቀጥል አሳውቋል።

ይህ እየተካሄደ ያለው በደቡባዊ እና ምስራቃዊ ዩክሬን ወታደራዊ ሸንፈት እያስተናገደች ባለበት ሰዓት ነው።

የሩሲያ የኒውክሌር ልምምድ የተደረገው ሞስኮ ኬርሶን የተሰኘው እና ከዩክሬን የጠቀለለችውን ግዛት ለመከላከል ወታደሮችን ባሰማራችበት ወቅት ነው።  

ሩሲያ ኬርሶን የተኘውን የዩክሬን ግዛት የተቆጣጠረችው በጦርነቱ በተጀመረ ጥቂት ጊዜያት ውስጥ ቢሆንም የዩክሬን ሃይሎች ግስጋሴን ተከትሎ አከባቢው ላይ ጫና በዝቷል።

የሩሲያው መከላካያ ሚኒስትር ሰርጌ ሾጊ በቴሌቪዢን ቀርበው በደረጉት የኒውክሌር ልምምዱ ወታደራዊ እዙን እና ቁጥጥሩን ለመመልከት ያለመ ሲሆን “የጠላትን የኒውክሌር ጥቃት አጸፋ ለመሰጠት በሚያስችል መልኩ” የተከናወነ ነው ብለዋል።

እስከ 800 ኪሎ ሜትር የሚሸፈን አህጉር አቋረጭ በሰሜናዊ ሞስኮ እንዲሁም ከቤራንቲስ ባህር ደግሞ ባለስቲክ ሚሳኤል መሞከሩን ጨምረው የገለጹ ሲሆን ሁሉም ሚሳኤሎች ግባቸውን መተዋል ብለዋል።

ፕሬዝደንት ፑቲን ሚሳኤሎቹ ሲተኮሱ በስክሪኖች እየተመለከቱ የሚያሳዩ ምስሎች ታይተዋል።

በተጨማሪም ከግዛት የስለላ አገልግሎቶች ጋር ምክክር ሲያደርጉ የሚያሳዩ ቪዲየዎች የተለቀቀ ሲሆን በዚህም ዩከሬን ላይ ያቀረቡትን “የቆሻሻ ቦንብ”ሴራ አጠናክረው ወቅሰዋል።

ጨምረውም ዩክሬን ላይ የቀረቡ መሰረተ የሌላቸውን ተጨማሪ ክሶችን አቅርበዋል።

የዩክሬን መከላከያ ሚኒስትር ኦለስኪ ሪዚንኮቭ “የኔ የግል እይታ ፑቲን ኒውከለር አይጠቀምም የሚል ነው” ሲሉ ለአሜሪካ ሚዲያ ብለዋል።

አክለውም ሀገራቸው የምታደረገው መልሶ ማጥቃት በዝናቡም የአየር ጸባይ ምክንያት ሊስተጓጎል እንደሚችል ተናግረዋል።

ባለፈው ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳናት ፑቲን ሀገራቸው “ጥፋት ሊያስከትሉ የሚችሉ” መሳሪያዎች እንዳላት ገልጸዋል።