የኮቪድ -19 ዝርያዎች በክትባቱ ላይ ‘ስጋት’ ፈጥረዋል ተባለ

ደ/ር ሮሼል ዋሌንስኪ፣ የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕከል (ሲ ዲ ሲ) ኃላፊ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ታትሟል

በከፍተኛ ተላላፊ የሆኑት የኮሮናቫይረስ ዓይነቶች መስፋፋት በአሜሪካ "ለአራተኛ ጊዜ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ሊያንረው ይችላል" የሚል ስጋት መኖሩን አንድ ከፍተኛ የጤና ባለሥልጣን አስጠንቅቀዋል፡፡

የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕከል (ሲ ዲ ሲ) ኃላፊ በቅርቡ የሚወጡት የኮቪድ -19 መረጃዎች እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት በቀን ወደ 70 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መያዛቸው መመዝገቡን "በጣም ከፍተኛ ቁጥር" ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ጊዜ በየቀኑ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች እንደሚሞቱ ተናግረዋል፡፡

"እባካችሁ በግልፅ አድምጡኝ በዚህ ዝርያ ስርጭት ያገኘነውን ስኬት ልናጣው እንችላለን፡፡ አዳዲሶቹ ዝርያዎች ለህዝባችንም ሆነ ለዕድገታችን እውነተኛ ስጋት ናቸው" ሲሉ የሲዲሲዋ ዳይሬክተር ዶ/ር ሮሼል ዋለንስኪ ሰኞ ዕለት ገልጸዋል።

በርካታ የኮቪድ -19 ዝርያዎች ስርጭት ቢኖርም የጤና ባለሙያዎች ለጥቂቶቹ ብቻ ትኩረት ሰጥተዋል፡፡

በዚህም መጀመሪያ በእንግሊዝ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በብራዚል ይበልጥ ተላላፊ የሚመስሉ ዓይነቶችን ያካትታሉ፡፡

ሲዲሲ በእንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በጣም ተላላፊው B.1.1.7 የተሰኘው ዝርያ በዚህ ወር በአሜሪካ ዋነኛው ስጋት እንደሚሆን ተንብይዋል፡፡

አዲሶቹ ዝርያዎች በአሜሪካ ከባድ ችግር ናቸው?

ክትባቶች መሰጠት ከጀመሩበት ጥር ወር ጀምሮ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ዕለታዊ የሰዎች በቫይረሱ የመያዝ እና የሞት ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል፡፡

ሲዲሲ ይህን ለብዙዎች ክትባት እስከሚሰጥ ድረስ አዲሶቹ ዝርያዎች ቀድሞውኑ በችግር ላይ ያሉ የጤና ስርዓቶችን አደጋ ላይ እስከሚጥሉ ድረስ በፍጥነት ሊዛመቱ ይችላሉ ብሏል፡፡

እንደሲዲሲ መረጃ ከሆነ አሳሳቢ የሆኑ ዝርያዎችን የሚያካትቱ ከ 2 ሺህ 463 በላይ ኢንፌክሽኖች ሪፖርት ተደርገዋል፡፡ ቢያንስ 2 ሺህ400 የሚሆኑት በእንግሊዝ የተገኘው ዝርያ ዓይነት ናቸው፡፡

በአሜሪካ ውስጥ በአዳዲሶቹ ዝርያዎች የተያዙ ሰዎች እውነተኛ ቁጥር ከዚህ የበለጠ ነው ተብሎ ይገመታል፡፡

በአዳዲሶቹ ዝርያዎች የሚጠቁ ሰዎች ላይ በጣም ከባድ በሽታ ስለማምጣቱ ምንም ማስረጃ የለም፡፡

የሳይንስ ሊቃውንት በሥራ ላይ የዋሉት ክትባቶች አዳዲሶቹንም ዝርያዎች ጭምር ይከላከላሉ ብለው ያምናሉ፡፡

ክትባቶቹ በአሜሪካ ምን ይመስላሉ?

እስከሰኞ ድረስ አሜሪካ ከ 76 ሚሊዮን በላይ ክትባቶችን እንደሰጠች የሲዲሲ መረጃዎች ያመለክታሉ።

አሜሪካ ከዓለም ሀገሮች ከፍተኛውን የክትባት መጠን ሰጥታለች፡፡ ሆኖም ቁጥሮቹ ከሕዝብ ቁጥር ለ100 ሰዎች ከተሰጠው አንጻር ሲወዳደር አሜሪካ ከእንግሊዝ፣ ከአረብ ኤሚሬቶች እና ከእስራኤል ቀጥሎ በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

በአሜሪካ ክትባት ከተሰጣቸው መካከል የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ እንደሚገኙበት ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡ ሁለቱም በጥር ወር ኋዋይት ሃውስ ክትባቱ እንደወሰዱ አንድ አማካሪ ለኒው ዮርክ ታይምስ እና ለሌሎች የአሜሪካ የመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል፡፡

የትኛው ክትባት እንደወሰዱ ግልፅ ባይሆንም በጥር ወር በተቆጣጣሪዎች ፈቃድ ያገኙት የፋይዘር እና ሞደርና ክትባት ብቻ ነበር፡፡

በጆንሰን እና ጆንሰን የተሠራው እና አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጠው ክትባት በአሜሪካ ጥቅም ላይ እንዲውል ቅዳሜ ፈቃድ አግኝቷል፡፡

ዶ/ር ዋለንስኪ በአሜሪካ ግዛቶች ሪፖርቶች "በእውነት ተጨንቄያለሁ። ሰዎችን ከኮቪድ-19 ለመከላከል ወደምንመክረው ትክክለኛ የህዝብ ጤና አጠባበቅ እርምጃዎችን ወደ ኋላ ትመልሳለች" ብለዋል፡፡

"አራተኛ ዙር ከፍተኛ ቫይረሱ ስርጭር በዚህ እንዳይከሰት የማስቆም አቅም አለን፡፡ እባካችሁ በእምነታችን ጠንካራ እንሁን" ብለዋል፡፡

አሜሪካ ከ 28 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙባት እና ከኮቪድ -19 ጋር በተያያዘ 500,000 ሰዎችን ሞት አስመዝግባለች ይላል የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ፡፡