ኮሮናቫይረስ፡ ኮቪድ-19ን ለመከላከል የበኩላቸውን ያደረጉ አፍሪካዊ ጀግኖች

ሐመልማል አባተ
ታትሟል

አፍሪካዊያን ዓለም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተጨነቀችበትን ይህን ጊዜ በማሰብ፤ ሌሎችን ለመርዳት አስገራሚ በጎ ተግባራት እያከናወኑ ነው። ከእነዚህ ጀግኖች መካከል ስድስቱን እናስተዋውቃችሁ።

መኖሪያ ቤቷን ለለይቶ ማቆያነት የሰጠችው ኢትዮጵያዊት ድምጻዊት

አንጋፋዋ ድምጻዊት ሐመልማል አባተ መኖሪያ ቤቷን ለለይቶ ማቆያነት እንዲውል አበርክታለች። ባለፈው ወር መንግሥት ማንኛውም ወደ አገር ውስጥ የሚገባ ሰው በራሱ ወጪ ራሱን ለ14 ቀናት ያህል በሆቴል ውስጥ ለይቶ እንዲያቆይ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር።

ይህም ድምጻዊቷን ያሳሰበ ጉዳይ ነበር፤ ውሳኔው ገንዘብ ላላቸው የውጭ ዜጎች ይሁን፤ ገንዘብ ለሌላቸውስ በሚል ሀሳብ ገብቷት ነበር። በመሆኑም በአዲስ አበባ የሚገኘውን መኖሪያ ቤቷ ለለይቶ ማቆያ እንዲሆን አበረክታለች።

ሐመልማል ቤታቸውንና የንግድ ቦታቸውን ለለይቶ ማቆያነት ከሰጡ ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዷ ናት።

ከፋሽን ዲዛነርነት የህክምና ገዋን ወደ መስፋት የተሻገሩት ሊቢያዊያን

ሊቢያዊያኑ የፋሽን ዲዛይነር የፋሽን ልብስ ከመስራት ወደ የህክምና ገዋን ማምረት ተሸጋግረዋል።

በሊቢያ መዲና ትሪፖሊ በሚገኘው የፋሽን ልብስ ማምረቻ፤ ስድስቱ ሴቶች ለህክምና ባለሙያዎች የሚሆን ራስን መጠበቂያ አልባሳት መስፋቱን ተያይዘውታል።

ሁሉም ሴቶች በጎ ፈቃደኞች ሲሆኑ አንዳንዴ በሥራ መብዛት ምክንያት እዚያው ፋብሪካው ውስጥ ይተኛሉ።

በጎ ፈቃደኞቹ እስካሁን 50 የሚሆኑ የህክምና አልባሳት የሰሩ ሲሆን ሁለተኛ ዙር ተጨማሪ ለማምረት እየሰሩ ነው።

ኮሮና
Banner

የአረጋዊያን ቤትን በአበባ ያስጌጡት አበባ አምራቾች

ወረርሽኙ በርካታ ሠርጎችና ሌሎች ክንውኖች እንዲሰረዙ ምክንያት ሆኗል። በዚህም ምክንያት የአበባ ምርቶች ከጥቅም ውጪ እንዲሆኑ በማድረግ መጥፎ አሻራ አሳርፏል።

ይሁን እንጅ በደቡብ አፍሪካ ፓርል የሚገኙ አበባ ሻጮች በመሰባሰብ ይህንን ጨፍጋጋ ጊዜ ትንሽም ቢሆን ብርሃን ለመስጠት እየሰሩ ነው።

ከአንድ የአበባ እርሻ የተበረከተላቸውን 600 አበቦች የአዛውንቶችን ቤት የውጪ ግድግዳ እያስጌጡበት ነው።

የደቡብ አፍሪካ ነዋሪዎች ወረርሽኙን ለመከላከል በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ቤታቸው ከከተቱ ሁለት ሳምንታት አልፏቸዋል።

በደቡብ አፍሪካ የአበባ መሸጫ ሰራተኞች የአረጋውያን መቆያን ሲያስውቡ

የፎቶው ባለመብት, Adene's Farm Flowers

የቤት ኪራይ ነጻ ያደረጉ ኬንያዊ ቤት አከራይ

በኬንያ 34 ተከራዮች ያሉት የቤት ባለቤት ተከራዮች መጋቢትና ሚያዚያ ወርን ተከራዮች ኪራይ እንዳይከፍሉ ወስነዋል። ይህን ውሳኔ ያሳለፉት የኮሮናቫረስ ወረርሽኝ በርካቶችን ለገንዘብ ችግር ስለዳረጋቸው ነው ብለዋል።

ማይክል ሙኔኔ የተባሉት እኝህ ባለሃብት በኬንያ ምዕራባዊ ግዛት እያንዳንዳቸው 3 ሺህ የኬንያ ሽልንግ [ከ250 ዶላር በላይ] የሚከፈልባቸው 28 አፓርትመንቶች አሏቸው።

ከዚህም በተጨማሪ በወር 5 ሺህ ሽልንግ የሚከፈልባቸው ስድስት የንግድ ቤቶችም ባለቤት ናቸው። ተከራዮች ይህንን ካልከፈሉ በወር ከ2 ሺህ ዶላር በላይ ገንዘብ ያጣሉ። ይህንን ነው በነጻ የሰጡት።

"በዚህ ጊዜ ከእነርሱ ጋር መስራትና መረዳዳት ያስፈልጋል" ብለዋል።

በኦንላይን የዳንስ ትርኢት የምታቀርበዋ ቱኒዚያዊት

ቱኒዚያዊቷ ዳንሰኛ ኔርሚን ስፋር በእንቅስቃሴ ገደብ ቤት ውስጥ ተዘግተው ለሚገኙ የሰሜን አፍሪካ ሕዝቦች ዳንስ በማቅረብ ታዝናናቸዋለች።

ከቤቷ ሆና የምታስተላልፈውን የዳንስ ትርኢትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በፌስቡክ ተከታትለውታል።

ዳንሰኛዋ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ "እናንተ ቤታችሁ ቆዩ፤ እኔ እደንስላችኋለሁ" የሚል ዘመቻ ከፍታ ነበር።

ለአድናቂዎቹ የምግብ የከፈለው ናይጀሪያዊው እግር ኳስ ተጫዋች

የናይጄሪያ ፕሪሚየር ዲቪዥን እግር ኳስ ተጨዋች ለአራት አድናቂዎቹ በወረርሽኙ ጊዜ ምግብ መመገብ የሚያስችላቸውን ገንዘብ ሰጥቷቸዋል።

የፕላቶ ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ቺኔዱ አኖዜ፤ ለአራቱ አድናቂዎቹ ለእያንዳንዳቸው 5 ሺህ የናይጄሪያ ናይራ (14 ዶላር) ለግሷል።

ይህም በጣም ትንሽ ልገሳ ነው ብሏል።

የናይጄሪያ ፕሪሚየር ዲቪዥን እግር ኳስ ተጨዋች ቺንዳዉ አኖዜ

የፎቶው ባለመብት, LMC Media