ኮሮናቫይረስ፡ የጉንፋን ቫይረስ ኮቪድ-19ን ማሸነፍ ይችል ይሆን?

የምትናፈጥ ሴት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

ጉንፋን የሚያሲይዙ ቫይረሶች የኮቪድ ቫይረስን ከሰውነት ውስጥ ማስወጣት ይችላሉ ይላሉ አጥኚዎች።

አንዳንድ ቫይረሶች ሰውነታችን ላይ ጉዳት ለማድረስ ፉክክር ከእኩዮቻቸው ጋር ፉክክር ያደርጋሉ።

የግላስጎው ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከሆነ ጉንፋን የሚያስከትለው ሪኖቫይረስ ኮሮናቫይረስን ይረታል።

ነገር ግን ጥቅሞቹ ቆይታቸው አጭር ሊሆን ይችላል፤ ቢሆንም ኮሮናቫይረስ በሰፊው የሚሰራጭ ስለሆነ ኮቪድን መፎካከሩ አይቀርም ነው የሚሉት አጥኚዎቹ።

አፍንጫችሁ፣ ጉሮሮዋችሁ አሊያም ሳንባችሁ ውስጥ ያሉ ሴሎችን በሥርዓቱ አንደተሰደሩ ቤቶች ውሰዷቸው። ቫይረሱ አንዴ ወደ ውስጥ ከገባ በኋላ በሩን ከፍቶ ሌሎች ቫይረሶች እንዲገቡ ያደርጋል አሊያም በሩን ዘግቶ ብቻውን መኖር ይጀምራል።

ኢንፍሉዌንዛ በጣም ራስ ወዳድ ከሚባሉ ቫይረሶች አንዱ ነው። ይህ ቫይረሱ ብዙ ጊዜ ብቻውን ነው ሰውነታችን ላይ ጉዳት የሚያደርሰው። ሌላ ቫይረስ አያስጠጋም።

እንደ አዴኖቫይረስ ያሉ ተዋህሲዎች ግን ሌሎች ቫይረሶችን ማስጠፋት ይወዳሉ።

ሳርስ-ኮቭ-2 የተሰኘው ቫይረስ ነው ኮቪድን የሚያመጣው። ይህ ቫይረስ ከሌሎች ቫይረሶች ጋር ተቀላቅሎ መኖር ይችላል።

ሳይንቲስቶች አሁን ነገሮችን ያከበደባቸው ምክንያት ማሕበራዊ ርቀት ነው። በማሕበራዊ ርቀት ምክንያት ጉንፋንን የመሳሰሉ ቫይረሶች ከሰው ሰው መዛመታቸውን ለጊዜው ገታ አድርገዋል።

አጥኚዎቹ ኮሮናቫይረስና ሪኖቫይረስ አንድ ላይ አድርገው በማኖር በጋራ መዝለቅ ይችሉ እንደሆን ለመለየት ሙከራ አድርገዋል።

ኮሮናቫይረስና ሪኖቫይረስ በአንድ ጊዜ ከተለቀቁ ጉንፋን አምጪው ሪኖቫይረስ ይረታል። ሪኖቫይረስ ከኮሮናቫይረስ 24 ሰዓት ቀድሞ ከገባ ኮሮናቫይረስ ጭራሽ ድርሽ አያደርገውም።

ኮሮናቫይረስ ቀድሞ ገብቶ ሪኖቫይረስ 24 ሰዓታት ዘግይቶ ቢገባ እንኳ ኮሮናቫይረስን ማስወጣት ይችላል።

በፈረንጆቹ 2009 የተከሰተውን የስዋይን ፍሉ ወረርሽኝ አውሮፓ ውስጥ ቀዝቀዝ ያደረገው በተመሳሳይ ወቅት ተከስቶ የነበረው ሪኖቫይረስ እንደሆነ ይገመታል።

ሌሎች ጥናቶች ደግሞ እንደሚያመላክቱት ሪኖቫይረስ የተጠቁ ሴሎች የመከላከል አቅማቸው እንዲጎለብት ያደርጋል። ይህ ደግሞ ኮሮናቫይረስ እንዳይዛመት ያደርገዋል።

ነገር ግን ኮሮናቫይረስ የክረምቱ ወራት ካለፈ በኋላና የመከላከል አቅም ከተዳከመ ተመልሶ ሊመጣ ይችላል።

ወደፊት የሚመጡ የክረምት ወራት ምን ዓይነት ተፅዕኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ ከአሁኑ መገመት ያዳግታል።

ኮሮናቫይረስ ወደፊትም ቢሆን ስርጭቱን ሊቀጥል እንደሚችል እሙን ነው። ሌሎች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ጠፍተው የነበሩ ቫይረሶችም ብቅ ብቅ ማለታቸው አይቀርም።

ለዚህ ነው ተመራማሪዎቹ አሁንም የአፍና አፍንጫ ጭምብል መጠቀም ዋነኛ መላ ነው የሚሉት።