የሞሮኮን ንጉሥ የተሳደበው አራት ዓመት ተፈረደበት

የፎቶው ባለመብት, Youtube
ታትሟል
ዝነኛ የሆነው ሞሮኮያዊ ዩቲዩበር የአገሪቱን ንጉሥ በመሳደቡ የአራት ዓመት ጽኑ እስራት እና የ4ሺህ ዶላር መቀጮ ተጣለበት።
ሞሐመድ ሴካኪ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ነበር የንጉሥ ሞሐመድን ንግግር በመተቸቱ እና ሕዝቡን 'አጋሰስ' ብሎ በመስደቡ በቁጥጥር ሥር የዋለው።
ሞሐመድ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ እንደሚል ተነግሯል።
በተመሳሳይ መልኩ ጋዜጠኛ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆነው ኦማር ራዲ፤ የፍርድ ቤት ዳኛን ተሳድባል ተብሎ በቁጥጥር ሥር ውሏል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የመብት ተሟጋቾች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሞሮኮ የዜጎች ነጻነት ላይ ከፍተኛ ገደብ እየተጣለ ነው ይላሉ።
ንጉስ ሞሐመድ ስድስተኛ ከአረብ አብዮት በኋላ ያላቸውን ስልጣን ተመርጦ ስልጣን ለያዘው መንግሥት ያጋሩ ቢሆንም አሁንም ድረስ ወሳኝ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጡት እሳቸው ናቸው እየተባሉ ይተቻሉ።












