ቼልሲን ለመግዛት ፍላጎታቸውን ከገለጹ መካከል የትኞቹ ከፍ ያለ ዕድል አላቸው?

የፎቶው ባለመብት, PA Media
ሮማን አብራሞቪች ከ19 ዓመት በፊት ቼልሲ የእግር ኳስ ክለብን በ140 ሚሊዮን ፓወንድ ነበር የገዙት፤ በአሁኑ ወቅት ግን ቡድኑ 3 ቢሊየን ፓወንድ ያወጣል ብለው ያስባሉ።
ከሽያጩ የሚገኘውን ገንዘብም በሩሲያና ዩክሬን ለተጎዱ ሰዎች መርጃ እንደሚውል አመልክተዋል።
በቺካጎ የቤዝቦል ሊግ ውስጥ ታላላቅ ከሚባሉት ቡድኖች አንዱ የሆነውን ቺካጎ ከብስን በባለቤትነት የያዘው 'ዘ ሪኪትስ ፋሚሊ'፤ 'የሎርድ ኩ' የተኘው ባለሃብት እና በብሪታኒያዊው ባለሀብት ኒክ ካንዲ የሚመራው ጥምረት ቼልሲን ለመግዛት ከሚወዳደሩት መካከል ናቸው።
የእንግሊዝ የፕሪሚየር ሊግ ክለብ ቼልሲ በሩሲያዊው ባለቤት ሮማን አብራሞቪች ለሽያጭ ከቀረበ በኋላ የጨረታው መዝጊያ ትናንት አርብ ነበር።
የቼልሲ ደጋፊና ለጨረታው የቀረበው ካንዲ ከደቡብ ኮሪያ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት እንዳገኘ እና ለጨረታው ከ2 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ እንደሚያቀርብ አሳውቋል።
አብራሞቪች ክለቡን ለመሸጥ የደረጉት ሙከራ በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) መንግሥት ማዕቀብ ከተጣለባቸው በኋላ ቼልሲን ጨምሮ ያሏቸው ንብረቶች ታግደዋል።
የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት እዚህ እርምጃ ላይ የደረሰው ሩሲያ ዩክሬንን በመውረሯ ሲሆን አብራሞቪች ደግሞ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ጥብቅ ግንኙነት አላቸው በሚል ነው።
ይህም በመሆኑ የአሜሪካው የኢንቨስትመንት ድርጅት 'ሬይን ግሩፕ' ቼልሲን የመሸጥ ኃላፊነት የተሰጠው ሲሆን ክለቡን ለመሸጥ የሚያስችል አዲስ ፍቃድ ከዩኬ መንግሥት ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ምንም እንኳን ቼልሲን ለመግዛት የወጣው የመጨረሻ ቀነ ገደብ ትናንት አርብ ቢሆንም፣ አንዳንድ ተጨራቾች እስከ ቅዳሜና እሁድ ድረስ ሊቀርቡ እንደሚችሉ ተገምቷል።
ክለቡን ለመግዛት ከ20 በላይ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ቢኖሩም በጨረታው እንደሚሳተፉ የተረጋገጡት ከ10 እስከ 15 የሚሆኑት ናቸው።
ቼልሲ እና ራይን ግሩፕ በሚቀጥለው ሳምንት ለጨረታ የሚወዳደሩ ዕጩዎችን ይፋ ያደርጋሉ። ይፋ የሚደረጉት ተጫራቾች በጨረታው ለመቀጠል የመንግሥት ይሁንታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፣ ይህም የገንዘቡን ምንጭ እና የገንዘቡን ቀጣይ መዳረሻ ለማወቅ ያለመ ነው ተብሏል።
በተጨማሪም ማንኛውም የክለብ ሽያጭ በፕሪሚየር ሊጉ ባለቤቶች ይሁንታ ማግኘት ስላለበት ቼልሲም በዚህ ሂደት ያልፋል።
ቼልሲን የመግዛት ሰፊ ዕድል ያላቸው ተጫራቾች የትኞቹናቸው?
- ቀዳሚ ግምት የተሰጠው በቀድሞው የሊቨርፑል ሊቀመንበር ማርቲን ብሮቶን የሚመራው ጥምረት ሲሆን ይንን ጥምረት የለንደን ኦሊምፒክ ዝግጅት የበላይ የነበሩት ሴባስቲያን ኮ ተቀላቅሏል።
- ዘ ሪኪትስ ፋሚል፣ የቺካጎ የሜጀር ሊግ ቤዝቦል ቡድን ባለቤት ሲሆን ለጨራታ የቀረቡ ኢንቬስተሮችን እየመራ ነው
- የስዊትዘርላንዱ ቢሊየነር ሀንስዮርግ ዊስ እና አሜሪካዊው የንግድ ሰው ቶድ ቦህሊ ቼልሲን ለመግዛት ጥምረት ፈጥረዋል። አሁን ደግሞ የአሜሪካዊው የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ ባርባራ ቻሮን፣ ብሪታኒያዊው የንግድ ሰው ጆናታን ጎልድስተይን እና ብሪታኒያዊው ጋዜጠኛ ዳንኤል ፊንከልስቴይን ተቀላቅለዋቸዋል።
- መሰረቱን ለንደን ያደረገው እና በፖርቹጋላዊው ሥራ ፈጣሪ ሪካርዶ ሲልቫ የሚመራው ኤቴል ፓርትነርስ የኢንቨስትመንት ተቋም ሌላው ሰፊ ዕድል ያለው ተጫራች ነው።
- የብሪታኒያዊው ባለብዙ ሚሊየን ባለሃብት ኒክ ካንዲ በቀድሞው የቼልሲ አጥቂ ጃንሉካ ቫይላ የተሳተፈበት 'ቲፎሲ' የተሰኘ የእግር ኳስ ዘርፍ ቢዝነስ ውህደት ነው። ይህ ውህደት ቼልሲን ለመግዛት ፍላጎት ያሳየ ሲሆን ሌሎች ዕውቅ የቢዝነስ ኩባንያዎች በጋራ ለመጨረት ተቀላቅለውታል።
- በክሪስታል ፓላስ የባለቤት ድርሻ ያለው የአሜሪካዊው ቢሊየነር እና የፊላዴልፊያ '76ers' ባለቤት ጆሽ ሃሪስ በክሪስታል ፓላስ በጨረታው ይሳተፋል። ከዚህ በተጨማሪ በሳዑዲ አረቢያ የሚገኝና ሌሎች ድርጅቶች ድርሻ አላቸው።















