ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የተመድ ዋና ጸሃፊ በአልጀዚራዋ ጋዜጠኛ ግድያ መደንገጣቸውን ተናገሩ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ትላንት ረቡዕ በአንጋፋዋ ፍልስጤም-አሜሪካዊ የአልጀዚራ ጋዜጠኛ ሺሪን አቡ አቅላ ላይ የተፈጸመው ግድያ "አስደንጋጭ ነው" ብለዋል።
አሜሪካም ግድያውን ያወገዘች ሲሆን "የዘጋቢዎች ጀግና " ስትልም ዘጋቢዋን ጠርታታለች።
የ51 አመቷ ዘጋቢ አቡ አቅላ የእስራኤል ሃይሎች በያዙት ዌስት ባንክ ውስጥ ያደረጉትን ወረራ ስትዘግብ ህይወቷ ሲያልፍ አብሯት በስራ ላይ የነበረው አዘጋጇም ጉዳት ደርሶበታል።
አልጀዚራ የእስራኤል ወታደሮች "ሆን ብለው" ጥይት ተኩሰውባታል ሲል የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር በበኩላቸው በፍልስጤም ታጣቂዎች ተመትታ ሳይሆን እንደማይቀር ተናግረዋል።
የናፍታሊ ቤኔት ወታደራዊ አዛዥ ግን የእስራኤል ታጣቂ ሃይሎች ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ እስካሁን አልቻሉም ብለዋል።
የፍልስጤም ባለስልጣን ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ "የሞት ቅጣት" ሲሉ ለገለጹት የእስራኤል መንግሥት ሙሉ ሃላፊነት እንደሚወስዱ ተናግረዋል።
ረቡዕ እለት በቃል አቀባዩ በኩል በሰጡት መግለጫ ሚስተር ጉተሬዝ "የሚመለከታቸው ባለስልጣናት በዚህ ክስተት ላይ ገለልተኛ እና ግልፅ የሆነ ምርመራ እንዲያካሂዱ እና ጥፋተኞች ተጠያቂ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርበዋል ።
"ዋና ጸሃፊው በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እና ግድያ ሁሉ ያወግዛል እናም ጋዜጠኞች በፍፁም የጥቃት ኢላማ መሆን የለባቸውም" ሲል መግለጫው አክሎ ተናግሯል።
ይህ በንዲህ እንዳለ የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ጄን ፕሳኪ በትዊተር ገፃቸው ላይ እንደፃፉት አሜሪካውያን ስለ አቡ አካላ ግድያ እና በፕሮዲዩሰርዋ ላይ የደረሰውን ጉዳት በማወቁ ልባቸው ተሰብሮ ነበር።
ወይዘሮ ፕሳኪ አክለውም "ለቤተሰቦቿ፣ ለጓደኞቿ፣ እና ግድያዋን አጥብቀን እናወግዛለን፣ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንልካለን" ስትል "የሚያውቁት ሁሉ የሚያዝኑባት" ሲሉ ጠርተዋታል።
የእስራኤሉ የመከላከያ አዛዥ የአገራቸው የጦር ሃይሎች ምን እንደተፈጠረ እስካሁን መለየት አልቻሉም ሲሉ ተናግረዋል።
የፍልስጤሙ መሪ መሃመድ አባስ በበኩላቸው ''ለተፈጸመው የግድያ ወንጀል'' የእስራኤል መንግሥት ሙሉ ሃላፊነት አለበት ሲሉ ወንጅለዋል።
"የሚመለከታቸው የመንግሥት ሃላፊዎች ገለልተኛ እና ግልጽ የሆነ ምርመራ እንዲያደርጉ ብሎም ድርጊቱን የፈጸሙትንም ተጠያቂነት እንዲያረጋግጡ'' ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒ ጉቴሬዝ በቃል አቀባያቸው በኩል ጥሪያቸውን አቅእርበዋል።
ዋና ጸሃፊው በጋዜጠኞች ላይ የሚደርስ ማንኛውም አይነት ጥቃት እንዲሁም ግድያን ያወገዙ ሲሆን ጋዜጠኞች የማንኛውም አይነት ጥቃት ኢላማ መሆን እንደሌለባቸው ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄን ፓሳኪ ''አሜሪካዊያን ግድያውን ሲሰሙ ልባቸው ተሰብሯል'' ሲሉም በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።