በጁዶ ስልጠና 27 ጊዜ ወደ መሬት የተጣለው የታይዋን ታዳጊ ሞተ

የጁዶ ስልጠና

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

በታይዋን ጁዶ በተባለው ራስ የመከላከል ሰፖርት አይነት 27 ጊዜ ከአየር ወደ መሬት የተጣለው የ7 አመት ታዳጊ ህይወት አልፏል።

በሚያዝያ ወር ላይ ህፃኑ በጁዶ ስልጠና ወቅት አብሮት የሚማር ታዳጊና አሰልጣኘ ከአየር ላይ ወደ መሬት ማጣጋታቸውን ተከትሎ ጭንቅላቱ ደም መፍሰስ አጋጥሞታል ተብሏል።

ስሙ ያልተጠቀሰው ይህ ታዳጊ ራሱን ስቶ በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ በአጋዥ መሳሪያ እየታገዘ ይተነፍስ ነበር።

ከ70 ቀናት በሆስፒታል ቆይታም በኋላ ቤተሰቦቹ አጋዥ መሳሪያው እንዲነቀል ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን የአገሪቱ ሚዲያ ታይፔይ ታይምስ ዘግቧል።

ሆ የተባሉት አሰልጣኝ ልጁ ሆስፒታል እንደገባ በቁጥጥር ስር ውለው የነበረ ቢሆንም ከሳምንታት በፊት በ3 ሺህ 583 ዶላር ዋስ ወጥተው ነበር።

በአሁኑ ወቅት ታዳጊው መሞቱን ተከትሎ አቃቤ በመጀመሪያ ያቀረበውን ክስ በመቀየር "ወደ ሞት የሚያደርስ አደጋ በሚል" እንደሚቀይረውም ታይዋን ኒውስ የተባለ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ግለሰቡ ጥፋተኛ ሆኖም ከተገኘ ከሰባት እስከ እድሜ ልክ እስራት የሚቆይ የእስር ቅጣትም እንደሚጠብቀው ዘገባዎች ያሳያሉ።

የሰባት አመቱ ታዳጊ በአውሮፓውያኑ ሚያዝያ 21 ከአጎቱ ጋር ወደ ጁዶ ስልጠና ሄደ።

አጎቱ በወቅቱ አብሮት የሁደው ጁዶ ለህፃኑ አደገኛ መሆኑን ቀርፆ ለታዳጊው ለማሳየት ነው።

ቪዲዮው እንደሚያሳየው በልምምድ ወቅት ተለቅ ባለ ታዳጊው ወደ መሬት የተጣለ ሲሆን በህመም ሲጮህ ይሰማል።

ነገር ግን አሰልጣኙ እንዲነሳና ልጁ አሁንም እንዲጥለው የነገረው ሲሆን ራሱን መሬት ላይ ጥሎታል።

በመጨረሻም ታዳጊው ራሱን ስቶ ተዝለፍልፎ የወደቀ ሲሆን አሰልጣኙ ውሸቱን ነው በማለት እንደወቀሰውም ቤተሰቦቹ ተናግረዋል።

አጎቱ ለምን አሰልጣኙን እንዳላስቆመው በተጠየቀበት ወቅት በታይዋን ለአሰልጣኞችና ለመምህራን ከፍተኛ ክብር እንዳለና ስልጣናቸው ጥያቄ ውስጥ እንደማይገባ ነው።

አሰልጣኙ ፍቃድ እንደሌለውም ታውቋል " ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁበትን ያችን ጥዋት አስታውሳታለሁ፤ ዘወር ብሎ አይቶኝ እማ ቻው አለኝ" በማለት የሚናገሩት እናቱ በምሽትም እንዲህ ሆኗል።