ወረፋውን ሳይጠብቅ የንግስቲቱን የሬሳ ሳጥን ቀርቧል የተባለው ግለሰብ ተከሰሰ

የፎቶው ባለመብት, PA Media
በዚህ ሳምንት አርብ ንግሥቲቱን ለመሰናበት በነበረ ሰልፍ ላይ ወረፋውን ሳይጠብቅ ወደ ንግሥቲቱ የሬሳ ሳጥን የቀረበው ግለሰብ ተከሰሰ።
የ28 አመቱ ግለሰብ የህዝብ ትዕዛዝን በመጣስ ነው ክስ የቀረበበት
በምስራቅ ለንደን ነዋሪ የሆነው መሀመድ ካን ሰኞ ዕለት በዌስት ሚኒስትር ፍርድ ቤት ይቀርባል።
የሜትሮፖሊታን ፖሊስ እንዳበለው በህዝባዊ ትዕዛዝ ህግ መሰረት ተከሷል ብሏል።
ግለሰቡ ሰልፉን አቋርጦም ወደ ንግሥቲቱ እሰከሬን ሲጠጋም በዌስት ሚኒስትር አዳራሽ የነበረው የቀጥታ ስርጭትም ተቋርጧል።
ፖሊስ በመግለጫው “በምስራቅ ለንደን ነዋሪ የሆነው የ28 ዓመቱ መሐመድ ካን ትናንት ቅዳሜ በህዝባዊ ትዕዛዝ ህግ መሰረት ትንኮሳ፣ ጭንቀት፣ ወይም የሚረብሽ ሁኔታ በመፍጠርም” በሚሉ ወንጀሎች ተከሷል ብሏል።
ነገ ሰኞ መስከረም 9፣ 2015 ዓ.ም በዌስት ሚኒስትር ፍርድ ቤት ይቀርባል።
ንግሥቲቱን ለመሰናበት ካለው ሰልፍና ወረፋም ጋር ተያይዞ ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ የተከሰሰ ሁለተኛ ሰው ነው።
አንድ የ19 አመት ወጣት ረቡዕ ዕለት በቪክቶሪያ ታወር ጋርደንስ በነበረ ወረፋ ላይ ራሱን በማጋለጥ እንዲሁም ከኋላው ኃዘንተኞች በመግፋት ተከሷል።
አዲዮ አዲሺኔ በወሲባዊ ትንኮሳ ሁለት ክሶች የቀረበበት ሲሆን በጥቅምት አጋማሽ ላይ በሳውዝዋርክ ክራውን ፍርድ ቤት ይቀርባል።
ሟቿ ንግሥት ኤልዛቤት 2ኛ ሰኞ መስከረም 9፣ 2015 ዓ.ም የቀብር ስነ ስርዓታቸው እስከሚፈጸም ድረስ አስከሬናቸው በዌስት ሚኒስትር አዳራሽ ይቆያል።












