ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
በጣሊያን ለ15 ዓመታት በሥራ ገበታው ሳይገኝ ደመወዝ 'ሲበላ' የነበረ ግለሰብ ተያዘ
ታትሟል
በጣሊያን በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ተቀጥሮ በ15 ዓመታት ውስጥ አንድም ቀን ወደ ሥራው 'ዝር ሳይል' ደመወዝ 'ሲበላ' የነበረው ተቀጣሪ ላይ ክስ ሊመሰረት እንደሆነ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ሰውየው ሥራ ባልተገኘባቸው አመታት የተከፈለው ጠቅላላ ገንዘብ 538 ሺህ ዩሮ ወይም በወቅታዊ ምንዛሬ ከ26 ሚሊዩን ብር በላይ እንደሆነ ተነግሯል።
ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ የሆስፒታሉ ስድስት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።
የሕዝብ ሀብት ላይ የሚደረጉ ማጭበርበሮችን በተመለከተ ፓሊስ በደረገው ዘለግ ያለ ምርመራ ነው ተጠርጣሪዎቹ ተደርሶባቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት።
በመንግሥት ሆስፒታል ተቀጥሮ የነበረው ግለሰቡ በሥራው ላይ የተመደበው እንደ አውሮፓውያኑ በ2005 ነው።
ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ወደ ስራ መሄድ አቆመ። ከዛ በኃላ ለቀጣዩቹ 15 አመታት ከሥራ ቦታው ጋር አልተያየም።
የተቀጣሪው አለቃ የሥነ ምግባር ጥሰት እንደፈፀመ ሪፓርት እንዳታደርግ ሲያስፈራራት እንደነበረም ተጠቁሟል።
እሷ ጡረታ ስትወጣ የእሷ ተተኪም ይሁን የሆስፒታሉ የሰው ሀብት ክፍል ጉዳዩ ላይ ምንም መረጃ እንዳልመበራቸው ተዘግቧል።