በአፍጋኒስታን የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ

ታትሟል
በምሥራቅ አፍጋኒስታን አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን መከስከሱን ባለስልጣናት ገለጹ።
ከዋና ከተማዋ ካቡል ደቡብ ምዕራብ በምትገኘው የጋዝኒ ግዛት ውስጥ ደህ ያክ በተባለ ቦታ አውሮፕላኑ መከስከሱን የአካባቢው ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም አውሮፕላኑ በቴክኒክ ችግር ምክንያት መከስከሱንና በእሳት መያያዙን ገልጸዋል።
መጀመሪያ ላይ አውሮፕላኑ ዘ አሪያና የተባለው አየር መንገድ ንብረት እንደሆነ ቢነገርም በኋላ የወጡ መረጃዎች ደግሞ አየር መንገዱ አውሮፕላኑ የእኔ አይደለም ማለቱን የሚያትቱ ናቸው።
"የአሪያና አውሮፕላኖች ሁሉም በሰላም ደርሰዋል። ይህ ማለት የተከሰከሰ የአሪያና አውሮፕላን የለም ማለት ነው" ይላል ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በወጡ መረጃዎች።
አውሮፕላኑ በእሳት መያያዙም እየተነገረ ነው። ለጊዜው የተጎጂዎች ማንነትም ሆነ ቁጥር አልተገለጸም።












