የኬንያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቀድሞ ውጤት መወሰን ‘በወንጀል የሚያስጠይቅ' ይሁን አለ

ታትሟል

የኬንያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውጤትን ወስኖ ወደ ሜዳ መግባት በወንጀል የሚያስጠይቅ ሕግ እንዲወጣ የአገሪቱን ፓርላማ ጠየቀ።

ፌዴሬሽኑ ይህንን ጥያቄ ያቀርበው በዚህ ዓመት በርካታ ተጫዎቾችና የቡድን አመራሮች ከጫወታ በፊት ወደ ሜዳ ከመግባት (ማች ፊክሲንግ) ጋር በተያያዘ ከታጋዱ በኃላ ነው።

የኬንያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኒክ ሞዎንዳ ውጤት ማጭበርበርን የሚመለከት ሕግ በአገሪቱ አለመኖሩ እንዲህ አይነት ጥፋቶች እንዲበራከቱ ምክንያት ሆኗል።

“ፌዴሬሽኑ እርምጃ መውሰድ የሚችለው የኛ አባል በሆኑና ውጤት ቀደመው በሚወሰኑ ላይ ብቻ ነው። ይህ ብቻውን በቂ አይደለም” ሲሉም አክለዋል።

ኃላፊው ለኬንያ ፓርላማ የስፖርትና ባሕል ኮሚቴ ሪፖርት ሲያቀርቡ “የጨዋታ ውጤት ቀድሞ በመወሰን ተጠርጥረው የታሰሩበት ሰዎች የሚዳኝ ሕግ ባለመኖሩ ክሱ ይዘጋል። ስለዚህ ችግሩ እንዲቆም ሰዎች መታሰርና መቀጣት አለባቸው” ብለዋል።

ሞዎንዳ ፌዴሬሽኑና ክለቦች ያለባቸው የገንዘብ ችግር የጨዋታ ውጤት ቀድሞ እንዲወሰን የሚፈልጉ ቡደኖች እጅ ላይ በቀላሉ እንዲወድቁ ያደርጋቸዋልም ብለዋል።

በዚህ ሳቢያ የኬንያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከታገደ በኃላ ችግሩ ስር እንደሰደደ የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ ቀድመው ውጤት የሚወሰኑት አከላት የሕግ ክፍተት መኖሩን እንደ እድል እየተጠቀሙበት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

እግር ኳስ በዚህ መልክ ሲጭበረበር ተመልካቾችን ያጣል ያሉት ኃላፊው “ውጤትን ቀድሞ መወሰን ለእግር ኳስ ብሎም ለስፖርት ኢንዱስትሪው አደጋ መሆኑ ግለጽ ነው” ሲሉ አክለዋል።

የእግር ኳስ ውጤትን ጨዋታው ከመከናወኑ በፊት ወስኖ ከመግባት ጋር በተያያዘ የኬንያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 18 ተጫዎቾችን እና 7 የቡድን አመራሮችን በድምሩ 25 ሰዎች አግዷል።

የፓርላማ አባሉና የኮሚቴው ሊቀመንብር ዳንኤል ዋንያማ ቀድሞ የጨዋታ ውጤትን የሚወስኑ ሰዎችን ለመቅጣት ሕግ መርቀቅ እንዳለበት እስማማለሁ ብለዋል።

“እንረዳችኋለን። ውጤት ቀድሞ መወሰንን ወንጀል የሚያደርግ ሕግ እንዲወጣ እንረዳለን። በዚህም ምክንያት አጥፊዎች ተከሰው ይታሰራሉ” ሲሉ ተናግረዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ በ2019 ፊፍ የ2010 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያን ጨምሮ በርካታ አለም አቀፍ ጨዋታዎች እንደተጭበረበረ በመግለጽ የተሟላ ምርመራ እንዲካሄድ ጠይቆ ነበር።

የቀድሞ የኬንያ እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን አምበልና የቶተንሃም ሆስፐር አማካኝ ቪክተር ዋንያማ ውጤትን ማጭበርበር እስካልተስተካከለና “ሙያዊ እስካልሆ ድረስ” የኬንያ ብሄራዊ በድን እገዳ መነሳት ላይ አልስማም ሲል ለቢቢሲ ስፖርት ገልጸ ነበር።