በሺዎች የሚቆጠሩ ሀሰተኛ የበይነ መረብ መድሃኒት መደብሮች ተዘጉ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
በግንቦት ወር በዓለም ዙሪያ ባሉ ሀሰተኛ የ'ኦንላይን' (በይነ መረብ) መድሃኒት መደብሮች ላይ የተወሰደው ይህ እርምጃ እስካሁን ከነበሩት ከፍተኛው ነው ተብሏል።
ዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም [ኢንተር ፖል] እያደረገ ያለው ዘመቻ አካል በሆነው በዚህ እርምጃ በበይነ መረብ አማካኝነት ህገ ወጥ መድሃኒቶች የሚሸጡ ከ100 ሺህ በላይ የ'ኦንላየን' (በይነ መረብ) ገበያዎች እንዲወገዱ ተደርገዋል።
በዚህ ዘመቻ በዩኬ 13 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ህገ ወጥ መድሃኒት በቁጥጥር ስር ውሏል።
እንድ አውሮፓውያኑ የዘመን ስሌት በ2008 ዘመቸው ከተጀመረ በኃላ የተመዘገበ ከፍተኛ ውጤት ሲሆን እርምጃው ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ ህገ ወጥ የ'ኦንላየን' የመድሃኒት ግብይት በተጦጦፈበት ጊዜ የተወሰደ ነው።
እንደ አውሮፓውያኑ በዘመቻው ከግምቦት 18 እስከ 25 ድረስ በነበሩት ቀናት በ92 ሀገራት 277 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 20 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ህጋዊ ያልሆነ መድሃኒትና ከህክምና ጋር የተያያዙ መሰራያዎች በመንግስታቱ ተወርሷል።
በቁጥጥር ከዋሉት ቁሶች አብዘኞቹ ለኮሮና ቫይረስ ምርመራ የሚውል ሀሰተኛና ትክክለኝነታቸው ያልተረጋገጠ ኪቶች መሆናቸም ተዘግቦል።
በዩኬ ከ3 ሺህ በላይ ህገ ወጥና ፍቃድ የሌላቸው የህክምና ምርቶችን የሚያስተዋውቁ የኢንተርኔት ማስታወቂያዎች የተወገዱ ሲሆን 43 ድረ ገጾች ደግሞ ተዘግተዋል።








