በኢራቅ ከጅምላ መቃብር አፀሞችን ማውጣት ተጀመረ

የፎቶው ባለመብት, EPA
ጅሃዳዊው ቡድን እስላማዊ መንግስት በኢራቅ ካካሄዳቸው ጭፍጨፋዎች እጅግ የከፋ በተባለለት ግድያ ሰለባ የሆኑ የ 123 ሰዎች አፅም በሞሱል አቅራቢያ ከሚገኘው የጅምላ ተቆፍሮ ወጣ ።
ከሟቾች የቅርብ ዘመዶች በሚወሰድ የዲኤንኤ ቅንጣት ምርመራዎች የሟቾችን ለመለየት ይረዳልም ተብሏል።
እነዚህ የጥቃቱ ሰለባዎች ባዶሽ በተባለው እስር ቤት ውስጥ ታስረው ከነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የሺዓ ሙስሊም እስረኞች መካል እ.ኤ.አ. በ 2014 ከተገደሉት ከ 600 በላይ እስረኞች መካከል ናቸው ።
የአይ ኤስ ታጣቂዎች በቅድሚያ እስር ቤቱን በማቃጠል እና አብረዋቸው ሱኒዎችን ነፃ ካወጡ በኋላ የሺዓ ሙስሊሞቹን ወደ አንድ ገደል በመኪና በመውሰድ በጥይት እንደገደሏቸው ተዘግቧል።
ቡድኑ በአንድ ወቅት ከምሥራቅ ኢራቅ እስከ ምዕራብ ሶሪያ ድረስ የተዘረጋ 88,000 ስኩየር ኪ.ሜ መሬት ተቆጣጥሮ ወደ ስምንት ሚሊዮን በሚጠጉ ሰዎችን በአሰቃቂ አገዛዝ ስር ያስተዳድር ነበር ።
አካባው ነፃ ሲወጣ መውጣት በቡድን ያደረሱትን በደሎች መጠን ያጋለጠ ሲሆን ይህም ያለ ፍርድ የሚፈፀም ግድያ፣ ማሰቃየት ፣ የአካል መቆረጥ ፣ ብሔር ተኮር ጥቃቶች እንዲሁም የሴቶች እና የሴቶች ልጆች አስገድዶ መድፈር እና ወሲባዊ ባርነትን ያጠቃለለ ነበር።
በኢራቅ እስካሁን ድረስ 12 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን አስከሬን የያዙ ከ 200 በላይ የጅምላ መቃብር ስፍራዎች መገኘታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።
ድርጅቱ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረትም አይኤስ የጦር ወንጀሎችን ፣ በሰብአዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን እና የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ሊያስከትሉ የሚችሉ ድርጊቶችን መፈጸሙን ድምዳሜ ላይ ደርሷል።
‹‹ለ 17 አመታ ያህል ልጄ በህይወት ይኑር ወይም የሙት አላውቅም። አሁን መልስ እፈልጋለሁ›› ሲሉ አባስ መሃመድ የተሰኙ ልጃቸው በባዶሽ በ 2005 ታስሮባቸው የነበረ አባት ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል ተናግረዋል።
በባግዳድ የፎረንሲክ ክፍል ውስጥ የጅምላ መቃብር ምድብ ሃላፊ የሀኑት ዶ/ር ያስሚን መንዘር በመዲናዋ ብቻ ባለፈው ሳምንት 100 ቤተሰቦች የደም ናሙና እንደሰጡና በአራት ደቡባዊ አውራጃዎችም በርካቶች ናሙና መስጠታቸውን ተናግረዋል።
ሆኖም የሟቾች ማንነት የመለየት ሂደት ከመጀመሩ በፊት ሌሎች አምስት አውራጃዎች ናሙና መውሰድ እንዳለባቸው አሳስበዋል












