በለንደን የታጠቁ ፖሊሶችን እጥረት ለመሙላት መከላከያ ወታደሮች ላሰማራ አለ

የለንደን ፖሊሶች

የፎቶው ባለመብት, AFP

ታትሟል

በለንደን የሚገኙ ፖሊሶች የጦር መሳሪያ ትጥቃቸውን ማስረከባቸውን ተከትሎ የአገሪቱ መከላከያ ድጋፍ እንዲሰጡ ወታደሮችን ለማሰማራት ጠየቀ።

ከአንድ ወጣት ግድያም ጋር በተያያዘ ከ100 በላይ ፖሊሶች የጦር መሳሪያ መያዝ የሚያስላቸውን ፍቃድ እንዲመልሱ መደረጋቸውንም አንድ ምንጭ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በለንደን ከ2ሺህ 500 በላይ የታጠቁ ፖሊሶች አሉ።

ይህ እርምጃ እየተወሰደ ያለው የጦር መሳሪያ ያልታጠቀ አንድ ግለሰብ በፖሊስ መገደሉን ተከትሎ ነው።

በለንደን ፖሊሶች የተገደለው ግለሰብ ዕድሜው 24 ዓመት ሲሆን ክሪስ ካባ ይሰኛል።

የለንደን ፖሊስ ዋና ኃላፊ ሰር ማርክ ሮውሊ የሃገር ውስጥ ጽሕፈት ቤት በታጠቁ ፖሊሶች ላይ ያደረገውን ግምገማ በበጎ እንደሚቀበሉት አስታውቀዋል።

ለሃገር ውስጥ ጽህፈት በጻፉት ደብዳቤ ፖሊሶቹ በዚህ ደረጃ መያዛቸው ትክክል እንደሆነ ቢያምኑም ነገር ግን አሁን ያለው አሰራር የፖሊስ አባላቶቹ ላይ ተፅእኖ እያደረሰ ነው ። ተጨማሪ የህግ ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።

ክሪስ ካባን ተኩሶ የገደለው ፖሊስ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር።

አንዳንድ የፖሊስ አባላትም አቃቤ ህግ በፖሊሱ ላይ ክስ ለመመስረት መወሰኑ “በእነሱ ላይ ስለሚያሳድረው ተፅእኖ” ስጋት ገብቷቸው እንደነበር ሜት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ከጥቂት ወራት በፊት የጦር መሳሪያ ትጥቁን የፈታ አንድ የቀድሞ ፖሊስ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ እና በቤተሰቦቻቸው ላይ የተጋረጠው አደጋም “በጣም ከፍተኛ” ነው ሲልም ለቢቢሲ ተናግሯል።

ስሜ አይጠቀስ ያለው ፖሊስ “ለእኔ ግልጽ የሆነው ጉዳይ ፖሊሶች በንዴትም ሆነ በደም ፍላት የሚሰሩ አይደሉም”

“እነዚህ የፖሊስ አባላት የትዳር አጋሮች እና ቤተሰቦች ያሏቸው ናቸው። ለሙያቸውም ቁርጠኛ ናቸው” ብሏል

የመከላከያ ኃይል ወታደሮች ፖሊሶችን በስራ ለማገዝ ከተገደዱ “በጣም አሳዛኝ ቀን ነው” ሲልም ተናግሯል።

ባለፈው ዓመት መስከረም ላይ መኪና እየነዳ በነበረበት ወቅት ነበር ክሪስ ካባ በፖሊስ በጥይት የተመታው።

አባት ለመሆን ወራቶች ብቻ ቀርተውት የነበረው ክሪስ በማግስቱ በሆስፒታል ህይወቱ አለፈ።

የግንባታ ሰራተኛው ንብረትነቱ የሱ ያልሆነ መኪና እያሽከረከረ ነው የተገደለው።

ሞቱም በርካታ ተቃውሞዎችን አስከትሏል።