ከሜዳው ውጪ የሚጫወተው ሊቨርፑል እንዴት ይሆናል?

አርሴናል ከክሪስታል ፓላስ
ታትሟል

አርሰናል በፈረንጆቹ ገና የፕሪሚር ሊጉ መሪ መሆን ችሎ ነበር።

መድፈኞቹ ሳይጠበቅ ቀጥሎ ባደረጓቸው ሁለት ጨዋታዎች በዌስት ሃም እና በፉልሃም ተሸንፈዋል።

“ለዋንጫ ያላቸውን ተስፋ ለማስጠበቅ በፓላስ መሸነፍ አይኖርባቸውም” ይላል የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን።

“ጨዋታውን ማሸነፍ አርሰናል ከሊቨርፑል ላለመራቅ ብቻ ሳይሆን ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ፉክክሩን የሚያጠናክረበት ነው።”

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት 5 ጨዋታዎች ባለፈው ሳምንት ተከናውነዋል። ቀሪዎቹ ጨዋታዎች ደግሞ ቅዳሜ፣ እሑድ እና ሰኞ ይከናወናሉ።

ሱተን በዚህ ሳምንትም የሊጉን ጨዋታዎች ግምት እንደሚከተለው አስቀምጧል።

ቅዳሜ

አርሰናል ከ ክሪስታል ፓላስ

ከማንቸስተር ሲቲ ጋር እንዳደረጉት ሁሉ ሮይ ሆድሰን በመከላከል እየተጫወቱ በመልሶ ማጥቃት ጎል ለማስቆጠር ይሞክራሉ።

በዚህ መንገድ አርሰናልን መፈተን ቢችሉም ዋናው ነገር መድፈኞቹ የፓላስን ተከላካይ መስመር የማለፍ ብቃት ነው።

ባለፉት ጨዋታዎች ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረው የማይክል አርቴታ የአጥቂ መስመር ለዚህ ችግር መፍትሔ ሊኖረው ይገባል።

አርሰናል በዋንጫው ፉክክር እንዲቀጥል እንደዚህ ያሉ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ይገባዋል።

ግምት፡ 2 – 0

ውጤት፡ 5 - 0

ብሬንትፈርድ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት
የምስሉ መግለጫ, ብሬንትፈርድ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

ብሬንትፈርድ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

ከስምንት ጨዋታዎች ሦስት ነጥብ ብቻ ያሳኩት ንቦቹ፤ በዚህ ጨዋታ ከስምንት ወራት ቅጣት በኋላ ኢቫን ቶኒን ማግኘታቸው ተስፋ ይሰጣቸዋል።

ቶኒ በሁለተኛው ቡድን እና በዝግ ጨዋታዎች ጎል ማስቆጠሩ የተነገረ ሲሆን ይህንን ለዋናው ቡድን እንደሚደግመው ይጠበቃል።

ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች ያሸነፉት ፎረስቶች በፋይናንስ ሕግ ጥሰት የቀረበባቸው ክስ የሚያስከትለው ቅጣት ያሳስባቸዋል።

ስለዚህ ሁለቱም ቡድኖች ይህንን ጨዋታ ለማሸነፍ ምክንያት አላቸው።

ግምት፡ 2 – 1

ውጤት፡ 3 - 2

እሑድ

ሼፊልድ ዩናይትድ ከ ዌስት ሃም

በቅርቡ የተሾሙት የሼፊልድ ዩናይትዱ አሰልጣኝ ክሪስ ዋይልደር ከተጫዋቾቻቸው ጋር በቂ ጊዜ ማግኘት አልቻሉም።

ቡድኑ ጎል የማስቆጠር ችግሩን ለመቅረፍ ቤን ብሬሬተን ዲያዝን በውሰት ከቪላሪያል አስፈርመዋል።

ዌስት ሃሞች ከኤፍኤ ዋንጫ ውጭ ቢሆኑም በዚህ ጨዋታ ይሸነፋሉ ብዬ አላስብም።

ሁለቱም ኳስ ይዘው መጫወትን የሚመርጡ ቡድኖች አይደሉም። ጨዋታው በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል።

ግምት፡ 1 – 1

ቦርንመዝ ከ ሊቨርፑል
የምስሉ መግለጫ, ቦርንመዝ ከ ሊቨርፑል

ቦርንመዝ ከ ሊቨርፑል

ማንቸስተር ሲቲ ያለ ኤርሊንግ ሃላንድ እንዴት እንደሚጫወት አይተናል። በተመሳሳይ ሊቨርፑልም ያለ ሞሐመድ ሳላህ ምን እንደሚመስል የምንመለከትበት ጨዋታ ነው።

ትሬንት አሌክሳንደር-አርኖልድን በጉዳት ያጡት ሊቨርፑሎች የሚፈተኑበት ጨዋታ ይሆናል።

አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ በጊዜ ሂደት መገንባት የሚፈልጉትን ቡድን እያየን ነው።

በርካታ ዕድል ከፈጠሩበት የቶተንሃም ሽንፈት በፊት ካደረጓቸው ስምንት ጨዋታዎች ሰባቱን አሸንፈው አንዱን አቻ ተለያይተዋል።

ግምት፡ 1 – 1

ሰኞ

ብራይተን ከ ዎልቭስ
የምስሉ መግለጫ, ብራይተን ከ ዎልቭስ

ብራይተን ከ ዎልቭስ

ይህ ለመገመት ከባድ የሆነ ጨዋታ ነው።

ብራይተኖች የባለፈው ዓመት አቋማቸው ላይ ባይደርሱም አሁን ጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ዎልቭሶች ያሉትን ሦስት ጨዋታዎች ከማሸነፋቸውም በላይ ጎል የማስቆጠር ብቃታቸውም ጥሩ ነው።

ብራይተን በሜዳው በመጫወቱ ግምቱን ቢወስድም ይህ ጨዋታ አቻም ሊጠናቀቅ ይችላል።

ግምት፡ 2 – 1