በርካታ አማኞች የእስራኤል ፖሊስ ክልከላን ተላልፈው የፋሲካን ዋዜማን ጧፍ በማብራት አከበሩ

ኢትዮጵያዊያን በበዓሉ ላይ ታድመዋል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

በእስራኤል ፖሊሶች እገዳ ቢጣልባቸውም በሺዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ቅዳሜ ዕለት በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውን በዓል በኢየሩሳሌምን አክብረዋል።

በፋሲካ በዓል ዋዜማ ጧፍ በማብራት በሚከበረው ሥነ-ሥርዓት ላይ የእስራኤል ፖሊስ ክልከላን ተላልፈው በርካታ ሕዝብ ምሥራቅ እየሩሳሌም በሚገኘው ቅዱስ ሰፑከ ተገኝቶ አክብሯል።

ስፍራው ክርስቲያኖች ኢየሱስ የተሰቀለበት እና የተቀበረበት እንደሆነ የሚያምኑበት ቦታ ነው።

ፖሊሶች በደኅንነት ስጋት ከውስጥ 1,800 እና ከውጭ ደግሞ 1,200 ሰዎች ብቻ እንዲገኙ ገደብ ጥለው ነበር።

የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እና ምዕመናን ግን ክልከላውን ችላ በማለት በከፍተኛ ቁጥር በበዓሉ ላይ ተሳታፊ ለመሆን ምሥራቅ እየሩሳሌም ተገኝተዋል።

የኢየሱስን ትንሳኤ በሚያመለክተው ሥነ-ሥርዓት ላይ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ አማኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

አማኞች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ቅዳሜ ከሰዓታት የግሪክ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ በጉጉት ወደ ሚጠባበቋቸው አማኞች ከመቃብር ስፍራው የበራ ሻማ ይዘው ወጠዋል። ይህ ስርዓት ከእሁድ የኦርቶዶክስ ፋሲካ በፊት በየዓመቱ የሚከናወን ስነ-ስርዓት ነው።

ሻማው በቤተ ክርስቲያኑ በጉጉት ለሚጠባበቁ ሁሉ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፈፋል።

በቀደሙት ዓመታት ወደ 10,000 የሚጠጉ ምዕመናን በቤተክርስቲያኗ እና በአቅራቢያው ባሉ መንገዶች ታጭቀው ሰነ ስርዓቱን ያከብራሉ።

ሻም የሚጠብቁ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ነገር ግን ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የቤተክርስቲያን መሪዎች ከደኀንነት ስጋቶች ጋር በተያያዘ የተሳታፊዎች ቁጥር እንደሚገደብ ተነግሯቸው ነበር።

የፖሊስ ቃል አቀባይ ሰርጀንት ዲን ኤልስዱን ቀደም ሲል እንደተናገሩት “ከውጭ መሐንዲሶች ጋር ተነጋግረን በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የሚፈቀደው የሕዝብ ብዛት ገደብ እንዳለው ከገለፁልን በኋላ በእነዚህ መሐንዲሶች በተሰጡት መግለጫ ህዝቡን እየገደብን ነው” ብለዋል።

አብያተ ክርስቲያናት እገዳዎች አያስፈልጉም በማለት ውሳኔውን ሲቃሙ ነበር።

አማኖች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የእስራኤል ፖሊሶች በመግቢያው እና በከተማው ዙሪያ ኬላዎችን መትከላቸውን ተከትሎ በሺህዎች የሚቆጠሩ አማኞች ወደ ቤተክርስቲያኑ መድረስ እንዳልቻሉም ተዘግቧል።

እገዳው የአካባቢውን የክርስቲያን ማህበረሰብ ለመግፋት የቆዩ ጥረቶች አካል ናቸው ሲሉ አብያተ ክርስቲያናቱ ተቃውሞ አሰምተዋል።