ምዕራባውያን ማስቆም ያልቻሉት እስራኤል በቤይሩት ያደረሰችው ፍንዳታ

እስራኤል የሄዝቦላህ ዋና መቀመጫ ነው ያለችውን በአየር ደብድባለች።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, እስራኤል የሄዝቦላህ ዋና መቀመጫ ነው ያለችውን በአየር ደብድባለች።
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 2 ደቂቃ

የመካከለኛው ምሥራቅ ቀውስ እየተባባሰ ነው። የለየለት ጦርነት እየተቃረበም ይመስላል።

እስራኤል የሄዝቦላህ ዋና መቀመጫ ነው ያለችውን በአየር ደብድባለች።

ቤይሩት ውስጥ ያሉ ሰዎች እንደሚናገሩት ከፍተኛ ፍንዳታዎች ይሰሙ ነበር።

የሄዝቦላህ መሪ ሐሰን ናስረላህን ዒላማ እንዳደረገች እስራኤል ገልጻ ነበር። በማኅበራዊ ሚዲያ ግን የሚዘዋወረው መረጃ የተመታው ሕንጻ ውስጥ መሪው መኖሩ ላይ ጥያቄ ያነሳል።

ሄዝቦላህ ስለጉዳዩ ምንም አለማለቱ የበለጠ ጥርጣሬ አጭሯል።

ነፍስ አድን ሠራተኞች በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ለማግኘት እየሞከሩ ነበር።

እስራኤል የምታደርሰው ጥቃት አላቆመም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የ21 ቀናት የተኩስ አቁም በተመለከተ ውይይት ለማድረግ ዝግጁ ናቸው ተብሎ ነበር።

አሜሪካ እና ፈረንሳይ በዋነኛነት የተኩስ አቁም እንዲደረግ ግፊት አሳድረዋል።

ሆኖም ግን የተባበሩት መንግሥታት በኒው ዮርክ ባደረገው ጉባዔ ላይ ኔታንያሁ ያደረጉት ንግግር ዲፕሎማሲ የራቀው ነው።

እስራኤል “ሊያጠፏት የተነሱ ክፉ ጠላቶቿን ከመዋጋት በስተቀር አማራጭ የላትም” ሲሉ ተደምጠዋል።

ኔታንያሁ ባደረጉት ንግግር “ሄዝቦላህ ይሸነፋል። በጋዛ ሐማስን እናሸንፋለን። እስራኤላውያን ታጋቾችን እናስመልሳለን” ብለዋል።

ሊባኖስ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ብትሻም በቤሩት የደረሰው ፍንዳታና የኔታንያሁ ንግግር የተኩስ አቁም የማድረጉ ነገር ጠባብ ዕድል እንዳለው ይጠቁማሉ።

ፔንታጎን እንዳለው እስራኤል ጥቃት ልትፈጽም እንደምትችል ቀድሞ መረጃ አልደረሰውም።

ኔታንያሁ መልዕክት ማስተላለፊያ ስልክ ይዘው በኒው ዮርክ የተነሱት ፎቶ እየተዘዋወረ ሲሆን፣ ይህም ጥቃቱ እንዲፈጸም ትዕዛዝ የሰጡበት ወቅት ነው ተብሏል።

ነፍስ አድን ሠራተኞች በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ለማግኘት እየሞከሩ ነበር።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ነፍስ አድን ሠራተኞች በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ለማግኘት እየሞከሩ ነበር።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን ለወራት ሲያረቁት የነበረው ስምምነት ውጤት ሊያሳይ እንደሚችልና ለንግግር ዕድል እንዳለ ተናግረዋል።

አሜሪካ ሄዝቦላህ እና ሐማስን አሸባሪ ብላ ስለፈረጀች በቀጥታ ለማነጋገር ሕጉ አይፈቅድላትም። ምርጫ እየተቃረበ ስለመጣም ከዚህ ቀደም እንደተደረገው እስራኤል ላይ ጫና ማሳደር ቀላል አይሆንም።

ሐማስ እስራኤል ላይ ጥቃት ባደረሰ ማግሥት የእስራኤል ኃያላን ባለሥልጣናት ሄዝቦላህ ላይ ጥቃት ማድረስ ቢፈልጉም አሜሪካ አስቁማቸዋለች።

ሆኖም ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ኔታንያሁ ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፈቃድ ውጭ እየወጡ ነው።

ሊባኖስ ላይ የደረሰው የአየር ጥቃት የተፈጸመበት ተዋጊ አውሮፕላንና ቦምብ ከአሜሪካ የተሰጠ ቢሆንም ጥቃቱ ሲፈጸም አሜሪካ ዳር ላይ ሆኖ ከመመልከት ውጭ አማራጭ አልነበራትም።

ባይደን፣ ኔታንያሁ ላይ እንዴት ጦርነቱ እንደሚካሄድ ጫና ማሳደር እንደሚችሉ ያምኑ ነበር። በፍልስጤም የተገደሉ ንጹኃን ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነ ያምናሉ።

ብሊንከን ቤይሩት ላይ የደረሰውን ፍንዳታ ተከትሎ ባደረጉት ንግግር መካከለኛው ምሥራቅ ወደለየለት ጦርነት ያልገባው በዲፕሎማሲ ምክንያት ነው ብለዋል።

በቀጣይ ሄዝቦላህ በእስራኤል ላይ ምን ዓይነት ጥቃት ይሰነዝራል? የሚለው ይጠበቃል።

የቀራቸውን ሚሳዔልና ሮኬት ካልተጠቀሙ እስራኤል የበለጠ ጥቃት ታደርሳለች።

እስራኤል ሊባኖስ ላይ የእግረኛ ጦር ወረራ ልትፈጽም እንደምትችል አስታውቃለች።

የእስራኤል አጋር የሆኑ የምዕራባውያን አገራት ዲፕሎማቶች ነገሮችን ማረጋጋት ስለሚፈልጉ እስራኤል የዲፕሎማሲ መፍትሄን እንድትቀበል እየጠየቁ ነው።

ከዳር ሆነው ነገሮችን እየተመለከቱ ሲሆን፣ አቅም አልባነትም ይስተዋልባቸዋል።