የክሪስ ሱቶን ግምቶች፡ አርሴናል አቻ ሲወጣ ሊቨርፑል ይሸነፋል!

አርቴታ እና ማርቲኔሊ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የፕሪሚየር ሊጉን ሰንጠረዥ እየመራ የሚገኘው አርሰናል ዛሬ ጨዋታውን ያደርጋል።
ታትሟል

ያለፉት ሳምንታት የእግር ኳስ ወዳጆች ትኩረት የኳታር የዓለም ዋንጫ ነበር።

የእንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ ከስድስት ሳምንታት በኋላ ዛሬ በቦክሲንግ ደይ ይመለሳል።

“አዲስ የውድድር ዓመት የመጀመር ስሜት ይፈጥራል” ሲል የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን ገልጿል።

“ቡድኖቹ ተጫውተው እስከምንመለከት ምን እንደሚፈጠር ለመገመት ከባድ ነው” ይላል።

ሰኞ

ብሬንትፎርድ ከ ቶተንሃም

ብሬንትፎርድ ከ ቶተንሃም

ከዓለም ዋንጫው በፊት ቡድኖችን ያስመዘገቡትን ውጤት ማስታወስ ከባድ ቢሆንም ብሬንትፎርድ በኢቫን ቶኒ ጎሎች ማንቸስተር ሲቲን ያሸነፈበትን ጨዋታ መርሳት አይቻልም።

ለእንግሊዝ ያልተመረጠው ቶኒ በነበረበት አቋሙ ለመቀጠል ሲያልም ሃሪ ኬንም ከዓለም ዋንጫው መልስ ውጤታማ ለመሆን ይጥራል።

ሰን ሂውንግ ሚን እና ዴጃን ኩሉሴቭስኪ ከጉዳት አገግመው ለስፐርሶች ይሰለፋሉ። ሪቻርልሰን ግን በጉዳት ከሜዳ ይርቃል።

ጨዋታው ድንቅ ሆኖ የፕርሚየር ሊጉን መመለስ ቢያበስር ምኞቴ ነው። ግን ቀዝቀዛ ጨዋታ ሆኖ አቻ እንደሚጠናቀቅ ውስጤ ይነግረኛል።

ግምት፡ 1 – 1

ክሪስታል ፓላስ ከ ፉልሃም

ይህን ጨዋታ መገመት ከባድ ነው። ምክንያቱ ደግሞ ፉልሃም ውድድሩ ከመቋረጡ በፊት ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡ ነው።

ፉልሃም ጥሩ ጉዞ ላይ ሲገኝ ፓላስ ደግሞ ከግምት በታች ሆኗል።

በሜዳቸው ጥሩ በመሆናቸው በዚህ ጨዋታ ግምቴን ለፓላስ እሰጣለሁ።

ግምት፡ 2 – 1

ኤቨርተን ከ ዎልቭስ

ይህ ጨዋታ ለሁለቱም ቡድኖች ወሳኝ ቢሆንም ኤቨርተኖች ደግሞ ይበልጥ ይፈልጉታል።

የዎልቭሱ አዲሱ አሰልጣኝ ዩለን ሎፕቴጊዩ ቡድናቸውን የሚያሳዩበት ምርጥ አጋጣሚ ነው።

ጎል ማስቆጠርን ጨምሮ ዎልቭስ ብዙ መሻሻል ይጠበቅባታል። ኤቨርተንም ከዓለም ዋንጫው በፊት የአቋም መውረድ ገጥሞታል።

ኤቨርተን ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ አለበት። እንደሚያሰንፉም እገምታለሁ።

ግምት፡ 1 – 0

ሌስተር ከኒውካስትል

ሌስተር ከ ኒውካስል

ሁለቱም ቡድኖች ከዓለም ዋንጫው በፊት ጥሩ ውጤት እያስመዘገቡ ነበር።

ሌስትር ከአምስት ጨዋታ አራቱን አሸንፏል። ኒውካስል ደግሞ አምስት ጨዋታዎችን በተከታታይ በማሸነፍ ሦስተኛ ደረጃን ይዟል።

ይህን ጨዋታ ባለፈው ዓመት ያሸነፈው ሌስተር ነው። ዘንድሮ ግን ኒውካስል ሌላ ቡድን ሆኗል። ኒውካስል ሦስቱን ነጥብ እንደሚያሳከ እገምታለሁ።

ግምት፡ 1 – 2

ሳውዛምፕተን ከ ብራይተን

ሳውዛምፐተንም በአዲሱ አሰልጣኝ ናታን ጆንስ ይመራል። አዲስ አሰልጣኝ ቢሾሙም ከሊጉ የሚወርዱ ይመስለኛል።

በቀድሞው አሰልጣኝ ራልፍ ሃሰንሃትል ስር ቢቆዩ ላይወርዱ ይችላሉ የሚል ግምት አለኝ።

ከፊታቸው ያሉት ጨዋታዎች ነጥብ ለመሰብሰብ የሚመቹ ናቸው።

ይህ ጨዋታ ግን ይከብዳቸዋል። በሮቤርቶ ዲ ዜርቢ የሚመሩት ብራይተኖች በነጻነት ከመጫወት ሌላ ጎሎችን እያስቆጠሩ ነው።

ግምት፡ 2 – 2

አስቶን ቪላ ከሊቨርፑል

አስቶን ቪላ ከ ሊቨርፑል

ሊቨርፑሎች ሐሙስ ምሽት ከማንቸስተር ሲቲ ጋር በነበራቸው የካራባኦ ዋንጫ ጨዋታ ጥሩ ነበሩ።

ዕድላቸውን ካለመጠቀማቸውም በላይ ተከላካይ መስመራቸውም አስተማማኝ አይደለም።

ከዓለም ዋንጫው በኋላ አንድ አስገራሚ ውጤት እንደሚመዘገብ እጠብቃለሁ።

የቪላው አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ዕድላቸውን ለመጠቀም እየተጠባበቁ ይመስለኛል።

ግምት፡ 1- 0

አርሰናል ከ ዌስት ሃም

አርሴናል ከ ዌስት ሃም

ሊጉ በዓለም ዋንጫው ምክንያት መቋረጡ ለሊጉ መሪ አርሴናሎች ጥሩ የሚባል አይደለም። ጥሩ ብቃት ላይ የነበረውን ጋብርኤል ጄሱስን በጉዳት አጥተዋል።

ጄሱስ በመጨረሻ ጨዋታዎች ጎሎችን ባያስቆጥርም ለቡድኑ የጨዋታ ፍሰት እና ኳስን ለመንጠቅ በሚደረገው ሥራ ትልቅ ተሳትፎ ነበረው።

ቡድኑ ውስጥ ካሉ ተጫዋቾች እሱን የሚተካ የለም። የጉዳቱ መጠን ሌላ ተጫዋች እንዲገዙ ሊያስገድዳቸው ይችላል።

በዚህ ዓመት ዌስተ ሃሞች ጥሩ ውጤት እንደሚያስዘግቡ ደጋግሜ ገምቼ ነበር። በዚህ ጨዋታ ግን የሚሸነፉ አይመስሉም።

ግምት፡ 1 – 1

ማክሰኞ

ቼልሲ ከ በርናማውዝ

ከስድስት ጨዋታዎች በአራቱ የተሸነፉት ቼልሲዎች ሁለቱን አቻ ተለያይተዋል። በዚህ ምክንያት አሰልጣኝ ግርሃም ፖተር ጫና ውስጥ ገብተዋል።

ፖተር ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው አምናለሁ። ቡድኑ የጎል ማስቆጠር ችግሩን መቀርፍ ይኖርበታል።

ይህን ጨዋታ ቼልሲ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ። የበርንማውዝ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ግን አሁንም አጓጊ ነው።

ጊዜያዊው አሰልጣኝ ጋሪ ኦኔል ቡድኑን በቋሚነት ለመምራት ውጤታማ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

ግምት፡ 2 – 0

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

የውድድር ዓመቱ ሲጀመር ኖቲንግሃም ፎረስ የሚወርድ አልመሰለንም ነበር። አሁን ግን አቅጣጫቸው ወደዚያ ይመስላል።

ፎረስቶች ራሳቸውን ለማዳን ጊዜ ቢኖራቸው በሜዳ ላይ ውጤታማ አይደሉም።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ማንቸስትርን ለቋል። ቡድኑ ያለ ኮከቡ ጥሩ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ይህን ጨዋታ ለማሸነፍ መታገል ይጠበቅባቸዋል።

ግምት፡ 1 – 0

ረቡዕ

ሊድስ ከ ማንቸስተር ሲቲ

ሐሙስ ምሽት በካራባኦ ዋንጫ ማንቸስተር ሲቲ ጠንካራ ቡድኑን ከሊቨርፑል ጋር አሰልፎ ብኣቱን አሳይቷል።

የሊድስ አጨዋወት ይመቸኛል።

የኤላንድ ሮድ ድባብ ሁሌም አስደናቂ ነው። ይህ ግን ቡድኑን አይጠቅመውም።

ግምት፡ 0 – 4