የአሪዞና ፖሊስ የበጎ አድራጎት ጉዞ ላይ የነበሩ ብስክሌተኛችን የገጨ አሽከርካሪ ላይ ተኮሰ

የእሳት አደጋና ሌሎች ተሽከርካሪዎች

የፎቶው ባለመብት, Show Low Police Department

ታትሟል

በአሜሪካ አሪዞና ግዛት የጭነት ተሽከርካሪ የሚዘውር ግለሰብ በደረሰው አደጋ የበጎ አድራጎት ጉዞ ላይ ተሳትፈው የነበሩ ስድስት ብስክሌተኞች ለከባድ ጉዳት ዳርጓቸዋል።

ታዲያ የ35 ዓመቱ አሽከርካሪ አደጋው ከደረሰ በኃላ ለማምለጥ የሞከረ ሲሆን ፖሊስ ተከትሎ ለማያዝ ያደረገው ጥረት ባለመሳካቱ እንደተኮሰበት ተመላክቷል።

በእርምጃውም አሽከርካሪው ላይ የከፋ ጉዳት ቢደርስበትም ለህይወቱ እንደማያሰጋ ግን ተገልጿል።

የአካባቢው ፖሊስ ጸህፈት ቤት ቃል አቀባይ ክርስቲን ስሌተር "በዚህ ክስተት ማህበረሰባችን የተደናገጠ ሲሆን ልባችን እና ጸሎታችን ከተጎጂዎች እና ቤተሰቦቻቸው ጋር ነው" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ቃል አቀባይዋ በአቅራቢያቸው ያለው ካውንቲ ወንጀለኛውን በማደን በኩል እንደረዳቸውና የአሪዞና የህዝብ ደህንነት መስሪያ ቤት በተጠርጣሪው ላይ ፖሊስ የወሰደውን ርምጃ በተመለከ ምርመራ እያካሄደ መሆኑንም ገልጸዋል።

እንደ ፖሊስ ገለጻ ከአደጋው በኋላ ስድስት ብስክሌተኞች ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አራቱ በአስጊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ሲሆን የተቀሩት ሁለቱ ደግሞ ከባድ ጉዳት ቢያጋጥማቸውም ለህይወት የሚያሰጋ ሁኔታ ላይ አይደሉም፡፡

ሌሎች ሁለት ወይም ሶስት የሚሆኑ የአደጋው ሰለባዎች ደግሞ በራሳቸው ወደ ሆስፒታል የሄዱ ሲሆን የከፋ ጉዳት አላጋጠማቸውም።

ውድድሩን 'ስፖንሰር' ያደረገው የአከባቢው የብስክሌት መደብር ባለቤት ማይክ ጋድዊን በተሽከርካሪው የተጎዱት የብስክሌተኞች ቡድን አባላት ዕድሜያቸው 55 እና ከዚያ እንደሆነ ለኒው ዮርክ ታይምስ ገልጸዋል።

'ባይክ ብላፍ' የተሰኘው ውድድሩ በምስራቅ አሪዞ የሚከናወን ሲሆን በኩል 93 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው። አለማውም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመግንባት ገቢ ማሰባሰብ ነው።