የዝውውር ጭምጭምታ፡ ዛሃ፣ ቤንቴኬ፣ ባብል፣ ጎትዘ፣ ትራዎሬ፣ ቪዳል እና ሌሎች

ትራዎሬ እና ዊልፍሬድ ዛሃ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, አዳማ ትራዎሬ እና ዊልፍሬድ ዛሃ
ታትሟል

የጄነዋሪ ወር የተጫዋቾች የዝውውር ጭምጭምታ፡ ዛሃ፣ ቤንቴኬ፣ ባብል፣ ጎትዘ፣ ትራዎሬ፣ ቪዳል እና ሌሎችም

ቼልሲ የክርስታል ፓላሱን እና የአይቮሪ ኮስት የፊት መስመር ተጫዋቹን ዊልፍሬድ ዛሃን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ኤክስፕረስ አስነብቧል።

ይሁን እንጂ ቼልሲዎች፤ ክሪስታል ፓላሶች የጠየቁትን 80 ሚሊዮን ፓዎንድ ለመክፈል ዝግጁ አይመስሉም።

Presentational grey line

ማንችስተር ሲቲ የዎልቭሱን ፈርጣማ አጥቂ አዳማ ትራዎሬን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው። ዎልቭስ በዘንድሮ የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች በሲቲዎች ላይ የበላይነትን ሲቀዳጁ የ23 ዓመቱ አዳማ ትራዎሬ ተጽእኖ ፈጣሪ ተጫዋች ነበር። ይህን የዘገበው ማንችስተር ኢቪንንግ ኒውስ ነው።

Presentational grey line

የባርሴሎና እና የቺሊ አማካይ አርቱሮ ቪዳል ወኪል ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር እንደሚነጋገር የዘገበው ሚረር ነው። እንደዘገባው ከሆነ፤ ቪዳል በጃንዋሪ የዝውውር መስኮት ወደ ማንችስተር ሊያቀና ይችላል።

Presentational grey line

አስቶን ቪላዎች የክሪስታል ፓላሱን ክሪስቲያን ቤንቴኬን ለማስፈረም ንገግር ላይ መሆናቸውን የዘገበው ቴሌግራፍ ነው።

አስቶን ቪላ የቀድሞ የሊቨርፑል የአሁኑን የኤሲ ሚላን ግብ ጠባቂ ፔፔ ሬይናን እንዲያስፈርሙ ጥያቄ እንደቀረበላቸው ደግሞ ሜይል ዘግቧል።

Presentational grey line

ጀርመን የ2014ቱን የዓለም ዋንጫ ስታነሳ ማሸነፊያ ጎሉን ያስቆጠረው ማሪዮ ጎትዘ የውድድር ዓመቱ ሲጠናቀቅ በነጻ ዝውውር ከቦሪሲያ ዶርትመንድ እንደሚለያይ የዘገበው ሚረር ነው። በዘገባው ጎትዘ ወዴት ሊያቀና እንደሚችል አልተጠቀሰም።

Presentational grey line

ኒውካስትል ዩናይድ የቀድሞውን የሊቨርፑል አማካይ ባብል ከጋላታሳራይ የማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ኤክስፕረስ ዘግቧል። የቱርኩ ክለብ ጋላታሳራይ ባብልን የማሰናበት ፍላጎት እንዳለው እና አያክስም ፍላጎት እንዳለው በዘገባው ተጠቅሷል።

Presentational grey line

ዘጋርዲያን እንደዘገበው ከሆነ ዌስት ሃም የቤኔፊካውን አማካይ ጌድስን ፈርናንዴስ ለማስፈረም ሲያደርግ የነበረው ጥረት አልተሳካም።

Presentational grey line

ኤቨርተን የጁቬንቱሱን ፈረንሳይዊ አማካይ አድሪያን ራቢዮት የዘንድሮ የውድድር ዓመት እስኪጠናቀቅ ድረስ በውሰት ማዘዋወር እንደሚፈልግ የዘገበው ስፖርት ዊትነስ ነው።

Presentational grey line

ከብራይተን ወደ ሊድስ ዩናይትድ በውሰት የሄደውን የ22 ዓመት ተከላከይ ቤን ዋይት ለማስፈረም ፍላጎት ካላቸው ክለቦች መካከል ሊቨርፑል፣ ቼልሲ እና ቶተነሃም ተጠቃሽ መሆናቸውን ያስነበበው ስካይ ስፖርት ነው።

Presentational grey line

መድፈኞቹ በጃንዋሪ የዝውውር መስኮት ቋሚ ተጫዋች የማስፈረማቸው እድል የተመናመነ መሆኑን፤ ይሁን እንጂ በውሰት ግን ተጫዋች ከሌላ ክለብ ሊያስፈርሙ እንደሚችሉ ጎል አስነብቧል።