ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ባለቤቱን በኮብራ እባብ አስነድፎ ያስገደለው ህንዳዊ በእስራት ተቀጣ
ባለቤቱን የኮብራ እባብ አስነድፎ በማስገደሉ ጥፋተኛ የሆነው ህንዳዊ ባልተለመደ ሁኔታ በሁለት የእድሜ ልክ እስራት ቅጣት ተቀጥቷል።
ሱራጅ ኩማር የተባለው ግለሰብ ባለቤቱ ኡትራ በእባብ ተነድፋ በመሞቷ ባለፈው ዓመት ነበር በቁጥጥር ስር የዋለው።
ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው ቤተሰቦቿ ለጥሎሽ ሲያስቸግራቸው እንደነበር ገልጸው ሳይገድላት እንዳልቀረ መናገራቸውን ተከትሎ ነው ፖሊስ ምርመራውን የጀመረው።
ባለቤቱ ተኝታ በነበረበችበት ወቅት አንድ ኮብራ እባብ አልጋው ላይ ለቅቆ በማስነደፍ ፍርድ ቤቱ ሰኞ እለት ጥፋተኛ ሆኖ አግኝቶታል።
የ25 አመቷ ባለቤቱ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር በቤቷ ውስጥ ሞታ ተገኝታለች።
ከሳምንታት በፊት ኡትራ ራስል ቫይፐር በተባለ እባብ ከሳምንታት በፊት ተነድፋ ስለነበር ነር ቤተሰቧቿ ጥርጣሬ አደረባቸው።
ከመጀመሪያው የእባብ መነደፍ እያገገመች በነበረበችበት ጊዜ በኮብራ እባብ ድጋሚ ተነድፋ መገደሏም ተገልጿል።
ሱራጅ በሁለቱም መነደፍ በስተጀርባ እንዳለበት በመጠርጠርም ነው ምርመራውን ፖሊስ የጀመረው።
እንዲሁም ፖሊሶች እባቦችን እንዲገዛ የረዳውን ሰው በቁጥጥር ስር አውለዋል። ግለሰቡ ፖሊሶችን እንደረዳና ጥፋተኛነቱም እንደተረጋገጠ ተገልጿል።
ላይቭ ሎው የተባለው የህንድ የህግ ድረ ገጽ እንደዘገበው ፖሊስ በሱራጅ የታቀደውንና የተተገበረውን ሰፊ ሴራ በክሱ በ1 ሺህ ገፆች በዝርዝር አስቀምጧል።
ዓቃቤ ሕግ በበኩሉ ያልተለመደ ወንጀል ነው በማለትም የተከራከረ ሲሆን እናም ለተከሳሹ የሞት ቅጣት ጠይቋል።
ዳኛው ያልተለመደ ወንጀል መሆኑን ቢቀበሉም ለሱራጅ ሁለት የእድሜ ልክ እስራትና 6 ሺህ 635 ዶላር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል አዘውታል።