ካሊፎርኒያ ተጨማሪ የበረዶ ውሽንፍር እያስተናገደች ነው

የፎቶው ባለመብት, EPA
በካሊፎርኒያ በዚህ ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ አንድ ተጨማሪ የበረዶ ውሽንፈር እየታየ ሲሆን ከባድ ዝናብ እና በረዶ አስከትሏል። ከአየር ጸባዩ ጋር በተገናኘ ቢያንስ 19 ሰዎች ሕይወታቸው አጥተዋል።
በካሊፎርኒያ ግዛት አንዳንድ አከባቢዎች ሰኞ ምሽቱን እና ማክሰኞ ንጋት ላይ ዝናብ እና በረዶ ውሽንፍር እንደሚከሰት ተተንብዮ ነበር።
በዚህ ሳምንት የአየሩ ሁኔታ ወደ መደበኛ እንደሚመለስ ቢጠበቅም በርካታ አከባቢዎች የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ ተገርጦባቸዋል።
ባለፈው ሳምንታት በበረዶ ውሽንፍር የተመታችው ካሊፎርኒያ ነዋሪዎቿን በጎርፍ ከመጠለቅለቁ ባሻገር አከባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ምክንያት ሆኗል።
በተከታታይ የተከሰተው ጎርፍ መንገዶች እንዲሸረሸሩ እና ዛፎች እንዲወድቁ አድርጓል። የበረዶ ውሽንፍሩ ዕጽዋት የተተከለባቸው አፈርን በማዳከሙ የበለጠ አደጋን ጋርጧል።
ከትላንት ሰኞ ጀምሮ ስምንት ሚሊዮን ሰዎች በከሊፎርኒ ማዕከላዊ የባሕር ዳርቻዎች በጎርፍ የተከበቡ ሲሆን 38 ሺህ 600 ሰዎች ከኤሌክትሪክ አቅርቦት ጋር ተቋራርጠዋል።
በካሊፎርኒያ ግዛት ሳካርሜንቶ ከተማ የአየር ትንበያ አገልግሎት ከመጠነኛ እስከ ከባድ በረዶ እስከ ሰኞ ሊቀጥል እንደሚችል የተነበየ ሲሆን በደቡብ ካሊፎርኒያ ከሰኞ እስከ ማክሰኞ ጠዋት ድረስ ከባድ ዝናብ እንደሚጥል ይጠበቃል።
የካሊፎርኒያ ገዢ ጋቪን ኒዎስም ነዋሪዎች በጥንቃቄ እንዲቆዩ ያሳሰቡ ሲሆን በቀጣዮች ከ24 እስከ 48 ሰዓት የሚመጡ ክስተቶችን በንቃት እንዲከታተሉም ጥሪ አቀርበዋል።
የካሊፎርንያ ሰማይ ከማክሰኞ ጀምሮ ፀሐይማ እንሚሆን የአየር ትንበያ አግልግሎቱ የተነበየ ሲሆን ሆኖም በአንዳንድ አካቢዎች ከዕረቡ እስከ ሀሙስ ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታው ይቀጥላል ብሏል።
ፕሬዝዳንት ባይደን ቅዳሜ ምሽት ላይ በአሜሪካ ከፍተኛ ሕዝብ በሚኖርባት ካሊፎርኒያ የአደጋ ጊዜን አውጀዋል።
“በትውልድ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለው” ተከታታይ የበረዶ ውሽንፍር በካሊፎርኒያ ግዛት በመቆም ወደ መደበኛ አየር ሁኔታ እየተመለሰ ነው።
በአጠቃላይ 19 ሰዎች መሞታቸው የተረጋገጠ ሲሆን በጎርፍ የተወሰደ አንድ የ5 ዓመት ሕጻየገባበት አልታወቅም።
ከባለፈው ወር የመጨረሻዎቹ ቀናት እስከ ጥር መግቢያ ድረስ በአንዳንድ የካሊፎርኒያ ግዛት አከባቢዎች ከወትሮው በ6 እጥፍ ሚበልጥ ዝናብ ተከስቷል።
ባለፈው ሳምንት ሳንታ ባራባራ በተባለው አከባቢ ከፍተኛ ዝናብ ተከስቷል።
በተጨማሪም የበረዶ ውሽንፍር እንደ ሳንታ ክሩዝ እና ሳን ፍራንሲስኮ ባሉ የባሕር ዳርቻ አከባቢዎች የመሬት መሰርጎድ እንዲፈጠር እና ሺዎች ከኤሌክትሪክ አቅርቦት ጋር እንዲቋራረጡ ሰበብ ሆኗል።












