ዋትስአፕ በመላው ዓለም ተቋርጦ እንደነበር ተገለጸ

የዋትስአፕ አርማ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

ዋትስአፕ የተሰኘው የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያ በመላው ዓለም ተቋርጦ እንደነበር ተገለጸ።

የፌስቡክ ባለቤት በሆነው ሜታ ስር የሚተዳደረው ዋትስአፕ 4፡00 ሰዓት ገደማ ላይ መቋረጡ ታውቋል።

በግማሽ ሰዓት ውስጥም ከ12 ሺህ በላይ ሪፖርቶች መመዝገባቸውንም ዳውን ዳይሬክተር ተባለው ድረ ገጽ አስታውቋል።

ብዙዎችም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መልዕክት መላክም ሆነ መቀበል እንዳልቻሉ በመግለጽ ቅሬታቸውን አስፍረዋል።

ዋትስአፕ ወደ ሁለት ቢሊዮን የሚጠጉ ቋሚ ተጠቃሚዎች አሉት።

ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በተለያዩ ሃገራት ቀዳሚው የመልዕክት መላላኪያ መድረክ ነው።