ደቡብ ኮሪያ ለፒዮንግያንግ የቆሻሻ ፊኛ መልስ የፕሮፖጋንዳ ስርጭት እጅምራለሁ አለች

በሰሜን ኮሪያ ከተላኩ ፊኛዎች መካከል

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ታትሟል

ደቡብ ኮሪያ በቆሻሻ የተሞሉ ፊኛዎች በሰሜን ኮሪያ አማካይነት ወደ ግዛቷ መላካቸው ተከትሎ ከስድስት ዓመታት በኋላ አቁማ የነበረውን የፕሮፖጋንዳ ስርጭት እንደምትጀመር ገለጸች።

ትናንት እና ከትናንት በስቲያ ሰኔ 1 እና 2 /2016 ዓ.ም. ፒዮንግያነግ ከ300 በላይ በቆሻሻ ወረቀቶች ፕላስቲክ የተሞሉ ፊኛዎችን ወደ ደቡብ አቅጣጫ ልካ 80 የሚሆኑት ደቡብ ኮሪያ ላይ አርፈዋል።

በቆሻሻ የተሞሉ ፊኛዎቿን ወደ ጎረቤት አገር የምትልከው ሰሜን ኮሪያ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ሰጥታ አታውቅም።

ሆኖም ቀደም ሲል ፒዮንግያንግ ደቡብ ኮሪያ የምታሰራጨውን የፕሮፖጋንዳ ስርጭት ጦርነት እንደማወጅ እንድምትቆጥረው ገላጻ ፊኛዎቹን መትቼ እጥላለሁ ስትል ትዝት ነበር።

ሰሜን ኮሪያ ባለፉት ሳምንታት በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ አክቲቪስቶች የፒዮንግያንግ ወታደራዊ መንግሥትን የሚተች የፕሮፖጋንዳ በራሪ ወረቀቶች መላካቸውን ተከትሎ ከ200 በላይ በቆሻሻ የተሞሉ ፊኛዎችን ወደ ደቡብ ልካለች።

ይህ ድርጊት ለተወሰኑ ቀናት ጋብ ብሎ የቆየ ቢሆንም ባለፉት የእረፍት ቀናት ግን ሰሜን ኮሪያ ወደዚህ ድርጊቷ በመመለስ በርካት ቆሻሻ ያዘሉ ፊኛዎችን ወደ ደቡብ ኮሪያ ድምበር አሻግራለች።

ፒዮንግያንግ ይህንን ድርጊት ወደ መፈጸም የተመለሰችው ባለፈው ሳምንት 10 በራሪ ወረቀቶች የተሞሉባቸው ፊኛዎች ከደቡብ ኮሪያ ስለታላኩባት እንደሆነ ኤኤፍፒ ዘግቧል።

የደቡብ ኮሪያ መከላከያ አሁን በሀገሩ ግዛት ላይ ምንም አይነት ፊኛ እንደማይገኝ እና በተላኩትም ውስጥ ጉዳት የሚያስከትል ነገር አለመኖሩን አስታውቋል።

ጨምሮም ዜጎች ፊኛዎቹን እንዳይነኩ እና ከሚወድቁ ቁሶች እንዲጠነቀቁ እንዲሁም የተለየ ነገር ሲመለከቱ ለፖሊስ እንዲጠቁሙ አሳስቧል።

የደቡብ ኮሪያ ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ሰሜን ኮሪያ ድረስ ዘልቀው የሚሰሙት በግዙፍ ስፒኮሮች የሚሰራጨው ፕሮፖጋንዳ ከመጪው ዕሁድ ጀምሮ እንዲቀጥል ወስኗል።

የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት ፊኛዎቹን እንዳይነኩ ይልቁንም ጠቅማ እንዲሰጡ አሳስበወኀዕ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት ፊኛዎቹን እንዳይነኩ ይልቁንም ጠቅማ እንዲሰጡ አሳስበወኀዕ

ባለፈው ሀሙስ በደቡብ ኮሪያ የሚገኝ አንድ ቡድን የሰሜኑን መሪ ኪም ጆንግ ኡንን የሚተቹ በራሪ ጽሁፎች፣ የዶላር ምስሎች እና በሰሜን ኮሪያ የታገዱ የሙዚቃ ቪዲዮዎች የተጫኑባቸው ‘ፍላሽ ዲስክ’ በፊኛዎች ውስጥ አድርገው ልከዋል።

ባለፉት ዓመታት ከደቡብ ኮሪያ የሚሰራጨው የፕሮፖጋንዳ ፕሮግራም ዜናና ስለዴሞክራሲ እንዲሁም በደቡብ ኮሪያ ስላለው ህይወት የሚገልጹ ናቸው።

የደቡብ ኮሪያ መከላከያ እንደሚለው ከሆነ ይህ ስርጭት የሰሜን ኮሪያን ግዛት ዘልቆ ከ10 እስከ 24 ኪሎ ሜትር ይሰማል።

ባለፈው ሳምንት ወደ ፒዮንግያንግ ፊኛዎችን የላከው የደቡብ ኮሪያ ቡድን 20 ፊኛዎችን እንዳሸገረ ገልጿል።

ከ4 ዓመት በፊት የደቡብ ኮሪያ ምክር ቤት ወደ ሰሜን በራሪ ወርቀቶችን መላክ ወንጀል ተደርጎ እንዲቆጥር ወስኖ ነበር።

ሆኖም ይህ በመናገር ነጻነት እና ከሰብዓዊ መብት ጋር የሚቃረን ነው በሚል ትችት ገጥሞት ነበር።

ሰሜን ኮሪያም ለዚህ አጸፋ ሲዉል የሚገኙ ባለስልጣንትን የሚሸነቁጡ ወረቀቶችን የያዙ ፊኛዎች ወደ ደቡብ ኮሪያ ልካ ነበር።

ከ8 ዓመታት በፊት ሰሜን ኮሪያ የመጸዳጃ ቤት ወረቀቶችን፣ የሲጋራ ቁራጭ እና ሌሎች ቆሻሻዎችን የያዙ ፊኛዎችን ወደ ደቡብ ጎረቤቷ ልካለች። የደቡብ ኮሪያ ፖሊስ ፊኛዎቹ ውስጥ ጉዳት የሚያስከትሉ የኬሚካል ውህድ እንዳላቸው ገልጾ ነበር።