አሰቃቂው የኢራን አስክሬን ማቆያ ክፍል ገጽታ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ኮሮናቫይረስ፡ በኢራን አስክሬን ማቆያ ክፍል ውስጥ
ታትሟል

ይህ ቪዲዮ በመንግሥት የአስክሬን ማቆያ ክፍል የተቀረጸ ነው። በቪዲዮ ላይ ሠራተኞች በበርካታ አስክሬኖች ተከበው ሥራቸውን ሲያከናውኑ ይታያሉ።

ገሚሱ አስክሬን በነጭ ጨርቅ ተጠቅልሏል። ሌላው በጥቁር ላስቲክ ተከቷል።

ቪዲዮን እየቀረጸ ያለው ሰው በነጭ ጨርቅ የተጠቀለሉት ዛሬ ጠዋት "የተሠሩ" ናቸው ይላል።

ከዛ ደግሞ በጥቁር የአስክሬን ላስቲክ ውስጥ የተጠቀለሉ እስክሬኖችን እያሳየ፤ "እነዚህ ደግሞ ቀብራቸው ከመፈጸሙ በፊት ገና ለቀብር ዝግጁ የሚደረጉ ናቸው" ሲል ይናገራል።

ከዚያ የስልኩን ካሜራ ከአንድ ክፍል ወደ ሌላው እየወሰደ በተመሳሳይ መልኩ ተደርድረው የሚታዩ በርካታ አስክሬኖችን ያስቃኛል።

ይህ ቪዲዮ የተቀረጸው በኢራን ቆም በምትባል ከተማ ውስጥ ነው። ኮሮናቫይረስ በኢራን መሰራጨት የጀመረው ከዚች ከተማ እንደሆነ ይታመናል።

ቪዲዮን የሚቀርጸው ግለሰብ ሁሉም በኮሮናቫይረስ ምክንይት እንደሞቱ ይናገራል። ቢቢሲ ግን ይህን አላረጋገጠም።

ቪዲዮን የሚቀርጸው ሰው፤ አስክሬኖቹ በዛ ስፍራ ከአምስት እስከ ስድስት ቀናት እንደቆዩ መናገሩ ግን የበርካቶችን ቀልብ ስቧል።

ይህ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከታየ በኋላ ኢራን ካመነችው በላይ በርካቶች በቫይረሱ ሳይሞቱ እና ሳይያዙ እንዳልቀሩ ያረጋገጠ ነው እየተባለ ነው።

Presentational grey line

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ አገራት በኮሮና ክፉኛ የተጠቃች አገር ናት።

በአገሪቱ ምን ያክሉ በቫይረሱ እንደተያዙ አልያም እንደሞቱ ማወቅ እጅጉን ከባድ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአገሪቱ የሚገኙ መንግሥታዊ አስክሬን ማቆያዎችን እና ቀብር አስፈጻሚዎች በአስክሬን ብዛት ተጥለቅልቀዋል።

ለዚህም እንደምክንያት ከሚጠቀሱት መካከል የግል ተቋማት ቫይረሱ ከሞቱ ሰዎች ወደ ሠራተኞቻችን ሊተላለፍ ይችላል በማለት በኮቪድ-19 ምክንያት ሞቱ ሰዎችን አስክሬን እንቀበልም ማለታቸው ይገኝበታል።

በአንዳንድ የመንግሥት አስክሬን ማቆያ ስፍራዎች በእስላማዊ ስርዓት አስክሬኖችን ለቀብር ዝግጁ እያደረጉ የሚገኙት በጎ ፍቃደኞች ናቸው።

የዓለም ጤና ድርጅት በኮቪድ-19 ከሞተ ሰው ቫይረሱ ስለመተላለፉ ማረጋገጫ ባይረኖርም ሰዎች በቫይረሱ የሞተ ሰው አስክሬን ጋር የሚኖራቸው ንክኪ ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት መሆን አለበት ሲል ይመክራል።

ለቪዲዮ የኢራን ባለስልጣናት ምላሻቸው ምን ነበረ?

በአስክሬን ማቆያ የተቀረጸውን ቪዲዮ በርካቶች ከተጋሩት በኋላ ቪዲዮን የቀረጸው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ውሏል። ባለስልጣናት ለሟች ቤተሰቦች ሁሉም አስክሬን በእስላማዊ ስርዓት በክብር እንደተያዙ ሲናገሩ ቆይተዋል።

የሟች ቤተሰቦች የዘመዶቻቸው አስክሬን እንዴት እንደተያዘ ማወቅ ቀርቶ የዘመዶቻቸው አስክሬን የት እንዳለ እንኳ እንደማያውቁ ይናገራሉ። መንግሥት ይህ ወረርሽኝ ካለፈ በኋላ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች የቀብር ስፍራዎችን ለዘመድ ወዳጅ እንደሚያሳውቅ ተናግሯል።

በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቀብር በኢራን

የፎቶው ባለመብት, Mehr news agency

የምስሉ መግለጫ, በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቀብር በኢራን

አንድ የኢራን መንግሥት ይፋዊ አሃዝ መሠረት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ60ሺህ በላይ ሲሆን በቫይረሱ ተይዘው ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ4ሺህ በላይ ነው። ይሁን እንጂ በአሜሪካ የሚገኙ ኢራናዊያን ተመራማሪዎች ባቨይረሱ የተያዙ እና የሞቱ ሰዎች ቁጥር መንግሥት ከሚለው ቁጥር እጅግ ከፍ ያለ መሆኑን ይናገራሉ።

ከማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት እና ቨርጅን ቴክ የሆኑት ኢራናውያን ተመራማሪዎች መንግሥት የሚሰጠው አሃዝ ትክክለኛነትን በመጠራጠራቸው ትክክለኛውን ቁጥር ያሳያል ያሉትን አንድ ስርዓት ፈጥረዋል።

ይህ ሰርዓት መነሻቸው ከኢራን ሆኖ በሌላ መዳረሻ አገር በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች እና ከበርካታ ኢራን ውስጥ ከሚገኙ የህክምና ተቋማት መረጃዎችን በመሰብሰብ በአገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ እና የሞቱ ሰዎችን ቁጥር አስልተዋል።

በዚህም መሠረት ከፈረንጆቹ ማርች 20 ወዲህ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 15ሺህ እንዲሁም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርን ደግሞ 1ሚሊዮን አድርሰውታል።

ይህ ቁጥር ግን መንግሥት ከሚለው ከ10 እጥፍ በላይ ከፍ ያለ ነው። የኢራን ባለስልጣናት ከማርች 20 ወዲህ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1433 እንዲሁም የሞቱት ደግሞ 20ሺህ ብቻ እንደሆነ አመላክተዋል።

ኮሮና
Banner