አርሰናል ከማንቸስትር ሲቲ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

ሀላንድ እና ጋብርኤል ማጋሌዥ
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ

የ24ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ቅዳሜ፣ እሑድ እና ሰኞ እንዲካሄዱ መርሃ ግብር ወጥቶላቸዋል።

በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ በኤሚሬትስ ስታዲም አርሰናል የአምናው ሻምፒዮና ማንቸስተር ሲቲን ያስተናግዳል።

አርሰናል በዋንጫ ፉክክሩ ለመቆየት፤ ማንቸስተር ሲቲ ደግሞ ከውጤት ቀውስ መውጣቱን ለማረጋገጥ ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል።

የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን ይህንን ጨምሮ ቀሪዎቹን የፕሪሚየር ሊጉን ጨዋታዎች ውጤት እንደሚከተለው ገምቷል።

ቅዳሜ

ኖቲንግሃም ፎረስት ከብራይተን

ፎረስት በጥሩ አቋም ላይ ቢሆንም የካሉም ሃድሰን-ኦዶይ አለመኖር ቡድኑን ይጎዳዋል።

ብራይተን በዘንድሮው ውድድር ዓመት ተገማች ቡድን ሊሆን አልቻለም።

ቡድኑ ከደረጃ ሰንጠረዡ አጋማሽ በላይ ቢቀመጠም በውጤት ውጣ ውረድ ውስጥ እያለፈ ነው።

ይህ ጨዋታ በአቻ ውጤት የሚጠናቀቅ ይመስላል።

ግምት፡ 2 – 2

በርንመዝ ከ ሊቨርፑል

ቦርንመዝ ከሊቨርፑል

ሊቨርፑል በመጨረሻው የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ በርካታ ተጫዋቾችን ለማሳረፍ ችሏል።

ቡድኑ በሁሉም አቅጣጫ ለማሸነፍ እየሞከረ በመሆኑ ማረፋቸው ተገቢ ቢሆንም ቦርንመዝም በጥሩ አቋም ላይ ይገኛል።

ቡድኑ ጉዳቶች ቢደራረቡበትም እነ ማንቸስተር ሲቲ፣ አርሰናል እና ኒውካስል ያሉትን ቡድኖች አሸንፏል።

በዚህ ጨዋታም ቦርንመዝ ሦስት ነጥቦችን ይሰበስባል።

ግምት፡ 2 – 1

ኤቨርተን ከሌስተር

ሁለቱም ቡድኖች ባለፈው ሳምንት ማሸነፍ ችለዋል።

ሌስተር ቶተንሃም ላይ ካስመዘገበው ድል በተጨማሪ ጎል አስቆጣሪው ጄሚ ቫርዲ ብቃቱ አብሮት እንዳለ ያስመሰከረበት ጨዋታ ነበር።

ኤቨርተን በጀምስ ታርኮውስኪ እና ጃራድ ብራንትወይት የተከላካይ መስመር ደጀንንት እና በግብ ጠባቂው ጆርዳን ፒክፎርድ ጠንካራ ተከላካይ መስመር ይኖረዋል።

በዚህ ጨዋታም ኤቨርተን አሸንፎ ከወራጅ ቀጠና ለመራቅ ይችላል።

ግምት፡ 1 – 0

ኢፕስዊች ታወን ከሳውዝአምፐተን

ሳውዝአምፕተን የሚፎካከረው በሊጉ ለመቆየት ሳይሆን በአነስተኛ ነጥብ ከሊጉ የወረደ ክለብ ላለመሆን ነው።

ኢፕስዊች ይህንን ጨዋታ ከተሸነፈ መጥፎ ውጤት ሆኖ ይመዘገብበታል።

ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ጨዋታቻው አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ኢፕስዊች ጎል ማስተናገዱ የሚቀር ባይመስልም በሊያም ዴላፕ ድጋፍ ሦስት ነጥቦችን ያሳካል።

ግምት፡ 2 – 1

ኒውካስል ዩናይትድ ከ ፉልሃም

ኒውካስል ዩናይትድ ከፉልሃም

ፉልሃም ለመገመት አስቸጋሪ ቡድን ሲሆን ኒውካስል ግን በዚህ ረገድ የተሻለ ነው።

ባለፈው ሳምንት በቦርንመዝ ከደረሰባቸው ሽንፈት በፊት ያሉትን አምስት ጨዋታዎች በሜዳቸው አሸንፈዋል።

ፉልሃም ማሸነፍ እንደሚችል በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ማሳየት ችሏል።

አሌክሳንደር ኢሳክ እና አንቶኒ ጎርደን በድንቅ አቋም ላይ ስለሚገኙ በዚህኛው ዙር ኒውካስል ያሸንፋል።

ግምት፡ 3 – 1

ዎልቭስ ከአስቶን ቪላ

ጆን ዱራን ድንቅ ብቃቱን ማሳየት በጀመረበት ወቅት ከዓለማችን ምርጡ ሊግ ለቅቆ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመሄድ ከወሰነ አሳዛኝ ይሆናል።

አርሰናል አጥቂው ኦሌ ዋትኪንስን ለመወሰድ መጠየቁም አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬን የሚያስደስት አይሆንም።

ቡድኑ በተከላካይ መስመር ክፍተት ቢኖርበትም ሞርጋን ሮጀርስ በጥሩ አቋም ላይ ይገኛል።

ቪላ ከሻምፒዮንስ ሊግ መልስ ያደረጋቸውን ያለፉትን ስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

ዎልቭስ በተከታታይ አራት ጨዋታዎችን ተሸንፎ 10 ጎሎችን አስተናግዷል።

ግምት፡ 2 – 2

እሑድ

ብሬንትፈርድ ከቶተንሃም

የሚኪ ቫን ደ ቬን መመለስ ጥሩ ዜና ቢሆንም የቶተንሃምን ውጤት ሙሉ ለሙሉ አይቀይርም።

ባለፈው ሳምንት በሌስተር ከደረሰባቸው ሽንፈት በተጨማሪ ካለፉት 11 ጨዋታዎች አምስት ነጥብ ብቻ ነው የሰበሰቡት።

ቡድኑ በዝውውር መስኮቱም እንዲደገፍ አልተደረገም።

ብሬንትፈርድ በዚህ ጨዋታ ሦስት ነጥቦችን ያሳካል።

ብሪያን ምቤሞ እና ዮአን ዊሳ ጎልችን ማስቆጠር ይችላሉ።

ግምት፡ 2 – 1

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ክሪስታል ፓላስ

ማንቸስተር ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ

ማንቸስተር ባለፈው ሳምንት አሳማኝ ባልሆነ መንገድ አሸንፏል። ድሉን በማስቀጠሉ ዙሪያ ግን ጥርጣሬ አለ።

አጥቂው ራስመስ ሆይሉንድ ወደ ጎል አስቆጣሪነት ለመመለስ በተከታታይ መሰለፍ እና ዕድሎቹን መጠቀም ይኖርበታል።

ቡድኑ ምን አይነት ሊሆን እንደሚችል መገመት ብቻ ነው የሚቻለው።

ፓላስ ከነበረው ጥንካሬ አንጻር ባለፈው ሳምንት በሜዳው በብሬንትፎርድ መሸነፉ አስገራሚ ነው።

ግምት፡ 1 – 1

አርሰናል ከ ማንቸስተር ሲቲ

አርሰናል ከማንቸስተር ሲቲ

ሚኬል አርቴታ ለረዥም ጊዜ አጥቂ እንደማይፈለግ ሲያስብ ቆይቶ ባለቀ ሰዓት ዋትኪንስ መጠየቁ አስገራሚ ነው።

የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት ባለመጠየቁ ትንሽ የዘገየ አድርጎታል።

ባለፉት ዓመታት ይህ ጨዋታ የዋንጫውን ማረፊያ የሚወስን ነበረ ሲሆን ዘንድሮ ግን የመድፈኞቹን በዋንጫ ፉክክሩ መቆየት ብቻ ይወስናል።

ሲቲ ባለፉት ሳምንታት እየተሻሻለ ቢሆንም ጎል ማስተናገዱን ቀጥሎበታል።

ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር 2 ለ 2 ቢለያዩም በዚህ ጨዋታ አንድ ቡድን ያሽንፋል።

አርሰናሎች የቆሙ ኳሶችን ከተጠቀሙ ሊገርመን አይገባም።

ግምት፡ 2 – 1

ሰኞ

ቼልሲ ከዌስት ሃም

የቀድሞው የቼልሲ አሰልጣኝ ግርሃም ፖተር ዌስት ሃምን ይዘው ወደ ብሪጅ የሚመለሱበት ጨዋታ ይሆናል።

ዌስት ሃም ከአስልጣኙ መሾም በኋላ ጥሩ መንቀሳቀስ ቢችልም ውጤት ግን አሁንም ርቆታል።

ቼልሲ ተፎካካሪ ለመሆን ግብ ጠባቂ እና አጥቂ ያስፈልገዋል። እንዲህም ሆኖ ጨዋታውን በበላይነት ያጠናቅቃል።

ግምት፡ 2 - 1