ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ከሬሣ ሳጥን ጌጣጌጥ የሰረቁት ፈረንሳዊት በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ሰሜናዊ ፈረንሳይ ውስጥ ነው። አንድ የመቃብር ሥፍራ ላይ።
አንድ ቤተሰብ ሃዘን ላይ ተቀምጧል። ለቅሶ ደራሽ ይጎርፋል። ዘመድ አዝማድ ሟችን ለመሰናበት ይመጣል።
በዚህ መሃል ለቤተ ዘመዱ አዲስ የሆኑ አንዲት ሴት ለቅሶ ለመድረስ ፊታቸውን በመሃረብ ሸፍነው ብቅ ይላሉ።
ቤተሰቡ ሴትየዋ አዲስ ብትሆንባቸውም መቸስ ለቅሶ አይደል ብለው ችላ ብለዋል።
ይህንን ቀዳዳ ያገኙት ሴት የሟች የቅርብ ጓደኛ ነኝ ብለው ወደ ሬሣ ሳጥኑ ቀርበው መሃረባቸው እስኪበሰብስ አነቡ።
ነገር ግን ትንሽ ቆይቶ ወደ ሬሣ ሳጥኑ ሰቂርቡ የሟች አንገት ጌጥ፣ ቀለበት እና ሎቲ የለም።
የሟች ቤተሰቦች ወዲያው ለፖሊስ ደውለው ከሬሣ ሳጥን ውስጥ ጌጣጌጥ ተሰርቆብናል ሲሉ አለመከቱ።
ፖሊስ ጉዳዩን ከመረመረው በኋላ በ60ዎቹ ዕድሜ ውስጥ ናቸው ያሏቸውን ሴት መፈለግ ያዙ።
ተጠርጣሪዋ ከሟች መኖሪያ ሰፈር ብዙም ርቀው እንደማይኖሩ የደረሰበት ፖሊስ ሴትዬዋን አፈላልገው የካቴና ሲሳይ አድርገዋቸዋል።
ፖሊስ ተጠርጣሪዋንና ከሰረቁትን ጌጣጌጥ ጭምር ነው በቁጥጥር ሥር ያዋለው።
የፈረንሳይ ፖሊስ ሴትዬዋን በቁጥጥር ሥር ካዋለ በኋላ ከዚያው የመቃብር ሥፍራ ከሚገኝ አንድ ሬሳ የኪስ ቦርሳ መስረቃቸውን ደርሰቦታል።
ሴትዬዋ ቤታቸው ሲበረበር የቅርብ ጊዜያት የሃዘን መግለጫዎች ተገኝተዋል ሲሉ የፈረንሳይ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።