በፓሪስ ውስጥ አንድ ግለሰብ አራት ፖሊሶችን በስለት ገደለ

የፈረንሳይ ፖሊስ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ታትሟል

በፈረንሳዩዋ ዋና ከተማ ፓሪስ አንድ ግለሰብ በፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት በር ላይ ስለት በመጠቀም በፈጸመው ጥቃት አራት የፖሊስ አባላት ህይወታቸው ማለፉን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ።

ጥቃት ፈጻሚው የፖሊስ ዋና መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ህንጻ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ የነበረ ሲሆን ጥቃቱን በፈጸመበት ቦታ ላይ በፖሊሶች በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ማለፉም ታውቋል።

'ኢል ዴ ላ ሲቴ' የተባለው የፈርሳይ ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት የሚገኝበት አካባቢ ከማንኛውም እንቅስቃሴ መዘጋቱ ተገልጿል።

ይህ ጥቃት የተፈጸመው የፈረንሳይ ፖሊሶች በአባላሎቻቸው ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች እንዲቆሙና እራሳቸውን የሚያጠፉ ፖሊሶች ቁጥር መጨመሩ አሳስቦናል በማለት በመላው ሀገሪቱ ተቃውሞ ካካሄዱ ከአንድ ቀን በኋላ መሆኑ ብዙዎችን አስቆጥቷል።

የፈረንሳዩ የሃገር ውስጥ ሚንስትር ክሪስቶፍ ካስታነር ጥቃቱ የተፈጸመበት መገኘታቸውም ተነግሯል።

የፈረንሳይ ፖሊስ

የፎቶው ባለመብት, Reuters