ሰውነቱና ፊቱ በንቅሳት የተሸፈነው ፈረንሳያዊ ህፃናትን ማስተማር አትችልም ተባለ

ሲልቫይን ሄላይን

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ታትሟል

ሰውነቱና ፊቱ ሙሉ በሙሉ በንቅሳት የተሸፈነው ፈረንሳያዊ የመዋዕለ ህፃናት ተማሪዎችን ማስተማር አትችልም ተብሏል።

ይህም የሆነው አንድ ቤተሰብ ከንቅሳቱ ጋር በተያያዘ ቅሬታ ለትምህርት ቤቱ መቅረቡን ተከትሎ ነው።

ሲልቫይን ሄላይን የተባለው ይህ ግለሰብ ሰውነቱ፣ ፊቱ፣ ምላሱ በንቅሳት ሙሉ በሙሉ የተሸፈነ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ አይኑንም በቀዶ ህክምና ጥቁር ነጥብ አድርጎበታል።

የ35 አመቱ ሲልቫይን አሁንም ከስድስት አመት በላይ የሆኑትን አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ማስተማር እንደሚችልም በትምህርት ቤቱ አመራሮች ተነግሮታል።

ሆኖም ቅሬታ ያቀረበችው ወላጅ ህፃን የእርሱ ተማሪ እንዳልሆነች የእርሱ ተማሪዎች እንደሚወዱትና ንቅሳቱንም በጥሩ መልኩ ያዩታል ብሏል።

"ከሩቅ የሚያዩኝ ሰዎች ብቻ ናቸው ስለ ንቅሳቴ መጥፎ ነገር የሚያስቡት" በማለትም ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግሯል።

ሲልቫይን ሄላይን

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ሲልቫይን ወይም በቅፅል ስሙ 'ፍሪኪ ሁዲ' ፓላይሲሁ በመዲናዋ ፓሪስ አካባቢ በሚገኝ ፓላይሲያው በሚባል ትምህርት ቤት እያስተማረ ይገኛል።

ባለፈው አመትም እንዲሁ የሶስት አመት ህፃን እሱን ማየቱ እያቃዠው እንደሆነም ለቤተሰቦቹ ተናግሯል።

የህፃኑ ወላጆች ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር ቅሬታ አቀረቡ።

ከሁለት ወራትም በኋላ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር በዚህ እድሜ ያሉ ህፃናትን ማስተማር እንደማይችልም ሲነግሩትም በጣም እንዳሳዛነውም አልደበቀም።

ንቅሳቱ ከነሱ የተለዩ ህፃናትን እንዲቀበሉ ይረዳልም ብሎ ያምናል።

"እኔን የሚያዩ ህፃናት መቻቻል እንዲማሩ ይረዳቻዋል። በዕድሜያቸው ትልቅ ሲሆኑ በተወሰነ ደረጃ ዘረኛ፣ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎችን የሚጠሉ አይሆኑም። ከዚህም በተጨማሪ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎችንም ሰርከስ የሚያሳዩ እንደሆነም አድርገው አያዩዋቸውም" ብለዋል።

ሲልቫይን ፊቱንና ሰውነቱን ለመሸፈን 460 ሰዓታትን ፈጅቶበታል።

ከነዚህም መካከል በአይኖቹ ያለው የቀዶ ህክምናን ለማድረግ ወደ ስዊዘርላንድ መጓዝ ነበረበት። ለዚህም ምክንያቱ በፈረንሳይ ህጋዊ ባለመሆኑ ነው።