ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበራቸውን ለማስመር ተስማሙ
ታትሟል
ሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ እና አቻቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በሁለቱ አገራት ድንበር ላይ ያለውን ውጥረት አስመልክቶ ማዕክሰኞ እለት በስልክ መወያየታቸውን ሱዳን ኒውስ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡
ሁለቱ መሪዎችም በውይይታቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ድንበር ለመወሰን የባለሙያዎች ቡድን ለማቋቋም ተስማምተዋል ተብሏል፡፡
በቅርቡ ሱዳን ኢትዮጵያ በሱዳን ድንበር በኩል የሚገኘውና በአገሪቷ ትልቁ የእርሻ አካባቢ አል ፋሻጋ የሚገኙ ወታደሮቿን እንድታስወጣ ጥሪ አቅርባለች፡፡
አካባቢው ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር የነበረ ነው፡፡
ከ12 ቀናት በፊት በኢትዮጵያ ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት አንድ የሱዳን ወታደር ሲገደል፤ ሌሎች ሦስት የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸው ተዘግቧል፡፡
ይሁን እንጅ ፕሬዚደንት ኦማር አልበሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ በሁለቱ አገራት መካካል ያለው ግንኙነት እየተሸሻለ መጥቷል፡፡