ሩሲያ ከኼርሶን ስትወጣ ዩክሬን ከፍተኛ ድል አስመዝግባለች

የዩክሬን ጦር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

ሩሲያ በደቡብ አቅጣጫ ከምተገኘው ከተማ ለቃ መውጣቷን ተከትሎ የዩክሬን ጦር በኼርሶን አካባቢ ትልቅ ስኬት ማግኘቱን ተናግሯል።

የዩክሬን ወታደሮች ከኼርሶን በስተሰሜን አቅጣጫ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ስኒሁሪቭካ የተባለች ቁልፍ ከተማን ተቆጣጥረዋል።

ኪዬቭ በኬርሶን አቅራቢያ ባሉ ሁለት ግንባሮች ላይም ወደ ፊት እየገፋች እንደሆነ አስታውቃለች። 

ሂደቱ ሳምንታትን ሊፈጅ ቢችልም ሩሲያ ከከተማዋ ለቃ መውጣት መጀመሯን ተናግራለች። 

የመውጣት እርምጃው ለሩሲያ በጦርነቱ እንደ ትልቅ ውድቀት ታይቷል። የዩክሬን ባለስልጣናት ወጥመድ ሊሆን ይችላል በሚል ጥርጣሬ ገብቷቸዋል። 

ከፍተኛ መጠን ያለው የሩሲያ ጦር ከኼርሶን ለቆ ስለመውጣቱ ምንም ማስረጃ የለም።

የዩክሬን ዋና አዛዥ ቫለሪ ዛሉዝኒ ሐሙስ ዕለት እንደተናገሩት የሩሲያ ጦር መውጣቱን ማረጋገጥም ሆነ መካድ ሳይፈልጉ ጦራቸው ጠቃሚ ድሎችን ማስመዝገቡን ተናግረዋል።

ጄኔራል ዛሉዚኒ እንዳሉት ወታደሮቻቸው በዲኒፕሮ ወንዝ ምዕራባዊ ዳርቻ በሚገኙ ሁለት ግንባሮች ወደ ፊት መጓዝ ችለዋል።  

ሰባት ኪሎ ሜትር ወደ ፊት መግፋት የተቻለወ "ባለፈው ቀን" ሲሆን ወታደሮቹ በሰሜን-ምስራቅ እና በምዕራብ አቅጣጫ ገፍተዋል።

የቪድዮ ምስሎች እንደሚያሳዩት ወታደሮች ስኒሁሪቭካ ከተማ ከገቡ በኋላ የአካባቢው ነዋሪዎች አደባባይ ወጥተው ሲቀበሏቸው ይታያል።

በማይኮላይቭ የሚገኘው የክልሉ አስተዳደር በቴሌግራም የመልዕክቱ "ዛሬ ብዙ የምስራች" አለ ብሎ አስፍሯል።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

ቢቢሲ የወቅቱን የግዛት ድሎች እና ኪሳራዎች በገለልተኛነት ማረጋገጥ አልቻለም። ሪፖርቶቹ የመጡት ግን የዩክሬን ጦር ለሳምንታት ተከታታይ ድሎችን ካስመዘገበ በኋላ ነው።

ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረ በኋላ በሩሲያ እጅ የወደቀ የመጀመሪያው እና ብቸኛዋ የክልል ዋና ከተማ ኬርሶን ነበረች።

ከመስከረም መገባደጃ ጀምሮ በክሬምሊን እንደ ሩሲያ ግዛት ይታይ ነበር። ይህ የሆነው በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነትን ያጣ “ህዝበ ውሳኔ” በዩክሬን በተያዙ አካባቢዎች ከተካሄደ በኋላ ነው።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቴሌቭዥን በተላለፈው መልዕክት ላይ አልተሳተፉም።

የዩክሬኑ ጄኔራል ዛሉጂኒ እንዳሉት ሩሲያ የአቅርቦት መስመሮቿ ወድመው እና የዕዝ ሰንሰለቷ ከተስተጓጎለ በኋላ ነው ከመሸሽ ውጪ ምንም አማራጭ የላትም።

ሐሙስ ዕለት የዩክሬን መከላከያ ሚኒስትር እንዳስታወቀው ሩሲያ ለቃ ለመውጣት ቢያንስ አንድ ሳምንት እንደሚፈጅባት እና የጠላታቸውን ድርጊት መተንበይ ቀላል እንዳልሆነም ተናግረዋል ።

የምዕራባውያን ሀገራት ወታደራዊ ጥምረት የሆነው ኔቶ ኃላፊ የንስ ስቶልተንበርግ እንዳሉት ሩሲያ ከባድ ጫና ውስጥ መሆኗ ግልፅ ቢሆንም "በመሬት ላይ ያለው ሁኔታ ምን እንደሚፈጠር" ማየት አስፈላጊ ነው።

የዩናይትድ ኪንግደም የመከላከያ ኃላፊ በበኩላቸው ሩሲያ ከዲኒፕሮ ወንዝ ማዶ ላይ የኮንክሪት ምሽጎችን በመጠቀም የመከላከያ መስመር እያዘጋጀች ይመስላል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡት ቤን ዋላስ "ሩሲያ የዘረፈችውን ንብረት መልሳ ስለሰጠች ዓለም አመስጋኝ መሆን የለበትም" ብለዋል።

የዩክሬን ፕሬዝዳንት አማካሪ ውጤቱን ለማክበር በጣም ገና ነው ብለዋል። ጠላታቸው በኬርሶን ፈንጂዎችን በመቅበር እና ከሩቅ በመምታት በማሴር ከተማዋን ወደ “ሞት ከተማ” ለመቀየር ይፈልጋል ሲሉ ከሰዋል።

በአንድ የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ጄኔራል የቅርብ ጊዜ ግምት መሠረት በሁለቱም ወገን 100,000 ወታደሮችን ሲገደሉ  40,000 ያህል ሠላማዊ ሰዎችም ህይወት አልፏል።