ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
'የምፅዓት ቀን' እምነት ተከታዮቹ ጥንዶች በልጆቻቸው ግድያ ክስ ተመሰረተባቸው
ከጥንዶች የቀድሞ ትዳር የተወለዱት ሁለት ልጆች ባለፈው ዓመት ህልፈታቸው ከተሰማና ከረዥምና ካልተለመድ የፍርድ ሂደት በኋላ በመጀመሪያ ደረጃ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ተከሰዋል።
የ7 ዓመቱ ጆሽዋና የ17 ዓመቷ ታይሊ ሪያን አስክሬን የተገኘው በአንደኛው ተከሳሽ ዴቤል መኖርያ ቤት ሲሆን ተከሳሽ ደራሲ እንደነበር ታውቋል።
ከዚህም ባለፈ ጥንዶቹ 'የምፅአት ቀን' የተሰኘ እምነት ተከታይ መሆናቸውና ባል ቻድ ዴቤል እምንቱን በተመለከተ የተለያዩ ድርሰቶች ማዘጋጀቱ ጉዳዩ የመገናኛ ብዙሃንን ቀልብ ስቦ ነበር።
ጥንዶቹ የሚከተሉት ይህ እምነት ለዓለም ፍፃሜ መዘጋጀትን በእጅጉ የሚያበረታታ በመሆኑ ምንአልባት ከህፃናቱ ሞት ጋር ግንኙነት ይኖረዋል በሚል ነው ትኩረትን ያገኘው።
በተጨማሪም ዴቤል አዲሱን ትዳር ከመሰረተ ከሳምንት በኋላ የቀድሞ ባለቤቱ መሞቷን ተከትሎ በሌላ የግድያ ወንጀልም ተከሷል።
ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን ማስረጃን በመሰወር ነበር የተከሰሱት። ታዲያ ይህ የፍርድ ሂደት ባልተጠበቀ ሁኔታ ተቀይሮ ባለፈው ማክሰኞ ጥንዶቹን በግድያ ወንጀል ተከሰዋል።
ጥንዶቹ ከግድያው ክስ ባሻገር በሌብነትና በኢንሹራንስ ማጭበርበር ክስ እንደሚጠብቃቸውም ተገልጿል።
የፍሪሞንት ካውንቲ አቃቤ ሕግ ሊንዚ ብሌክ 'የምፅአት ቀን' እምነት ተከታዬቹ ጥንዶች ሆን ብለው 3 ንፁሀንን ገድለዋል ለማለት የሚያስችል በቂ ምክንያት አለን ሲሉ ተደምጠዋል።