'ጥቁርነት ውበት ነው' የተሰኘው እንቅስቃሴ የተወለደባት ከተማ

ጥቁር ሞዴል
ታትሟል

አንድ ፎቶግራፈር፤ በርካታ ሞዴሎች እና የፋሽን ትርዒት አሁን ዓለምን የናኘውን የባሕልና ፖለቲካ እንቅሳቃሴ ወለዱ።

በአውሮፓውያኑ ጥር 1962 ፐርፕል ማኖር ከተሰኘው የምሽት ክበብ ፊት ብዙ ሰዎች ተሰልፈዋል።

ቦታው ኒው ዮርክ ከተማ ሃርለም አካባቢ።

ክበቧ የፋሽን ትርዒት እያሰናዳች ነው። ትርዒቱ በጣም ከመወደዱ የተነሳ በአንድ ምሽት ለሁለተኛ ጊዜ ነበር የተዘጋጀው።

ይህ የፋሽን ትርዒት ጥቁሮች ውበታቸው ጀነን ብለው እንዲያንፀባርቁ የተዘጋጀ ነበር።

እነሆ ይህ የፋሽን ትርዒት 'ብላክ ኢዝ ቢውቲፉል' [በግርድፍ ትርጉሙ 'ጥቁርነት ውበት ነው'] የተሰኘውን እንቅስቃሴ ወለደ።

'ናቹራሊ 62' የተሰኘውን ትርዒት ላይ ፎቶ ሲያነሱ የነበሩት ወንድማማቾቹ ክዋሜ ብሬዝዋይትና ኢሎምቤ ብራዝ ናቸው።

ክዋሜ አሁን 82 ዓመቱ ነው። ወንድሙ ግን 2014 ላይ አልፏል።

ትርዒቱ ጥቁር ሴቶች የምዕራባውያንን የውበት ልኬት እርግፍ አድርገው ትተዋል።

በፋሽን ትርዒቱ ቀይ ምንጣፍ ላይ የተራመዱት ሴቶች አፍሯቸውን አበጥረው ከሌጎስ፣ አክራና ናይሮቢ በተውጣጡ ልብሶች አጊጠው ታይተዋል።

ሴቶቹ 'ግራንዳሳ ሞዴል' ይባላሉ።

ትርዒቱ የሴቶቹን ውበት ከማሳየት ያለፈ ዓላማ ነበረው።

ከዚህ የፋሽን ዐውደ ርዕይ በኋላ ነው 'ጥቁርነት ውበት ነው' የሚለው እንቅስቃሴ መስፋፋት የጀመረው። ይህ እንቅስቃሴ በ60ዎቹና 70ዎቹ ብዙዎችን አዳርሷል።

የመጀመሪያዎቹ የግራንዳሳ ሞዴሎች የማርከስ ጋርቬይ ርዕዮተ ዓለም ተከታዮች ናቸው።

የክዋሜ ፎቶዎች ታሪካዊ ናቸው። ፎቶዎቹ ላይ ወጣት ሴቶች በተፈጥሯዊ ውበታቸው ደምቀው ይታያሉ።

ክዋሜ ከ1950ዎቹ ጀምሮ እስከ 70ዎቹ ድረስ ስቲቪ ዎንደርና ቦብ ማርሊን ጨምሮ በርካታ ታዋቂ ጥቁር አርቲስቶችን ፎቶ አንስቷል።

የእሱ ፎቶዎች ጥቁርነት ውበት ነው ለተሰኘው እንቅስቃሴ ከባድ ውለታ ውለዋል።

ክዋሜና

የፎቶው ባለመብት, Philip Martin Gallery

የምስሉ መግለጫ, ክዋሜ

ክዋሜና አጋሮቹ ጥቁር ሴቶችና ወንዶች በውስጣዊና ውጫዊ ውበታቸው እንዲኮሩና በማርከስ ጋርቬይ አስተምህሮት እንዲጓዙ ይመክራሉ።

የጥቁር ሰዎች መብት ተመጓጋች የነበረው ጋርቬይ ጥቁሮች በሕብረ-ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ራሳቸውን እንዲችሉ ይመክር ነበር።

ክዋሜ ከአጎቱ በተደበረው ካሜራ ነው ፎቶ ማንሳት የጀመረው። ገና የ19 ዓመት ለጋ ወጣት ሳለ።

በጊዜው ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር በመሆን የጃዝ ሙዚቃ ምሽቶችንም ያዘጋጅ ነበር።

"በወቅቱ ጃዝ ማለት የአፍሪካ አሜሪካውያን ሙዚቃ ነበር። ልክ የኔ ትውልድ ሂፕ ሆፕ እንዳለው ሁሉ የዛኔው ትውልድ ሙዘቃ ጃዝ ነበር" የክዋሜ ልጅ።

"ያ ትውድል ነው የሰብዓዊ መብት እንቅስቃሴ የጀመረው።"

ከጆርጅ ፍሎይድ ግድያ በኋላ የጎመራው የብላክ ላይቭስ ማተር [የጥቁሮች ሕይወት ዋጋ አላት] እንቅስቃሴን ተከትሎ ክዋሜ ትንሹ የአባቱን ፎቶ ተጠቅሞ አዲስ እንቅስቃሴ ጀምሯል።

ከሙዚቀኞች ጋር በመተባበር 'እንተነፍሳለን' የሚል ሙዚቃም ሠርቷል።

በየዓመቱ ነሃሴ 17 [በአውሮፓውያኑ] የማርከስ ጋርቬይ ቀን ይከበራል። ሃርለም ከተማም ትደምቃለች።

ኮከቧ ድምፃዊት ኒና ሲሞንን ጨምሮ ሌሎች በርካታ አርቲስቶችም በጊዜያቸውን ይህን ጥቁርነት ውበት ነው የተሰኘውን እንቅስቃሴ ያዜሙ ነበር።

ዘንድሮ ጥቁርነት ውበት መሆኑ በሰፊው ይነገራል፤ ይታያል፤ ይደመጣል።

ፎቶግራፈሮች ደግሞ ይህንን እንቅስቃሴ በሥራዎቻቸው በማንፀባረቅ ቅድሚያውን ይይዛሉ።

ባለፈው ዓመት ሪሃና አዲስ ላቋቋመችው የመዋቢያ ምርቶች ኩባንያ መነቃቃት የሆናት ፎቶግራፈሩ ክዋሜ እንደሆነ ተናግራ ነበር።

የሰውዬው ፎቶግራፎች በርካታ ጥቁሮች ከምዕራባውያን የውበት መሥፈርት ተላቀው ራሳቸውን በተፈጥሯዊ መንገድ እንዲያሳዩ ምክንያት ሆነዋል።

ወደፊትም ከመሆን የሚያግዳቸው ነገር ያለ አይመስልም።