ቼልሲ አሰልጣኙን ቶማስ ቱህልን አሰናበተ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ታትሟል
የእንግሊዙ ፕሪሚየር ሊግ ክለብ ቼልሲ አሰልጣኙን ቶማስ ቱህልን አሰናበተ።
አሰልጣኝ ቱህል የተሰናበቱት በ2022/23 የውድድር ዓመት በመጀመሪያ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ከተሸነፉ በኋላ ነው።
የጀርመናዊው አሰልጣኝ ቡድን ቼልሲ ትናንት ማክሰኞች ጳጉሜ 2/2014 ዓ.ም. ወደ ክሮሺያ ተጉዞ በዳይናሞ ዛግሬብ 1 ለ 0 ተሸንፏል።
አሰልጣኙ በቼልሲ ቆይታቸው ቻምፒንስ ሊግ፣ ሱፐር ካፕ እና የክለቦች የዓለም ዋንጫን ማንሳት ችለዋል።
ክለቡ የቱህልን መሰናበት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ለቼልሲ አዲስ አሰልጣኝ እስኪሰየም ድረስ የልምምድ እና ወደፊት የሚካሄዱ ጨዋታዎች ዝግጅትን የክለቡ አሰልጣኞች ቡድን ይመራዋል ብሏል።
ቱህል 100ኛ የቼልሲ ጨዋታቸውን ነበር ትላንት ምሽት ያከናወኑት።
ባለፉት 7 ጨዋታዎች ሦስቱን አሸንፈው በአንዱ አቻ ሲለያዩ በቀሪዎቹ ተሸንፈዋል።
ቡድኑ በመጪው ቅዳሜ ከፉልሃም ጋር ይጫወታል።












