በዛንዚባር የተመረዘ የውሃ ኤሊ ስጋ የበሉ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
በታንዛኒያ ፔምባ ደሴት የተመረዘ የውሃ ኤሊ ስጋ የበሉ የሦስት ዓመት ህጻንን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ።
ሌሎች ሦስት ሰዎች ደግሞ በሆስፒታል ህክምናቸውን እየተከታሉ ይገኛሉ።
በደሴቲቲቷ ነዋሪዎች ዘንድ ስጋው የተለመደ ምግብ ነው። ነገር ግን አሁን ባለሥልጣናቱ በአካባቢው ኤሊዎችን መመገብ ከልክለዋል።
አልፎ አልፎ የውሃ ኤሊ ሥጋ 'በኬሎኒቶክሲዝም' በመባል በሚታወቅ የምግብ መመረዝ ምክንያት መርዛማ ሊሆን ይችላል።
ትክክለኛው መንስኤው በውል ባይታወቅም የውሃ ኤሊዎቹ ከሚመገቡት መርዛማበምጥ ላይ የነበሩት የኒውዚላንዷ የፓርላማ አባል ሳይክላቸውን ነድተው ሆስፒታል ደርሰው ወለዱ አልጌ ጋር የተያያዘ ነው ተብሎ እንደሚታሰብ የተርትል ፋውንዴሽን የተባለ የበጎ አድራጎት ድርጅት ገልጿል።
ከፊል የራስ ገዝ በሆነው የዛንዚባር ደሴቶች አካል በሆነው በፔምባ ቢያንስ አምስት ቤተሰቦች የውሃ ኤሊ ስጋውን ባለፈው ሐሙስ በልተዋል ሲሉ የአካባቢው ፖሊስ አዛዥ ጁማ ሰኢድ ሃሚስ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ምልክቶቹ መጀመሪያ የታዩት በማግስቱ ሲሆን የሦስት ዓመቱ ልጅ መጀመሪያ ህይወቱ አለፈ። በዚያው ምሽት ሌሎች ሁለት ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች አራት ሰዎች ደግሞ እሁድ ህይወታቸው አልፏል።
ተጨማሪ 38 ሰዎች ሆስፒታል የገቡ ቢሆንም አብዛኞቹ ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። የቀሩት ሦስት ሰዎች ግን በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል።
የዛንዚባሩ ፕሬዝዳንት ሁሴን ምዊኒ በትዊተር ገጻቸው ለተጎዱ ቤተሰቦች ሃዘናቸውን አስተላልፈዋል።
ጉዳቱ በልጆች እና በእድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የከፋ ተጽዕኖ ሊያመጣ ቢችልም ጤናማ ጎልማሶችም ሊገድል ይችላል ሲል ተርትል ፋውንዴሽን ይናገራል።
በማዳጋስካር ባለፈው በመጋቢት ዘጠኝ ህጻናትን ጨምሮ 19 ሰዎች የውሃ ኤሊ ስጋ በልተው መሞታቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
በኢንዶኔዥያ፣ በማይክሮኔዥያ እና በህንድ የህንድ ውቅያኖስ ደሴቶችም ተመሳሳይ ጉዳዮች ተዘግበዋል።












