የቀድሞው የቱኒዝያ ፕሬዚዳንት ቤን አሊ በግዞት ህይወታቸው አለፈ

ታትሟል

ቱኒዚያን ለሁለት አስርታት በኃያል ክንዳቸው የገዟት ዛይን ኢል አባዳን ቢን አሊ በ83 ዓመታቸው ዛሬ አርፈዋል።

ቢን አሊ ህልፈታቸው የተሰማው በጥገኝነት ከኖሩባት ሳኡዲ አረቢያ ነው።

ፕሬዚዳንቱ ቱኒዝያን ለ23 አመታት ያህል የገዙ ሲሆን መረጋጋትና ኢኮኖሚያዊ እድገትን በማምጣት ይወደሳሉ።

ነገር ግን ፖለቲካዊ ነፃነትን በማፈንና ሙስና በተንሰራፋ ስርአታቸውም በከፍተኛ ሁኔታ ይተቻሉ።

በጎርጎሳውያኑ 2011 የህዝቡን አመፅ ተከትሎም ከስልጣን ተገርስሰዋል።

ፍርድ ቤት በሌሉበት እድሜ ይፍታህ ፈርዶባቸው ነበር።

የሳቸውም ከስልጣን መወገድ ተከትሎም በአረቡ አለም ተዛምቶ በተመሳሳይ ሁኔታ ታሪካዊውን የአረብ ስፕሪንግን ፈጥሯል።

ብዙ ሃገራትም ለብዙ አመታት የገዙ መሪዎቻቸውንም መገርሰስ ችለዋል።

ከስልጣን መውረዳቸውን ተከትሎ እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ መቀመጫቸውን በሳዑዲ አረቢያ አድርገው ነበር።

ቀብራቸውም አርብ መስከረም 9፣ 2012 በሳዑዲ አረቢያ እንደሚፈፀምም ጠበቃቸው ለሮይተርስ ዜና ወኪል ተናግሯል።