በዓለም ዙሪያ ያሉ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች የገና በዓል አከባበር በምስል

ታትሟል

በመላው ዓለም የሚገኙ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዛሬ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን (ገና) እያከበሩ ነው።

በዓለም ዙሪያ ከ200 ሚሊዮን በላይ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የሚገኙ ሲሆን የልደት በዓልን በተለየ ዕለት ያከብሩታል።

አብዛኞቹ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በምሥራቅ አውሮፓ አገራት ውስጥ የሚገኙ ቢሆንም በዓሉ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎችም የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ውስጥ እየተከበረ ነው።

የበዓሉን አከባበር የሚያሳዩ ፎቶዎች እነሆ።

የገና በዓል በድምቀት ከሚከበርባቸው አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ፣ በላሊበላ የቅድስት ማሪያም ቤተ ክርስቲያን የገና በዓል ዋዜማ ደማቅ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የገና በዓል በድምቀት ከሚከበርባቸው አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ፣ በላሊበላ የቅድስት ማሪያም ቤተ ክርስቲያን የገና በዓል ዋዜማ ደማቅ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።
ሩሲያ ሞስኮ ውስጥ በሚገኘው የመድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን የተካሄደውን የገና በዓል ሥነ ሥርዓት 110 ሚሊዮን አማኞች ያላት የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጳጳስ የሆኑት ፓትሪያርክ ኪሪል ሲመሩ።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሩሲያ ሞስኮ ውስጥ በሚገኘው የመድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን የተካሄደውን የገና በዓል ሥነ ሥርዓት 110 ሚሊዮን አማኞች ያላት የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጳጳስ የሆኑት ፓትሪያርክ ኪሪል ሲመሩ።
ከዩክሬን ጋር ጦርነት ላይ የሚገኙት የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን ቤተመንግሥታቸው ክሬምሊን ውስጥ በተካሄደው የፀሎት ሥነ ሥርዓት ላይ በተገኙበት ጊዜ። ፑቲን የገናን በዓል በማስመልከት የአጭር ጊዜ ተኩስ እንዲደረግ ጥሪ ቢያቀርቡም ዩክሬን ሳትቀበለው ቀርታለች።

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, ከዩክሬን ጋር ጦርነት ላይ የሚገኙት የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን ቤተ መንግሥታቸው ክሬምሊን ውስጥ በተካሄደው የፀሎት ሥነ ሥርዓት ላይ በተገኙበት ጊዜ። ፑቲን የገናን በዓል በማስመልከት የአጭር ጊዜ ተኩስ እንዲደረግ ጥሪ ቢያቀርቡም ዩክሬን ሳትቀበለው ቀርታለች።
በጦርነት ውስጥ ባለችው የዩክሬን ዋና ከተማ ኪዬቭ በሚገኘው ቅዱስ ቮሎዲሚር ካቴድራል ምዕመናን ሻማ ሲያበሩ። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዩክሬናውያን የገና ዓልን ለማክበር ወደ አብያተክርስቲያናት ሄደዋል።

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, በጦርነት ውስጥ ባለችው የዩክሬን ዋና ከተማ ኪዬቭ በሚገኘው ቅዱስ ቮሎዲሚር ካቴድራል ምዕመናን ሻማ ሲያበሩ። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዩክሬናውያን የገና ዓልን ለማክበር ወደ አብያተ ክርስቲያናት ሄደዋል።
በሰርቢያ ዋና ከተማ ቤልግሬድ ውስጥ በሚገኘው የቅድስት ሳቫ ቤተክርስቲያን ውስጥ በተከበረው የልደት በዓል ላይ የችቦ ማብራት ሥነ ሥርዓት ሲካሄድ። የሚነደው ችቦ ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ጊዜ  ግርግሙን ለማሞቅ እረኞች የለኮሱትን እሳት ለማስታወስ ይውላል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በሰርቢያ ዋና ከተማ ቤልግሬድ ውስጥ በሚገኘው የቅድስት ሳቫ ቤተክርስቲያን ውስጥ በተከበረው የልደት በዓል ላይ የችቦ ማብራት ሥነ ሥርዓት ሲካሄድ። የሚነደው ችቦ ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ጊዜ ግርግሙን ለማሞቅ እረኞች የለኮሱትን እሳት ለማስታወስ ይውላል።
ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደባት ቤተልሔም ውስጥ በሚገኘው ቤተክርስቲያን ውስጥ ለኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ዋነኛ ከሆኑት በዓላት መካከል አንዱ የሆነውን የልደት በዓል ለማክበር ምዕመናን ተሰባስበው።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደባት ቤተልሔም ውስጥ በሚገኘው ቤተክርስቲያን ውስጥ ለኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ዋነኛ ከሆኑት በዓላት መካከል አንዱ የሆነውን የልደት በዓል ለማክበር ምዕመናን ተሰባስበው።