ዛምቢያ ዕፀ ፋርስን ህጋዊ ልታደርግ ነው

የፎቶው ባለመብት, PABLO PORCIUNCULA BRUNE
ታትሟል
የዛምቢያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዕፀ ፋርስ እንዲዘራ፣ ተመርቶም ለንግድም ሆነ ለመድሃኒትነት እንዲውል የሚያስችለውን ህግ እንዲረቀቅ ውሳኔ አስተላልፏል።
የመንግሥት ቃል አቀባይ ዶራ ሲልያ ባወጡት መግለጫ እንዳሳወቁት ውሳኔው የተላለፈው በቅርቡ በነበረ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውይይት ነው።
ቀጣዩ እርምጃ የሚሆነው ህጉ የሚረቀቅበት እንዲሁም ወደ ፓርላመንት ቀርቦ የሚፀድቅበት ቀን ነው፤
ለዚህ ደግሞ ቁርጥ ያለ ቀን አልተሰጠም።
በአለም ላይ ያሉ የተለያዩ ሃገራት የዕፀ ፋርስን መድሃኒትነት በመረዳት ህጋዊ እያደረጉ ሲሆን፤ በባለፈው አመት ሌሴቶ ዕፀ ፋርስን ለመድኃኒትነት ለመጠቀም ህጋዊ በማድረግ የመጀመሪያዋ ቀዳሚ አፍሪካዊ አገር ብትሆንም ኢንዱስትሪ ገና በጅማሮ ላይ ነው።
በትንሽ መሬት ዕፀ ፋርስን የሚያመርቱት ገበሬዎች ከመድኃኒት ዕፀ ፋርስ ጋር ሲወዳደር የቴክኖሎጂ አቅርቦትም ሆነ ንግዱ የሚያስፈልገው መነሻ ገንዘብ የላቸውም።
የመድኃኒቱ ዕፀ ፋርስ በትልቅ ደረጃ የታሰበ ከመሆኑ አንፃር ጋር ሲወዳደር ያለውን ከፍተኛ የስራ እድል ለመፍጠርም ትግል ላይ ነው።












